TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
#Ethiopian_PremierLeague

የ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ #አራተኛ እስከ #ዘጠነኛ ሳምንት በሀዋሳ ከተማ መካሄዱን ሲቀጥል የጨዋታ ሰዓቶች እና የደጋፊዎች የስታዲየም አገባብ አስመልክቶ አክስዮን ማህበሩ ወቅታዊ መረጃ አጋርቷል ።

በፕሮግራሙ መሰረት በየሳምንቱ ስምንት ጨዋታዎች ላይ የመጀመሪያው ጨዋታ በ 9፡00 ሰዓት እንዲሁም ሁለተኛው በ 12፡00 ሰዓት የሚደረጉ ይሆናል ።

በ ሁሉም ጨዋታዎች የኮቪድ ፕሮቶኮሉ ተጠብቆ የ ሐዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ለደጋፊዎች ክፍት ሲሆን ማንኛውም ተመልካች ወደ ስታዲየም ሲመጣ ከመግቢያ ትኬት በተጨማሪ ማንነቱን የሚገልፅ #መታወቂያ መያዝ ይኖርበታል ።

የስታዲየም መግቢያ ትኬት ባለ ሜዳ ክለቦች በሚያመቻቹት መንገድ የሚሸጥ መሆኑን የ አክስዮን ማህበሩ አሳውቋል ።

* ሙሉ የውድድር መርሐ ግብሩ በምስሉ ላይ ተያይዟል ።

#Betika
#CentralHawassaHotel

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ነጥብ ሲጥል ቼልሲ ድል ቀንቶታል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በውድድር ዘመኑ ለአራተኛ ጊዜ አቻ ሲወጡ በሜዳቸው ከ ብራይተን ጋር ሶስት አቻ ተለያይተዋል።

√ ሮቤርቶ ፊርሚንሆ ሁለት ጎሎች እና ዌብስተር በራሱ ላይ የሊቨርፑልን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ትሮሳርድ በአንፊልድ ሀትሪክ በመስራት የብራይተንን ሶስት ጎሎች ከመረብ አሳርፏል።

√ በአሰልጣኝ ግራም ፖተር የሚመራው ቼልሲ በኦባምያንግ እና ጋላግሀር ጎሎች ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችለዋል።

√ ትሮስራድ ከአስራ አራት ዓመታት በኋላ #በሊጉ #በአንፊልድ ሀትሪክ መስራት የቻለ ተጫዋች ሆኗል።

√ በሌሎች የሊጉ መርሐ ግብሮች #ኤቨርተን እና #ኒውካስትል ተጋጣሚዎቻቸውን ረተዋል።

√ ሊቨርፑል አስር ነጥቦችን በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት ብራይተኖች በአስራ አራት ነጥቦች #አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

√ የለንደኑ ክለብ ቼልሲ በአስራ ሶስት ነጥብ #አምስተኛ ላይ ሲቀመጡ በቀጣይ ከ ዎልቭስ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

√ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ #አርሰናል እንዲሁም ብራይተን ከ #ቶተንሀም ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል በሜዳው ተረቷል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ስታዲየም በሊድስ ዩናይትድ 2ለ1 ተረተዋል።

√ ሮድሪጎ እና ሰመርቪል የጄሲ ማርሹን ቡድን አሸናፊ ያደረጉ ሁለት ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

√ ሞሀመድ ሳላህ ቀያዮቹን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።

√ ሮድሪጎ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ስድስተኛ ጎሉን በሊጉ ለሊድስ ዩናይትድ ማስቆጠር ችሏል።

√ ሞሀመድ ሳላህ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ አስራ አንድ ከፍ አድርጓል።

√ የየርገን ክሎፑ ስብስብ ሊቨርፑል በሊጉ #አራተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

√ በአስራ ሁለት የሊጉ ጨዋታዎች አስራ ስድስት ነጥቦችን የሰበሰቡት ሊቨርፑሎች #ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው ይገኛሉ።

√ሊቨርፑል በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ከሰሜን ለንደኑ ክለብ #ቶተንሀም ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቀያይ ሴጣኖቹ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !

የእንግሊዝ #EFLCUP የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ቀያይ ሴጣኖቹ የሻምፒየን ሺፑን ክለብ በርንሌይ በሜዳቸው 2ለ0 ረተዋል።

√ ክርስቲያን ኤሪክሰን እና ማርከስ ራሽፎርድ የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።

√ ማርከስ ራሽፍርድ በአራት ተከታታይ የኦልድ ትራፎርድ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

√ ክርስቲያን ኤሪክሰን በዘንድሮው ዓመት በሁሉም የውድድር መድረኮች ባደረጋቸው ጨዋታዎች #በሰባት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን አድርጓል።

√ ማርከስ ራሽፎርድ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ባደረጋቸው ሀያ ጨዋታዎች #ዘጠነኛ ጎሉን አስቆጥሯል።

√ በምሽቱ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች #ኖቲንግሀም_ፎረስት እና #ቻርልተን ተጋጣሚያቸውን በመርታት ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል።

ቀጣዪን ዙር እነማን ተቀላቅለዋል ?

√ ማንችስተር ዩናይትድ

√ ሌስተር ሲቲ

√ ኒውካስትል ዩናይትድ

√ ሳውዝሀምፕተን

√ ቻርልተን

√ ዎልቭስ እና

√ ኖቲንግሀም ቀጣዩን ዙር መቀላቀላቸውን ያረጋገጡ የሊጉ ክለቦች ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የየርገን ክሎፕ የሊቨርፑል ቆይታ ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ክለቡ እያሳየ በሚገኘው ደካማ አቋም ምክንያት ከሀላፊነታቸው የሚነሱበት እድል #እንደሌለ ተነግሯል።

የሊቨርፑል አመራሮች ጀርመናዊውን አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በቀያዮቹ ቤት ማቆየት ቅድሚያ የሚሰጡት ስራ እንደሆነ እና በአሰልጣኙ መሪነት የወደፊት እቅድም እንዳላቸው ተገልጿል።

ሊቨርፑል በዘንድሮው የውድድር አመት ስድስት ጨዋታዎች የተሸነፉ ሲሆን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ ስምንት ነጥብ ሰብስበው #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ነጥብ ተጋርቷል !

በጣልያን ሴሪያ አስራ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጁቬንቱስ ከ አታላንታ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል።

የጁቬንቱስን ግብ አንግል ዲማሪያ ፣ ሚሊክ እና ዳኒሎ ሲያስቆጥሩ ለአታላንታ ግቦችን ሚህል እና ሉክማን 2x ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ለስምንት የሊግ ጨዋታዎች ያህል ግብ ሳይቆጠርባቸው መውጣት የቻሉት ጁቬንቱሶቾ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች #ስምንት ግቦች አስተናግደዋል።

ጁቬንቱስ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ በሀያ ሶስት ነጥብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አታላንታ በሰላሳ አምስት ነጥብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ጁቬንቱስ ከ ሞንዛ እንዲሁም አታላንታ ከ ሳምፕዶርያ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ነጥብ ተጋርቷል !

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ከ ፉልሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል።

ቼልሲ በሁሉም ውድድሮች ካደረጋቸው ካለፉት ሰባት ጨዋታዎች ውስጥ ማሸነፍ የቻለው #አንዱን ብቻ ነው።

ፉልሀም ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ በሊጉ አንድ ነጥብ ማስመዝገብ ችለዋል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ከመሪው አርሰናል በሀያ ነጥቦች ርቀው ሰላሳ ነጥቦችን በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ፉልሀም በበኩላቸው ሰላሳ ሁለት ነጥቦች በመሰብሰብ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ #ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቼልሲ ከ ዌስትሀም እንዲሁም ፉልሀም ከ ኖቲንግሀም ፎረስት የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe