TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
ፈረሰኞቹ ሽንፈት አስተናግደዋል !

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የመቻልን የማሸነፊያ ግብ የቀድሞ የፈረሰኞቹ ተጨዋች ከነዓን ማርክነህ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፈረሰኞቹ በውድድር አመቱ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

መቻል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰላሳ ሶስት በማድረስ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሽንፈት ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሀምሳ አንድ ነጥብ ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል።

የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ከተከታዩ ባህርዳር ከተማ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ #አራት ጠቧል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም መቻል ከ ሲዳማ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ድል አድርጓል !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ከ ሻልክ 04 ጋር ያደረጉትን የሊግ መርሐ ግብር 6ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነታቸውን አጠናክረዋል።

የባየር ሙኒክን የማሸነፊያ ግቦች ቶማስ ሙለር ፣ ኪሚች ፣ ናብሪ 2x ፣ ቴል እና ናዝራዊ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ባየር ሙኒክ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ ስምንት በማድረስ አንድ ጨዋታ ከሚቀረው ተከታዩ ዶርትመንድ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #አራት ከፍ ማድረግ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ከሌፕዚግ የሚገናኝ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪንሰስ ጁኒየር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥኑት ሪያል ማድሪዶች የወርሀ ግንቦት የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር የሪያል ማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመባል በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ለተከታታይ #አራት ወራት እንዲሁም በውድድር አመቱ ለ #አምስተኛ ጊዜ የሪያል ማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ክብርን መቀዳጀት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ በኮከብነቱ ቀጥሏል !

አርጀንቲናዊው የኢንተር ሚያሚ የፊት መስመር ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ ቡድኑን ከሽንፈት ሲታደግ ሁለት ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የሊዮኔል ሜሲ የኢንተር ሚያሚ ቁጥሮች ምን ይመስላሉ ?

- ኢንተር ሚያሚ ሊዮኔል ሜሲ በተሰለፈባቸው #አራት ጨዋታዎች አልተሸነፉም።

- ሊዮኔል ሜሲ በኢንተር ሚያሚ ቤት በድምሩ በስምንት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን ማድረግ ችሏል።

- ሜሲ ሰባተኛ የኢንተር ሚያሚ ጎሉን ዛሬ ሌሊት ከመረብ ማሳረፍ ይችላል።

- ሊዮኔል ሜሲ ተሰልፎ በተጫወተባቸው አራት ጨዋታዎች #በሙሉ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጧል።

የክለቡ የዓመቱ ከፍተኛ ግብ አግቢ ማነው ?

1. ሊዮኔል ሜሲ :- ሰባት ጎል ( በአራት ጨዋታ )

2. ጆሴፍ ማርቲኔዝ :- ሰባት ጎል ( ሀያ ስምንት ጨዋታ )

3. ሮበርት ታይለር :- አምስት ጎል ( ሀያ ሰባት ጨዋታ )

4. ሊዮናርዶ ካምፓና :- አራት ጎል ( ሀያ ሁለት ጨዋታ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ በስንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች?

በሀንጋሪ ቡዳፔሽት እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአንድ ወርቅ ፣  አንድ ብር እና ሁለት ነሐስ ሜዳሊያዎች በድምሩ #አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት #በሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በደረጃ ሰንጠረዡ፦

🇺🇸 አሜሪካ 🥇🥇🥇 🥈🥈 🥉

🇪🇸 ስፔን 🥇🥇

🇪🇹  ኢትዮጵያ 🥇 🥈 🥉🥉

በማግኘት የደረጃ ሰንጠረዡን ይመራሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሳውዲ ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

አራተኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የሳውዲ አረቢያ ሊግ የወርሀ ነሀሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አራት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት ክርስቲያኖ ሮናልዶ ( አል ናስር ) ፣ ሪያድ ማህሬዝ ( አል አህሊ ) ፣ ማልኮም ( አል ሂላል ) እና ኢጎር ኮሮናዶ ( አል ኢትሀድ ) በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸዉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሆልዲንግ ክሪስትያል ፓላስን ሊቀላቀል ነው !

ክሪስትያል ፓላስ እንግሊዛውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሮብ ሆልዲንግን ከሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አርሰናል ከሮብ ሆልዲንግ ዝውውር #አራት ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ክፍያ እንደሚቀበሉ ሲገለፅ ተጨዋቹ በአሁኑ ሰዓት የህክምና ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአርሰናል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አራት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

እጩዎች እነማን ናቸው ?

👉 ቤን ዋይት

👉 ኢዲ ኒኪታህ

👉 ዊልያም ሳሊባ

👉 ዴክላን ራይስ

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአርሰናል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አራት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

እጩዎች እነማን ናቸው ?

👉 ቡካዩ ሳካ

👉 ዴክላን ራይስ

👉 ማርቲን ኦዴጋርድ

👉 ዊልያም ሳሊባ

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኖቲንግሀም ነጥብ ሊቀነስበት ይችላል ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ኖቲንግሀም ፎረስት ወደ ሊጉ ካደገ ወዲህ የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግን ሳይጥስ እንዳልቀረ ተገልጿል። በዚህ ወር መጨረሻ በሚደረግ ማጣራት ኖቲንግሀም ፎረስት የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግን ጥሷል ተብሎ ከታመነ የነጥብ ቅነሳ እንደሚጠብቀው ተገልጿል። ኖቲንግሀም ፎረስት ባለፈው የውድድር ዘመን ወደ ፕርሚየር ሊጉ ካደገ ወዲህ አርባ ሁለት…
ኖቲንግሀም ፎረስት ነጥብ ተቀነሰበት !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ኖቲንግሀም ፎረስት የፕርሚየር ሊጉን ፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ መጣሳቸውን ተከትሎ #አራት ነጥቦች እንደተቀነሱባቸው ተገልጿል።

የአራት ነጥብ ቅነሳውን ተከትሎ ኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ወራጅ ቀጠናው በመውረድ በሀያ አንድ ነጥቦች አስራ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።

ኖቲንግሀም ፎረስት በዘንድሮው የውድድር አመት ከኤቨርተን በመቀጠል ነጥብ የተቀነሰበት ሁለተኛው የፕርሚየር ሊግ ክለብ ሆነዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኖቲንግሀም ፎረስት ነጥብ ተቀነሰበት ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ኖቲንግሀም ፎረስት የፕርሚየር ሊጉን ፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ መጣሳቸውን ተከትሎ #አራት ነጥቦች እንደተቀነሱባቸው ተገልጿል። የአራት ነጥብ ቅነሳውን ተከትሎ ኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ወራጅ ቀጠናው በመውረድ በሀያ አንድ ነጥቦች አስራ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል። ኖቲንግሀም ፎረስት በዘንድሮው የውድድር አመት ከኤቨርተን…
ኖቲንግሀም ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት አላገኘም !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ኖቲንግሀም ፎረስት የፕርሚየር ሊጉን ፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጥሰዋል በሚል በቅርቡ #አራት ነጥቦች እንደተቀነሱባቸው ይታወቃል።

ኖቲንግሀም ፎረስት ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ መጠየቃቸው ቢገለፅም ተቀባይነት ሳያገኙ ቀሬተው ቅጣቱ መፅናቱ ታውቋል።

የአራት ነጥብ ቅነሳው የፀናባቸው ኖቲንግሃም ፎረስቶች አሁን ላይ ከወራጅ ቀጠናው በሶስት ነጥብ ርቀው በሀያ ዘጠኝ ነጥቦች አስራ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄራርድ ፒኬ ምርመራ እንደተከፈተበት ተገለጸ !

የቀድሞ የስፔን ብሔራዊ ቡድን እና ባርሴሎና የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጄራርድ ፒኬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ ተገልጿል።

ጄራርድ ፒኬ ምርመራው የተከፈተበት ሉዊስ ሩብያሌስ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ወደ ሳውዲ አረቢያ ማምራት ጋር በተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።

የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ሳውዲ አረቢያ ላይ እንዲደረግ የአምስት አመት ውል ሲፈፀም የጄራርድ ፒኬ ተቋም የኮሚሽን ክፍያ ማግኘቱ ተገልጿል።

እስከ 2025 በሚዘልቀው ስምምነቱ የጄራርድ ፒኬ ተቋም እንደ ኮሚሽን በአመት #አራት ሚልዮን ዩሮ እንደሚቀበል ሲገለፅ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን #አርባ ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኝ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናይጄሪያ ሽንፈት አስተናግዳለች !

በአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ከቤኒን አቻው ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ዘ ሱፐር ኤግል በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያው ያደረጋቸውን #አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ ሶስት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት አጠናቆ በአንዱ ተሸንፎ በሶስት ነጥቦች እና አንድ የግብ እዳ የምድቡ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀድሞ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጌርኖት ሮር የሚመራው የቤኒን ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቦቹን ሰባት በማድረስ ምድቡን በበላይነት መምራት ጀምሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በዛሬው ዕለት ጅማሮውን ባደረገው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በመጀመሪያው ቀን ውሎ አስራ ሶስት የወርቅ ሜዳልያዎች ለውድድር አሸናፊዎች እንደሚበረከቱ ተገልጿል።

የሀገሪቱ የፈጣን ባቡር መስመር ትላንት ጥቃት የተፈፀመበት መሆኑን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ
አትሌቶች በጀልባ ለመጓጓዝ መገደዳቸው ተነግሯል።

ቻይና የመጀመሪያውን የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሀገር መሆን ችላለች።

በዛሬው ዕለት በዋና #አራት ፣ በብስክሌት ፣ ፌንሲንግ ፣ ጁዶ ለእያንዳንዳቸው #ሁለት እንዲሁም በዳይቪንግ ፣ ራግቢ እና ሹቲንግ ለእያንዳንዳቸው #አንድ የወርቅ ሜዳልያ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የመድፈኞቹ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አራት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ቡካዮ ሳካ ፣ ዴቪድ ራያ ፣ ካይ ሀቨርትዝ እና ዊሊያም ሳሊባ የአርሰናል የአመቱ የመጀመሪያ ወር ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል

የ 2024/25 የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ #አራት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ፣ ፔፕ ጋርዲዮላ ፣ ፋብያን ሁርዜለር እና አርኔ ስሎት የሊጉ የመጀመሪያ ወር ምርጥ አሰልጣኝ እጩ በመሆን የቀረቡ አሰልጣኞች ናቸዉ።

የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶተንሀም ድል አድርጓል !

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስረኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሀም ከአስቶን ቪላ ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የቶተንሀምን የድል ግቦች ዶሚንክ ሶላንኬ (2x) ፣ ጄምስ ማዲሰን እና ብሬናን ጆንሰን ሲያስቆጥሩ ለአስቶን ቪላ ሞርጋን ሮጀርስ አስቆጥሯል።

ዶሚንክ ሶላንኬ በውድድር አመቱ በሊጉ ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛቶች #አራት ማድረስ ችሏል።

አስቶን ቪላ #ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ በሊጉ ያለመሸነፍ ግስጋሴያቸው ተገቷል።

የደረጃ ሰንጠረዡ ?

5⃣ አስቶን ቪላ - 18 ነጥብ

7⃣ ቶተንሀም - 16 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ?

ቅዳሜ - ሊቨርፑል ከ አስቶን ቪላ

እሁድ - ቶተንሀም ከ ኢፕስዊች ታውን

@Tikvahethsport   @kidusyoftahe
የመድፈኞቹ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አራት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

ቡካዩ ሳካ

ማርቲኔሊ

ቶማስ ፓርቴ እና

ካይ ሀቨርትዝ የጥቅምት ወር የአርሰናል ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethpl🇪🇹

በሰባተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከስሑል ሽረ ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ ውጤት አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የስሁል ሽረን ግብ ፋሲል አስማማው ሲያስቆጥር አንተነህ ተፈራ የቡናማዎችን የአቻነት ግብ ከመረብ አሳርፏል።

አንተነህ ተፈራ በውድድር አመቱ በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች #አራት ማድረስ ችሏል።

የደረጃ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1⃣1⃣ ኢትዮጵያ ቡና - 8 ነጥብ
1⃣5⃣ ስሑል ሽረ - 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ?

- ሀድያ ሆሳዕና ከ ኢትዮጵያ ቡና

- ስሑል ሽረ ከ ባህርዳር ከተማ

@Tikvahethsport   @kidusyoftahe