TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.8K photos
1.48K videos
5 files
3.42K links
加入频道
#PremiereLeague

ፖርቹጋላዊው የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዘንድሮው የውድድር አመት በህመም እና ጉዳት ምክንያት አራተኛ ጨዋታው የሚያመልጠው ይሆናል።

ማንችስተር ዩናይትድን ያለ ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ሲሆን በሁለቱ ተሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Premiereleague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

ማንችስተር ዩናይትድ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ የውድድር አመት አስራ አራት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተሸንፏል።

አርሰናል ከአስራ ስምንት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድን በአንድ የውድድር አመት ሁለት የሊግ ጨዋታዎችን አሸንፎታል።

አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ክለብ ሳምንት ከሚደረጉ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ ይታወቃል።

የአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታው ቡድን አርሰናል በዘንድሮው የውድድር አመት በሊግ ምርጥ #ስድስት ክለቦች ጋር ያደረገውን ጨዋታ አልተሸነፈም።

አርሰናል በውድድር አመቱ ሀያ ሰባት ጨዋታዎችን በአሸናፊነት ሲወጣ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ የክለቡ ትልቅ ድል ሆኖ መመዝገብ ችሏል።

ከሊጉ መሪ አርሰናል በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ያለውን ቀሪ አንድ ጨዋታ ማክሰኞ ከቶተንሀም ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

የሊጉን ዋንጫ ማን ያሳካል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጥሩ ያልሆነ ጊዜን ማሳለፉ ቀጥሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአንድ የውድድር አመት በርካታ ግቦች ሲቆጠሩበት ከሀምሳ ሶስት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ቀያይ ሴጣኖቹ በአንድ የውድድር አመት በርካታ ጨዋታዎች ሲሸነፉ ከአርባ ስድስት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድ በፕርሚየር ሊጉ ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች የሚቀሩት ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

ቶተንሀም ከማንችስተር ሲቲ ጋር በሜዳው ያደረጋቸውን ያለፉት አራት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳይቆጠርበት ሁሉንም በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።

ማንችስተር ሲቲ በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስር ከየትኛውም ክለብ በላይ በቶተንሀም ስድስት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ተሸንፏል።

ቶተንሀም ባለፉት ሶስት አመታት ካደረጋቸው የሊጉ የመጨረሻ የሜዳ ጨዋታዎች በሁለቱ ሲሸነፍ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

ማንችስተር ሲቲ በቶተንሀም ስታዲየም ካደረጋቸው ሀያ ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በስድስቱ ብቻ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፊል ፎደን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተባለ ! በነገው ዕለት ፍፃሜውን የሚያገኘው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን የፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ ተመርጧል። ፊል ፎደን በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ለማንችስተር ሲቱ አስራ ሰባት…
#PremiereLeague

ፊል ፎደን ከ2015/16 የውድድር አመት ጄሚ ቫርዲ ካሸነፈ ወዲህ የፕርሚየር ሊግ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት ያሸነፈ የመጀመሪያው እንግሊዛዊ ተጨዋች ሆኗል።

ባለፉት አምስት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የውድድር አመታት የማንችስተር ሲቲ ተጨዋቾች የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን የግላቸው ማድረግ ችለዋል።

ባለፉት አምስት አመታት እነማን አሸነፉ ?

- ኬቨን ዴብሮይን :- 2019/20 የውድድር አመት

- ሩበን ዲያስ :- 2020/21 የውድድር አመት

- ኬቨን ዴብሮይን :- 2021/22 የውድድር አመት

- ኤርሊንግ ሀላንድ :- 2022/23 የውድድር አመት

- ፊል ፎደን :- 2023/24 የውድድር አመት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague

ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ማንችስተር ሲቲን በሀላፊነት እየመሩ ስድስተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በተከታታይ አራተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫቸውን በማሳካትም አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሰባት የውድድር አመት ውስጥ ስድስት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫዎችን አሳክተዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ በሲቲ ቤት ምን አሳኩ ?

6️⃣ ፕርሚየር ሊግ

4️⃣ ካራባኦ ካፕ

2️⃣ ኤፌ ካፕ እና ኮሚኒቲ ሺልድ

1️⃣ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ

1️⃣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ፣ የፊፋ ክለቦች ዋንጫ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የፕርሚየር ሊግ መርሐግብሮች ይፋ ሆኑ ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሚቀጥለው የ2024/25 የውድድር ዘመን የጨዋታ መርሐግብሮች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት በውድድሩ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብሮች :- - ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ - አርሰናል ከ ዎልቭስ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ ፉልሀም ( የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ) - ኢፕስዊች ታውን ከ ሊቨርፑል - ሌስተር ሲቲ ከ ቶተንሀም…
#PremiereLeague

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን መርሐግብሮች ይፋ ሲደረጉ በመጀመሪያ ሳምንት መርሐግብር ቼልሲን ከማንችስተር ሲቲ አገናኝቷል።

ተጠባቂው የማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ጨዋታ በሊጉ ሶስተኛ ሳምንት መርሐግብር ኦልድትራፎርድ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።

ተጠባቂው የሰሜን ለንደን ደርቢ በአርሰናል እና ቶተንሀም መካከል በአራተኛው ሳምንት መርሐግብር ሲደረግ መድፈኞቹ በአምስተኛ ሳምንት ማንችስተር ሲቲን ይገጥማሉ።

የመጀመርያው የማንችስተር ደርቢ ጨዋታ ታህሳስ ወር ውስጥ ኢትሀድ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague

በሶስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር አስቶን ቪላ ፣ ብሬንትፎርድ እና በርንማውዝ ተጋጣሚዎቻቸውን መርታት ችለዋል።

በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ በአማዱ ኦናና እና ዱራን ግቦች ሌስተር ሲቲን 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

ብሬንትፎርድ በምቤሞ 2x እና ዊሳ ግቦች ከሳውዝሀምፕተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ፉልሀም ከኢፕስዊች ታውን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በርንማውዝ ከኤቨርተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ በመጨረሻ ደቂቃዎች ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች 3ለ2 ማሸነፍ ችሏል።

ዎልቭስ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ 0ለ0 ሲለያዩ ቼልሲ ከኖቲንግሀም ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የቼልሲን ግብ ኖኒ ማዱኬ ማስቆጠር ሲችል ለኖቲንግሀም ፎረስት ክሪስ ውድ ከመረብ አሳርፏል።

የሰማያዊዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኪ በውድድር ዘመኑ አራተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ኮል ፓልመር በ 2024 አስራ ሁለት የፕርሚየር ሊግ አሲስቶችን በማድረግ ቀዳሚው የሊጉ ተጨዋች ነው።

ማርክ ኩኩሬላ እና ፎፋና የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ በቅጣት በቀጣይ የሊቨርፑል ጨዋታ የሚያመልጣቸው ይሆናል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

4️⃣ኛ ቼልሲ :- 14 ነጥብ
5️⃣ኛ አስቶን ቪላ :- 14 ነጥብ
1️⃣4️⃣ኛ ማንችስተር ዩናይትድ :- 8 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ?

ቅዳሜ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብሬንትፎርድ

ቅዳሜ ፉልሀም ከ አስቶን ቪላ

እሁድ ሊቨርፑል ከ ቼልሲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

ማንችስተር ዩናይትድ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ታሪክ ከሰባት የሊግ ጨዋታዎች በኋላ አነስተኛ የሚባለውን ውጤት አስመዝግቧል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ከፕርሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሰባት ጨዋታዎች ስምንት ነጥቦችን ብቻ ሲሰበስቡ በታሪክ የመጀመሪያው ነው።

ማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ያስቆጠራቸው የፕርሚየር ሊግ ግቦች አምስት ናቸው።

ከማንችስተር ዩናይትድ በታች በሊጉ አነስተኛ ግቦችን ያስቆጠረው ሳውዝሀምፕተን ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe