#ኤቭራ
ዝነኛው የቀድሞ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንና የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ፓትሪስ ኤቭራ ወደ ኃላ መመለስ ቢችል ለፈረንሳይ ከመጫወት ይልቅ ለትውልድ ሀገሩ ለሴኔጋል መጫወትን እንደሚመርጥ ለRMC በሰጠው ቃል ተናግሯል።
ኤቭራ ፤ ወደ ኃላ መመለስ ብችል ፈረንሳይን ከመወከል ይልቅ የትውልድ ሀገሬን ሴኔጋልን ለመወከል እመርጥ ነበር ብሏል።
አክሎም ፤ " ጥሩ ስትጫወት እና ስታሸንፍ እንደ ፈረንሳዊ ትከበራለህ ፤ ነገር ግን ቡድኑ ሽንፈት ሲገጥመው እንደ ሴኔጋላዊ ተነጥለህ ትወጣለህ " ሲል ለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ሲጫወት የነበረውን ጊዜ ገልጿል።
ኤቭራ በአፍሪካ ሀገራት እየተዘዋወረ ወጣቶችን ለተሻለ ስኬት የማነሳሳት እና ሌሎችንም ተግባራት እየፈፀመ ነው።
ኤቭራ ሴኔጋል ዳካር ውስጥ የተወለደ ሲሆን ያደገው ፈረንሳይ ውስጥ ነው።
በነገራችን ላይ ብዙ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አባላት አፍሪካዊ ተወላጆች ሲሆኑ በሚገርም ሁኔታ የፈረንሣይ 2018 የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ቡድን 87 በመቶው አፍሪካዊ ስር መሰረት ያላቸው ተጨዋቾችን ያቀፈ ነው።
የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የአፍሪካ ሀገራትን በቅኝ በሚገዙበት ወቅት ፈረንሳይ ሴኔጋልን ጨምሮ በርከት ያሉ ሀገራትን በቅኝ ግዛት ትገዛ ነበር።
@tikvahethsport