TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.8K photos
1.48K videos
5 files
3.42K links
加入频道
Forwarded from WANAW SPORT (Wanaw Sportswear)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የዩናይትድ ደጋፊዎች ተቃውሞ ሊያሰሙ ነው !

የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ከእሁዱ የአርሰናል ጨዋታ ከፍተኛ ተቃውሞ ለማሰማት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ደጋፊዎቹ የሚያቀርቡት ተቃውሞ የክለቡ ከፍተኛ ድርሻ ባለቤት የግሌዘር ቤተሰቦችን በመቃወም መሆኑ ተገልጿል።

ተቃውሞውን ያዘጋጁት የደጋፊዎች ቡድን በጨዋታው ዕለት ደጋፊዎች ክለቡ ከሚታወቅበት ቀይ ቀለም ይልቅ ጥቁር ለብሰው እንዲመጡ መጠየቃቸው ተነግሯል።

የደጋፊዎች ቡድን አስተባባሪዎች በሰጡት አስተያየትም “ ክለቡ 1958 ካጋጠመው አሳዛኝ የሙኒክ አውሮፕላን አደጋ በኋላ አስከፊ ሁኔታ ላይ ነው ብለዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ እሁድ ምሽት 1:30 ሰዓት በኦልድትራፎርድ ተጠባቂ የሊግ መርሐ ግብሩን ያደርጋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ሊጉን ለማሸነፍ ቆርጫለሁ “ ሳላህ

የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ ከሊቨርፑል ጋር ፕርሚየር ሊጉን ለማሸነፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

“ ከሊቨርፑል ጋር ሊጉን ለማሸነፍ ቆርጬ ተነስቻለሁ የማይረሳ ይሆናል ድሉን ከደጋፊው ጋር ማክበር እፈልጋለሁ " ሲል መሐመድ ሳላህ ተናግሯል።

ከዚህ በፊት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ቅድሚያ የሚሰጠው እንደነበር የገለፀው ሳላህ አሁን ግን ትኩረቴ ፕርሚየር ሊግ ማሸነፍ ነው ብሏል።

“ በመጀመሪያ ጨዋታዬ የገጠመኝ ከባድ ትግል እዚህ በዚህ ሁኔታ እንዴት መቀጠል እችላለሁ የአካል ብቃቴን ለማሳደግ ጂም መሄድ አለብኝ ብዬ እንዳስብ ያደረገኝ ነበር።" ሳላህ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ቡናማዎቹ ተከታታይ ድላቸውን አሳኩ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የቡናማዎቹን የማሸነፊያ ግብ ኮንኮኒ ሀፊዝ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኢትዮጵያ ቡና ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን በማሳካት ደረጃውን ወደ ሁለት ከፍተኛ ማድረግ ችሏል።

ቡናማዎቹ ያለፉትን ሶስት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፉም።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ ኢትዮጵያ ቡና - 32 ነጥብ
1️⃣0️⃣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ - 25 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

እሁድ - ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

እሁድ - ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ስሑል ሽረ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ እና አርሰናልን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል ጋር የሚያደርጉትን ተጠባቂ የፕርሚየር ሊግ መርሐግብር የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

ኦልድትራፎርድ ስታዲየም ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ አንቶኒ ቴለር በመሐል ዳኝነት እንዲመሩት መመረጣቸው ይፋ ሆኗል።

ጨዋታው እሁድ ከምሽቱ 1:30 በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቅጣት ተጣለባቸው ! የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከመርሲሳይድ ደርቢ በኋላ ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ ምክንያት ቅጣት ተጥሎባቸዋል። አሰልጣኙ ከደርቢው በኋላ ቀይ ካርድ የተመለከቱ ሲሆን ከእንግሊዝ ኤፍኤ የቀረበባቸውን ክስ አምነው መቀበላቸው ይታወሳል። አሁን ላይ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት እንደተጣለባቸው ይፋ ተደርጓል። አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በቀጣይ…
“ ሊጉን ካላሸንፍን ተጠያቂ ነህ “ አርኔ ስሎት

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከመርሲሳይድ ደርቢ በኋላ የጨዋታውን ዳኛ ማይክል ኦሊቨር የተናገሯቸው ንግግር ይፋ ሆኗል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከደርቢው በኋላ አላስፈላጊ ንግግር አድርገዋል በሚል በኤፍኤው ሁለት ጨዋታዎች መቀጣታቸው ይታወቃል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ምን ብለው ነበር ?

አርኔ ስሎት ከጨዋታው በኋላ “ በጨዋታ አመራርህ እንደምትኮራ ተስፋ አደርጋለሁ “ በማለት ዳኛውን እንደተናገሯቸው ተዘግቧል።

አሰልጣኙ አክለውም “ ሊጉን የማናሸንፍ ከሆነ አንተን ነው ተወቃሽ የማደርገው " ሲሉ ማይክል ኦሊቨርን መናገራቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንሄል ዲማርያ ጉዳት አጋጥሞታል !

አርጀንቲናዊው የቤኔፊካ የፊት መስመር ተጨዋች አንሄል ዲማርያ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ አንሄል ዲማርያ ከነገው የባርሴሎና የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተነግሯል።

ቤኔፊካ ነገ ምሽት 5:00 ሰዓት ከባርሴሎና ጋር በሜዳው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪንሰስ ጁኒየር ስንት ክፍያ ጠየቀ ?

የብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ኮንትራት ለማራዘም ንግግር የጀመሩት ሎስ ብላንኮዎቹ እስካሁን ከስምምነት አልደረሱም።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ሪያል ማድሪድ የሰላሳ ሶስት ፐርሰንት የደሞዝ ጭማሬ እንዲያደርግለት መጠየቁ ተገልጿል።

ቪንሰስ ጁኒየር የጠየቀው ክፍያ ከኪሊያን ምባፔ በ አራት ሚልዮን ዩሮ የሚበልጥ መሆኑ ተነግሯል።

በካርሎ አንቾሎቲ ስር የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች መሆን የቻለው ቪንሰስ ጁኒየር የፊፋ የአመቱ ምርጥ ሽልማት ካሸነፈ በኋላ ክፍያው ወደ 15 ሚልዮን ዩሮ ማደጉ ይታወቃል።

ሪያል ማድሪድ ጥያቄውን የሚቀበል ከሆነ ቪንሰስ ጁኒየር በአመት 20 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ በማግኘት የክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋች ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐግብር ሲዳማ ቡና ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሲዳማ ቡናን ግብ መስፍን ታፈሰ ሲያስቆጥር ለሀድያ ሆሳዕና የአቻነቷን ግብ ኢዮብ አለማየሁ ከመረብ አሳርፏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

3️⃣ ሀድያ ሆሳዕና - 32 ነጥብ
1️⃣1️⃣ሲዳማ ቡና - 25 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

ሰኞ - ሀድያ ሆሳዕና ከ ባህርዳር ከተማ

ሰኞ - ሲዳማ ቡና ከ አዳማ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ግብ ጠባቂው ቅጣት ተጣለበት !

ፈረንሳዊው የኤሲ ሚላን ግብ ጠባቂ ማይክ ማይግናን የአንድ ጨዋታ እገዳ እና 15,000 ዩሮ ገንዘብ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ማይክ ማይግናን ቅጣቱ የተጣለበት ከላዚዮ ጨዋታ ሽንፈት በኋላ የጨዋታውን ዳኛ አክብሮት በጎደለው መልኩ አይቷል በሚል መሆኑ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ማይክ ማይግናን ኤሲ ሚላን ከሊቼ ጋር የሚያደርገው የሊግ መርሐግብር የሚያመልጠው ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የካራባኦ ካፕ ፍፃሜን ማን ይመራዋል ?

በሊቨርፑል እና ኒውካስል ዩናይትድ መካከል የሚደረገውን የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

በግዙፉ ዌምብሌይ ስታዲየም የሚካሄደውን ተጠባቂ የፍፃሜ ጨዋታ ጆን ብሩክስ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት በይፋ ተገልጿል።

ጨዋታው እሁድ መጋቢት 7/2017 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ዩሮፓ ሊግ ማሸነፍ ለእኛ አስፈላጊው ነገር አይደለም “ አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አሁን ላይ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ ለቡድናቸው በጣም አስፈላጊው ነገር አለመሆኑን ገልጸዋል።

“ ሰዎች ዩሮፓ ሊግ ማሸነፍ እና ሻምፒየንስ ሊግ መግባትን እንደ እድል ይመለከቱታል ነገርግን እኔ የበለጠ ልናስብበት የሚገባን ብዙ አስፈላጊ ነገር አለ ብዬ አስባለሁ “ ሲሉ ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም “ ነገሩ ትንሽ እንግዳ ሊመስል ይችላል ነገርግን እኛ በአሁኑ ሰዓት ዋንጫ ከማሸነፍ የበለጠ አስፈላጊ ነገር እየገነባን ነው “ ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
ማይክል ኦሊቨር ለዳኝነት ሳይመረጡ ቀሩ !

እንግሊዛዊው ዳኛ ማይክል ኦሊቨር በሳምንቱ መጨረሻ ለሚደረጉ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዳኝነት ሳይመረጡ መቅረታቸው ተገልጿል።

ማይክል ኦሊቨር ለዳኝነት ያልተመረጡት ከቀናት በፊት የሚልዋል ግብ ጠባቂ ፊሊፕ ማቴታ ላይ ለሰራው ከባድ ጥፋት ቀድመው ቀይ ሳይሰጡ በማለፋቸው መሆኑ ተገልጿል።

የክሪስታል ፓላሱ ተጨዋች ፊሊፕ ማቴታ በተሰራበት ከባድ ጥፋት ምክንያት ሀያ አምስት ጊዜ ለመሰፋት መገደዱ ተነግሯል።

ዋና ዳኛው በሳምንቱ መጨረሻ ለሚደረጉ ጨዋታዎች ለመሐል ዳኝነትም ሆነ የአራተኛ እና ቫር ዳኝነት አለመመረጣቸው ተዘግቧል።

የ 40ዓመቱ ዳኛ ማይክል ኦሊቨር ነገ ምሽት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባየር ሙኒክ ከባየር ሌቨርኩሰን የሚያደርጉትን ጨዋታ ይመራሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

5:00 ሪያል ማድሪድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

5:00 ዶርትመንድ ከ ሊል

5:00 ፒኤስቪ ከ አርሰናል

5:00 ሪያል ማድሪድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ክለብ ብሩጅ 1-3 አስቶን ቪላ

      ዴ ኩይፐር       ባይሌይ
                        ሜቼሌ ( በራስ ላይ )
                                 አሴንሲዮ

- ማርኮ አሴንሲዮ በአስቶን ቪላ ቤት ባደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

- የመልስ ጨዋታው በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ቪላ ፓርክ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe