ድሬዳዋ ከተማ አሸንፏል !
በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የድሬዳዋን የማሸነፊያ ግቦች እያሱ ለገሰ እና ሱራፌል ጌታቸው ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለወልቂጤ ከተማ ጌታነህ ከበደ አስቆጥሯል።
የወልቂጤ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ጌታነህ ከበደ በውድድር አመቱ አስራ ስድስተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልቂጤ ከተማ በሀያ ዘጠኝ ነጥብ አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ይገናኛሉ።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

" ሮናልዶን እንዲጠቀሙበት ነግሬያቸዋለሁ "
የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሙስሊ አል ሙማር የክለቡ ተጨዋቾች ክርስቲያኖ ሮናልዶን ተጠቅመው ራሳቸውን እንዲያሳዩ እንደነገሯቸው ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸውም " ሁልጊዜም ለአል ናስር ተጨዋቾች የምነግራቸው ከጎናቸው ያለውን ምርጡን ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶን እንዲጠቀሙበት እና ራሳቸውን እንዲያሳዩ ነው።
ምክንያቱም ከሀምሳ በላይ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ለጨዋታዎቹ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ይሰጣሉ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

ዋልያዎቹ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ !
በመጪው ክረምት በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሜሪካ የሚጓዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ ቆይታው የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርግ ይፋ ተደርጓል።
ብሔራዊ ቡድኑ ወደ አሜሪካ በሚያደርገው ጉዞ የመጀመርያውን ጨዋታ ከጉያና ብሔራዊ ቡድን ጋር ሐምሌ 1/2015 ዓ.ም በፊላደልፊያ ሱባሩ ፓርክ እንደሚደረግ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

TIKVAH-SPORT
ጁቬንቱስ በድጋሜ ነጥብ ሊቀነስበት ይችላል ! የጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ የአስራ አንድ ነጥቦች ቅነሳ ቅጣት እንዲጣልበት የሀገሪቱ የፌደራል አቃቤ ህግ ይግባኝ መጠየቁ ተገልጿል። የሀገሪቱ የፌደራል አቃቢ ህግ በጁቬንቱስ ላይ የጠየቀውን ይግባኝ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ተጠቁሟል። ጁቬንቱስ አቃቤ ህግ የጠየቀው የአስራ አንድ ነጥቦች ቅነሳ ቅጣት ውሳኔ የሚተላለፍበት ከሆነ አሁን ላይ ከሚገኝበት…
ጁቬንቱስ በድጋሜ ነጥብ ተቀነሰበት !
የጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ የፌደራል አቃቢ ህግ የጠየቀው ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቶ የአስር ነጥቦች ቅነሳ ቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈበት ይፋ ሆኗል።
የፌደራል አቃቢ ህግ ጁቬንቱስ አስራ አንድ ነጥቦች እንዲቀነሱበት የይግባኝ ጥያቄ ቢያቀርብም አስር ነጥብ እንዲቀነስ መወሰኑ ተገልጿል።
ጁቬንቱስ አሁን ላይ ከነበረው ስልሳ ዘጠኝ ነጥቦች ላይ አስር ነጥቦች መቀነሳቸውን ተከትሎ በሀምሳ ዘጠኝ ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።

ጁቬንቱስ ሽንፈት አስተናግዷል !
በጣልያን ሴርያ ሰላሳ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጁቪንቱስ ከ ኢምፖሊ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የኢምፖሊን የማሸነፊያ ግቦች ካፑቶ 2x ፣ ሉፔርቶ እና ፒኮሊ ሲያስቆጥሩ ለጁቬንቱስ ቼሳ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ከጨዋታው ቀደም ብሎ አስር ነጥቦች የተቀነሱበት ጁቬንቱስ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ በሀምሳ ዘጠኝ ነጥቦች ሰባተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ጁቬንቱስ ከ ኤሲ ሚላን ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ኒውካስል ለሻምፒየንስ ሊግ ማለፉን አረጋግጧል !
ኒውካስል ዩናይትድ ከሌስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን የሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት በማጠናቀቅ ለሻምፒየንስ ሊግ ማለፉን አረጋግጧል።
በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ #ሰባ ነጥቦችን መሰብሰብ የቻለው ኒውካስል ዩናይትድ ከሀያ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ማለፋቸውን ማረጋገጥ ችለዋል።
ሌስተር ሲቲ በበኩላቸው በሰለሳ አንድ ነጥቦች በወራጅ ቀጠናው አስራ ስምንተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ታችኛው ሊግ ለመውረድ ተቃርበዋል።

" ለሻምፒየንስ ሊግ ማለፍ ይገባናል "
የኒውካስል ዩናይትዱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኬራን ትሪፕዬር ቡድናቸው ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ማለፍ እንደሚገባው ተናግሯል።
ኬራን ትሪፕየር በንግግሩም " ቡድናችን በዘንድሮው የውድድር አመት ካደረገው ነገር አንፃር ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ማለፍ ይገባዋል።"ሲል ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።
እንግሊዛዊው ተጨዋች ኬራን ትሪፕዬር ከጨዋታው በፊት የኒውካስል ዩናይትድ የ2022/23 የውድድር አመት ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

"ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ!
አሁኑኑ በ betika.et ይወራረዱ!!
የዛሬውን ዕለታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - betika.et/et/daily-jackpot
የዛሬው የተመረጡ ዕለታዊ ጨዋታዎች ላይ ለመወራረድ - betika.et/et/
የሳምንታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - betika.et/et/jackpot"

ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ
በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።
እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።
ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848
#ShemelesBekele18

" ሳሊባን ሰበብ ማድረግ አያስፈልግም "
በስካይ ስፖርት ቴሌቪዥን ጣቢያ በስፖርት ተንታኝነት እያገለገለ የሚገኘው ጋሪ ኔቭል መድፈኞቹ ለሽንፈታቸው ሳሊባን ምክንያት ማድረግ እንደሌለባቸው ተናግሯል።
ኔቭል በሰጠው አስተያየትም " አርሰናል ከ ዌስትሀም እና ሳውዝአምፕተን ጋር ነጥብ ለማጣቱ ዊሊያም ሳሊባን ሰበብ ወይም ምክንያት ማድረግ አያስፈልግም " ሲል ተናግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
በስካይ ስፖርት ቴሌቪዥን ጣቢያ በስፖርት ተንታኝነት እያገለገለ የሚገኘው ጋሪ ኔቭል መድፈኞቹ ለሽንፈታቸው ሳሊባን ምክንያት ማድረግ እንደሌለባቸው ተናግሯል።
ኔቭል በሰጠው አስተያየትም " አርሰናል ከ ዌስትሀም እና ሳውዝአምፕተን ጋር ነጥብ ለማጣቱ ዊሊያም ሳሊባን ሰበብ ወይም ምክንያት ማድረግ አያስፈልግም " ሲል ተናግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሉሲዎቹ ተጋጣሚያቸውን ቀጣይ ሳምንት ያውቃሉ !
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለፓሪሱ የኦሎምፒክ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን ተጋጣሚውን በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ በግብፅ ካይሮ በሚኖረው የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ያውቃል።
በኦሎምፒኩ ላይ አፍሪካን በመወከል ሁለት ሀገራት ብቻ ተሳታፊ የሚሆን ሲሆን የማጣርያው ውድድር አራት ዙሮች ይኖሩታል።
በዚህም መሰረት :-
👉 የመጀመሪያ ዙር :- ሐምሌ 4 - 18/2015 ዓ.ም
👉 ሁለተኛ ዙር :- ጥቅምት 12 - 20/2016 ዓ.ም
👉 ሶስተኛ ዙር :- የካቲት 11 - 20/2016 ዓ.ም
👉 አራተኛ ዙር :- መጋቢት 23 - 30/2016 ዓ.ም ድረስ የማጣርያ ውድድሮቹ እንሚካሄዱ ይፋ ተደርጓል።

ቲክቫህ ስፖርት በፎቶ ሥራዎቹ በተለያዩ ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጥ 10 ውስጥ ተካተተ።
የዓለም አቀፉ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ( AIPS ) በየአመቱ በሚያዘጋጀው የስፖርት ጋዜጠኞች ሽልማት ውድድር በተለያዩ ዘርፎች አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል።
በአህጉር ደረጃ እንደ አፍሪካ በወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ ቲክቫህ ስፖርት (Tikvah Sport Image ) በተለያዩ ዘርፎች ምርጥ አስር ውስጥ በመካተት አጠናቋል።
ቲክቫህ ስፖርት በውድድሩ ምርጥ 10 ውስጥ መግባት የቻለው " Sport Portfolio " እና " Sport Action " በሚሉት ሁለት ዘርፎች ሲሆን ከአፍሪካ ስምንተኛ እና አስረኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።
ለአምስተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ከ1800 በላይ ተወዳዳሪዎች እንዲሁም ከ138 በላይ ሀገራት ተሳታፊ ነበሩ። ከአፍሪካ ደግሞ 39 ከሚሆኑ ሀገራት 320 ተሳታፊዎች ሥራዎቻቸውን የላኩ ሲሆን ከኢትዮጵያ 5 ተሳታፊዎች በውድድሩ ተካተዋል።

የስፔን ፖሊስ አራት ግለሰቦች አስሯል !
የስፔን ብሔራዊ ፖሊስ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ማድሪድ ከዘረኝነት ጥቃት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ይፋ አድርጓል።
በዘረኝነት ጥቃት ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት አራት ግለሰቦች አንዲት አሻንጉሊት የቪንሰስን ማልያ አልብሳችሁ አስቀምጣችዋል በሚል መሆኑን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል።
ግለሰቦቹ የቪንሰስ ጁኒየርን ማልያ የለበሰውን አሻንጉሊት ያስቀመጡት በሪያል ማድሪድ ልምምድ ማዕከል አቅራቢያ በሚገኝ ድልድይ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የማድሪድ እና ቫሌንሽያ ጨዋታ የቫር ዳኛ ታግደዋል !
የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የዳኞች ቴክኒክ ኮሚቴ በጋራ በመሆን የሪያል ማድሪድ እና ቫሌንሽያን ጨዋታ በቫር ጃኝነት የመሩትን ዳኛ ማገዳቸው ተገልጿል።
የቫር ዳኛው እገዳው የተጣለባቸው በዕለቱ በተጨዋቾች መካከል በነበረው አለመግባባት ለቪንሰስ ጁኒየር ብቻ የቀይ ካርድ ውሳኔ እንዲሰጥ በማድረጋቸው መሆኑ ተነግሯል።
በተጨማሪም ሌሎች ተጨማሪ አምስት የቫር ዳኞች በቀጣዩ የውድድር አመት የስፔን ላሊጋ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንዳይሆኑ መታገዳቸው ተገልጿል።

👉 ነገ የሚደርስ ማልያዎን ዛሬ ይዘዙ !
የተዘጋጁ ማሊያዎችን በ 499 ብር ብቻ በእጅዎ ያስገቡ።
WANAW ወደ ፊት . . . . . 👉
📞 ይደውሉ:- 📱0910 851 535
📱0901138283
👇🏽
https://yangx.top/wanawsportwear
የተዘጋጁ ማሊያዎችን በ 499 ብር ብቻ በእጅዎ ያስገቡ።
WANAW ወደ ፊት . . . . . 👉
📞 ይደውሉ:- 📱0910 851 535
📱0901138283
👇🏽
https://yangx.top/wanawsportwear
የርገን ክሎፕ ሚልነርን ማቆየቶ ፈልገው ነበር !
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እንግሊዛዊውን የመስመር ተጨዋች ጄምስ ሚልነር በክለቡ ማቆየት ፈልገው እንደነበር ተገልጿል።
አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ጄምስ ሚልነርን በመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ቤት ለማቆየት የፈለጉት በተጨዋችነት እንዳልሆነ ተነግሯል።
ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ጄምስ ሚልነር በቡድኑ የአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ እንዲቀላቀል ጥያቄ አቅርበውለት እንደነበር ተዘግቧል።