TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.6K photos
1.48K videos
5 files
3.4K links
加入频道
#ኢትዮጵያ 🇪🇹

የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ በአሁን ሰዓት በመካሄድ ላይ ሲገኝ የሸገር ደርቢ ለመታደም የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ተገኝተዋል።

ከንቲባዋ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ለሁለቱም የመዲናዋ ክለቦች በድምሩ ሀያ ሚሊዮን ብር መስጠታቸውን ገልፀዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ ቡና 1 - 0 ቅዱስ ጊዮርጊስ
እረፍት | ኢትዮጵያ ቡና 1 - 0 ቅዱስ ጊዮርጊስ

አብድልከሪም ወርቁ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
49 ' ኢትዮጵያ ቡና 1 - 1 ቅዱስ ጊዮርጊስ

አብድልከሪም ወርቁ ሀብቶም

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ኢትዮጵያ ቡና 1 - 1 ቅዱስ ጊዮርጊስ

አብድልከሪም ወርቁ ሀብቶም

√ ጨዋታው ወደ መለያያ ምት አምርቷል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቅዱስ ጊዪርጊስ በመለያያ ምት ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ከፒኤስጂ ይልቅ በብሔራዊ ቡድን ነፃነት ይሰማኛል "

ፈረንሳዊው የፒኤስጂ የፊት መስመር ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ ለሀገሩ ሲጫወት #የተሻለ ነፃነት እንደሚሰማው ከጋዜጠኞች ጋር ባደረገው ቆይታ ተናግሯል።

እንደ ኪሊያን ምባፔ ገለፃ " በፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ብዙ ነፃነት አለኝ ፣ ኳሶችን እጠይቃለሁ በተለያዩ የሜዳ ክፍሎች ላይ መንቀሳቀስ እችላለሁ ፣ በፒኤስጂ ግን ይህን አላደርግም " ሲል ምባፔ ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለጤና ቡድንዎ የአንድነት መንፈስ አንድ አይነት ማልያ ለብሰው ውጤትዎን ያሳምሩ !

ከዋናው የስፖርት አልባሳት ስምዎ ያረፈበትን እና የታተመበትን ማልያ በ 500 ብር ብዛት ከሀያ ጀምሮ እናቀርብልዎታለን ።

ዋናው ወደ ፊት . . . . .

📞 ይደውሉ :- 📱0910 851 535   
                      📱0901138283

ቻናላችን :- https://yangx.top/wanawsportwear

📌 አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት
አርጀንቲና ለአዲስ ሪከርድ ተቃርባለች !

ሌሊት በተደረገ የወዳጅነት ጨዋታ ሆንዱራስን በሊዮኔል ሜሲ ሁለት ጎሎች እና ላውታሮ አንድ ግብ 3ለ0 የረቱት አርጀንቲናዊያን አዲስ ሪከርድ ለማስመዝገብ ተቃርበዋል።

ሰላሳ አራት ጨዋታዎችን ያልተሸነፉት አርጀንቲናዎች በቀጣይ አራት ጨዋታዎች #የማይሸነፉ ከሆነ የጣልያንን ሪከርድ ይሰብራሉ።

አርጀንቲና ቀጣይ ተጋጣሚዎቿ ማናቸው ?

1. ጃማይካ :- የወዳጅነት ጨዋታ

2. ሳውዲ አረቢያ :- የአለም ዋንጫ

3. ሜክሲኮ :- የአለም ዋንጫ

4. ፖላንድ :- የአለም ዋንጫ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Tennis እውቁ ስዊዘርላንዳዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ሮጀር ፌዴሬር በቀጣይ ሳምንት ከሚያደርገው የላቨር ካፕ ውድድር በኋላ ራሱን ከውድድር እንደሚያገል አሳውቋል። የ 41ዓመቱ ሮጀር ፌዴሬር እያጋጠሙት ያሉት ጉዳቶች እና በርከት ያሉ ቀዶ ጥገናዎችን ማድረጉ ከውድድሩ ራሱን እንዲያገል ምክንያት መሆናቸው ተገልጿል። የሀያ ጊዜው የግራንድ ስላም አሸናፊው ሮጀር ፌዴሬር ከአንድ ዓመት በላይ በጉዳት ከውድድር…
#Tennis🥎

ስዊዘርላንዳዊው ታሪክ አይሽሬ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ሮጀር ፌደረር ዛሬ ሌሊት የመጨረሻው ጨዋታውን በላቨር ካፕ ካደረገ በኋላ ራሱን ከውድድር አለም ማግለሉን አሳውቋል።

በውድድሩ ላይ በርካታ ታዳሚያን በመገኘት ተወዳጁን ተጫዋች በእምባ ታጅበው ሲሸኙ " ደስተኛ ነኝ አልተከፋሁም " በማለት ለወዳጁቹ ሮጀር ፌዴረር መልዕክቱን አስተላልፏል።

ሮጀር ፌዴረር ምን አይነት ክብሮችን ተጎናፅፏል ?

🙌 369 ጨዋታዎችን አሸንፏል

🏆 103 የኤቲፒ የነጠላ ውደድር ባለድል

🏆 20 ጊዜ የግራንድ ስላም ሻምፒዮን

🏅 2 ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ባለሜዳሊያ

🏅በ 36ዓመቱ የአለም ቁጥር አንድ በመሆን በእድሜ አንጋፋ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች

🏅237 ተከታታይ ሳምንት የአለም ቁጥር አንድ ካስመዘገባቸው #ጥቂት ስኬቶች መካከል ናቸው።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ባርሴሎና ተጫዋቾቹ ተጎድተዋል ! በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ሀገራቸውን የወከሉት የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ሁለት ተጫዋቾች ጉዳት እንዳጋጠማቸው ተገልጿል። የመሐል ተከላካዩ ጁሌስ ኩንዴ ሀገሩ ፈረንሳይ 2ለ0 ኦስትርያን ባሸነፉበት ጨዋታ በሀያ ሶስተኛው ደቂቃ ተቀይሮ ሲወጣ ጉዳቱ #ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚያርቀው ተጠቁሟል። ሌላኛው የቡድኑ ተጫዋች የፊት መስመር አጥቂ ሜምፊስ ዴፓይ ጉዳት ያጋጠመው ተጫዋች ሲሆን…
ባርሴሎና ተጫዋቹን ለሳምንታት ሊያጣ ነው !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ፈረንሳዊው የመሐል ተከላካይ ጁሌስ ኩንዴ ከቀናት በፊት ባጋጠመው ጉዳት ለአራት ሳምንት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል የክለቡ ቅርብ የመረጃ ምንጮች ዘግበዋል።

ጄሌስ ኩንዴ ለአንድ ወር ከሜዳ መራቁን ተከትሎ ጥቅምት 6/2015ዓ.ም የሚካሄደው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ ሊያመልጠው እንደሚችል ተጠቁሟል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#ኢትዮጵያ 🇪🇹

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ፣ በወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ፣ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መካከል በሰኔ 1 ቀን በከተማዋ እንደ ስፖርት ያሉ ቱሪስቶች የመሳብ አቅም ያላቸውን እንቅስቃሴዎች በጋራ በማበልፅግ የስፖርት ቱሪዝምን እንዲስፋፋ ለመስራት የሶስትዮሽ ስምምነት እንደተደረገ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ክብርት ዶክተር ሂሩት ካሳው ፣ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በተገኙበት ስምምነቱ ተካሂዶ ነበር።

ይህንንም መነሻ በማድረግ ላለፋት ሶስት ወራት ተቋርጦ የነበረው የእንጦጦ ፖርክ ሩጫ ከመስከረም ወር ጀምሮ እንደሚጀመር ይፋ ሆኗል።

ለዚህም ወርሀዊ ውድድር ምዝገባ የፊታችን ሰኞ ጠዋት 12 ሰአት ጀምሮ በኦንላይን ተወዳዳሪዎች መመዝገብ የሚችሉ ይሆናል።

መመዝገቢያ :- www.entotoparkrun.com

@tikvahethsport @kidusyoftahe