TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
#GoldenBoyAward

በየአመቱ የሚካሄደው የ " GOLDEN BOY " ሽልማት በዚህ ዓመትም ሲጠበቅ የመጨረሻ #አርባ ውስጥ የተካተቱ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆኗል ።

በጣልያኑ የስፖርት ጋዜጣ ቱቶ ስፖርት አዘጋጅነት የሚካሄደው ውድድር ዘንድሮ ላይ አስራ ዘጠነኛ አመቱን ይዟል ።

ሽልማቱ በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚጫወቱ እድሜያቸው ከ 21ዓመት በታች የሆኑ ተጫዋቾች ብቻ ተሳታፊ የሚያደርግ ይሆናል ።

ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ጇ ፍሊክስ እና ማቲያስ ዲ ላይት ያለፉት ዓመታት አሸናፊዎች እንደነበሩ ይታወሳል ።

ሙሉ የተጫዋቾች ዝርዝር በምስሉ ላይ ተገልጿል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ደስታውን ከገለፀ ችግሮች ይፈጥራሉ " በዚህ ሳምንት ከሚጠበቁ የስፔን ላሊጋ መርሀ ግብሮች መካከል በማድሪድ ደርቢ አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሪያል ማድሪድ ጋር የሚያገናኘው መርሐ ግብር ይገኝበታል። በላሊጋው ድንቅ ጅማሮ ላይ የሚገኙት ሪያል ማድሪድ የመስመር ተጫዋች ቪንሰስ ጁኒየር ደስታውን የሚገልፅበት መንገድ የአትሌቲኮ ማድሪዱን ኮኬ ያስደሰተ እንዳልሆነ ተገልጿል። ኮኬ በሰጠው ማስጠንቀቂያ " በዋንዶ…
ቪንሰስ ጁኒየር ድጋፍ እየተቸረው ነው !

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጫዋች ቪንሰስ ጁኒየር የደስታ አገላለፁን ተከትሎ በርካታ ተጫዋቾች ከጎኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

" ደስታህን ማንም ሰው እንዲወስድብህ አትፍቀድ ፣ ሁሌም ዳንስህን አሳይ ይህ አክብሮት አለመስጠት አይደለም " ሲል የሀገሩ ልጅ ቲያጎ ሲልቫ ተናግሯል።

የባርሴሎናው ዋና አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ በበኩሉ " የማንንም ክብር እስካልነካህ ድረስ ማንኛውም ተጫዋች በፈለገበት መልኩ ደስታውን መግለፅ አለበት " ሲል ለጋዜጠኞቹ ምላሹን ሰጥቷል።

በርካታ ብራዚላዊያን ተጫዋቾች በማህበራዊ ገፆቻቸው ከተጫዋቹ ጎን መሆናቸው ባጋሩት ፅሁፍ ለመመልከት ተችሏል።

ለአብነት ያክል :-

ራፊና ( ባርሴሎና ) :- " ስትደንስ እና ስትደሰት ማየት እፈልጋለሁ "

ኔይማር ( ፒኤስጂ ) :- " አሁን ባለህበት ሁኔታ ደስተኝ ነኝ ፣ በቀጣይ አግብትህ እንደንሳለን "

የስፔን የወኪሎች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆነው ፔድሮ ብራቮ ለስፔን ቴሌቪዥን በሰጠው ቃለ መጠይቅ ጉዳዩን በመቃወም " ቪንሰስ ጁኒየር ተጋጣሚዎቹን ማክበር አለበት " ብሏል።

" መደነስ እና መጨፈር ከፈለገ በብራዚል ወደሚገኘው ሳምባድሮም ይሂድ ፣ በስፔን ውስጥ ተጋጣሚህን ማክበር አለብህ " ሲል ፔድሮ ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አፄዎቹ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል !

በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣርያ እየተካፈለ የሚገኘው ፋሲል ከነማ በድምር ውጤት 3ለ1 ቡማሙሩን በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።

√ ፋሲል ከነማ በቀጣዩ ዙር የማጣርያ ደርሶ መልስ ጨዋታ የቱኒዚያውን ሴፋክሲያን የሚገጥሙ ይሆናል።

√ አፄዎቹ ከ ሴፋክሲየን ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሜዳቸው ከመስከረም 27-29/2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ ያደርገሉ።

√ የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ከጥቅምት 4-6/2015 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#ኢትዮጵያ

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች እና አሠልጣኝ ሉቺያኖ ቫሳሎ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ አሰናድታ የወሰደችውን የ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አምበል ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋች እና አሠልጣኝ በመሆን በውጤታማነት ይታወቃል።

ጋሽ ይድነቃቸው ተሰማ የሚተማመንበት ጠንካራ ስፖርተኛም ነበር ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ የአሰልጣኝነት ዘመኑ ተተኪዎች ላይ በሠራው ስራ የሚታወቀው ሉቺያኖ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

መረጃው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይፋዊ ማህበራዊ ገፅ የተገኘ ነው።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ፉልሃም እና አስቶን ቪላ አሸነፉ።

ዛሬ ምሽት የ7ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ መካሄድ የጀመረ ሲሆን አስቶን ቪላ እና ፉልሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።

አስቶንቪላ ሳውዝ ሃምፕተንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ፉልሃም ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 2 አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ በደረጃ ሰጠረዡ ሌሎች ቀሪ ጨዋታዎች እስኪካሄዱ ፉልሃም 6ኛ አስቶን ቪላ 13ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

@tikvahethaport
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለጤና ቡድንዎ የአንድነት መንፈስ አንድ አይነት ማልያ ለብሰው ውጤትዎን ያሳምሩ !

ከዋናው የስፖርት አልባሳት ስምዎ ያረፈበትን እና የታተመበትን ማልያ በ 500 ብር ብዛት ከሀያ ጀምሮ እናቀርብልዎታለን ።

ዋናው ወደ ፊት . . . . .

📞 ይደውሉ :- 📱0910 851 535   
                      📱0901138283

ቻናላችን :- https://yangx.top/wanawsportwear

📌 አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት
ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !

8:30 ዎልቭስ ከ ማንችስተር ሲቲ

10:30 ኦግስበርግ ከ ባየር ሙኒክ

10:30 ዶርትመንድ ከ ሻልክ

11:15 ባርሴሎና ከ ኤልቼ

1:30 ቶተንሀም ከ ሌስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#AddisAbabaCitycup

አስራ ስድስተኛ የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ቢቂላ ስታዲየም በስድስት ክለቦች መካከል መደረጉን ይጀምራል።

በዛሬው ዕለት ከቀኑ 8:00ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም 10:00ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቻል ጋር ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።

ተመልካቾች ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በስፍራው በመገኘት የስታዲየም መግቢያ ትኬቶችን መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ውድድሩ በአዲስ ሚድያ ኔትዎርክ በማህበራዊ ገፆቹ ፣ በራዲዮ እና ቴሌቪዥን የቀጥታ ሽፋን የሚያገኝ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቪንሰስ ጁኒየር ድጋፍ እየተቸረው ነው ! ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጫዋች ቪንሰስ ጁኒየር የደስታ አገላለፁን ተከትሎ በርካታ ተጫዋቾች ከጎኑ መሆናቸውን ገልፀዋል። " ደስታህን ማንም ሰው እንዲወስድብህ አትፍቀድ ፣ ሁሌም ዳንስህን አሳይ ይህ አክብሮት አለመስጠት አይደለም " ሲል የሀገሩ ልጅ ቲያጎ ሲልቫ ተናግሯል። የባርሴሎናው ዋና አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ በበኩሉ " የማንንም ክብር…
" ለትምህርታዊ ነገር ብዙ እሰራለሁ "

ብራዚላዊው የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር ተጫዋች ቪንሰስ ጁኒየር ደስታ አገላለፁን ተከትሎ በርካታ የዘረኝነት ጥቃት እና ተቃውሞ እየደረሱበት መሆኑ ተዘግቧል።

ተጫዋቹ በጉዳዩ ላይ ዝምታውን ሲሰብር " የዘረኝነት ጥቃት ሲፈፀምብኝ " ነበር ሲል " በአውሮፓ ውስጥ የድል አድራጊው ጥቁር ብራዚላዊ ደስታ ያስጨንቃል።

ዳንሶቼ ደስታዬን ለመግለፅ የምጠቀምባቸው ናቸው ፣ ተቀበሉት አክብሩት የማቆመው ነገር አይደለም " ሲል ቪንሰስ ጁኒየር ተናግሯል።

ቪንሰስ አያይዞም ከማንም የገንዘብ ድጋፍ ሳይጠብቅ ለህፃናት የሚሆን የትምህርት መተግበሪያ መስራቱ ተገልጿል።

" በስሜ ትምህርት ቤት እየሰራሁ ነው ፣ ለትምህርታዊ ነገር ብዙ እሰራለሁ መጪው ትውልድ ልክ እንደ እኔ #ዘረኞችን ለመዋጋት እንዲዘጋጅ እፈልጋለሁ " ሲል አሳስቧል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#ኤቭራ

ዝነኛው የቀድሞ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንና የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ፓትሪስ ኤቭራ ወደ ኃላ መመለስ ቢችል ለፈረንሳይ ከመጫወት ይልቅ ለትውልድ ሀገሩ ለሴኔጋል መጫወትን እንደሚመርጥ ለRMC በሰጠው ቃል ተናግሯል።

ኤቭራ ፤ ወደ ኃላ መመለስ ብችል ፈረንሳይን ከመወከል ይልቅ የትውልድ ሀገሬን ሴኔጋልን ለመወከል እመርጥ ነበር ብሏል።

አክሎም ፤ " ጥሩ ስትጫወት እና ስታሸንፍ እንደ ፈረንሳዊ ትከበራለህ ፤ ነገር ግን ቡድኑ ሽንፈት ሲገጥመው እንደ ሴኔጋላዊ ተነጥለህ ትወጣለህ " ሲል ለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ሲጫወት የነበረውን ጊዜ ገልጿል።

ኤቭራ በአፍሪካ ሀገራት እየተዘዋወረ ወጣቶችን ለተሻለ ስኬት የማነሳሳት እና ሌሎችንም ተግባራት እየፈፀመ ነው።

ኤቭራ ሴኔጋል ዳካር ውስጥ የተወለደ ሲሆን ያደገው ፈረንሳይ ውስጥ ነው።

በነገራችን ላይ ብዙ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አባላት አፍሪካዊ ተወላጆች ሲሆኑ በሚገርም ሁኔታ የፈረንሣይ 2018 የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ቡድን 87 በመቶው አፍሪካዊ ስር መሰረት ያላቸው ተጨዋቾችን ያቀፈ ነው።

የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የአፍሪካ ሀገራትን በቅኝ በሚገዙበት ወቅት ፈረንሳይ ሴኔጋልን ጨምሮ በርከት ያሉ ሀገራትን በቅኝ ግዛት ትገዛ ነበር።

@tikvahethsport
#MadridDerby

በላሊጋው በዚህ ሳምንት ከሚጠበቁ መርሐ ግብሮች መካከል አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሪያል ማድሪድ በነገው ዕለት ምሽት 4:00 ሰዓት በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ የሚያደርጉት ጨዋታ ይገኝበታል።

የአትሌቲኮ ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሚዮኔ በነገው ጨዋታ ሳቪች ፣ ሌማር ፣ ሂሚኔዝ እና ሬጉሊዮን በጨዋታው #እንደማይኖሩ ገልፀዋል።

በተቃራኒው ግብ ጠባቂው ጇን ኦብላክ ለጨዋታው ዝግጁ መሆኑን እና የነገውን ጨዋታ በቋሚ አሰላለፍ እንደሚጀምር ዲያጎ ሲሚዮኔ አሳውቋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሀገራችን 🇪🇹 ተጋጣሚዋን አውቃለች ! በሀገራችን አስተናጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር ከመስከረም 20/2015 ጀምሮ ሲካሄድ የምድብ ድልድሉ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል። #አስር ሀገራት በሚሳታፉበት ከ 17ዓመት በታች ውድድር ሀገራችን በምድብ አንድ ተደልድላለች። ምድብ ድልድሉ ምን ይመስላል ? ምድብ አንድ :- ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ኤርትራ ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ምድብ…
የሴካፋ መርሐ ግብር ይፋ ሆኗል!

ሀገራችን የምታስተናግደው የሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር የምድብ ድልድል ከቀናት በፊት ይፋ መሆኑ ሲታወስ የውድድር ሙሉ መርሐ ግብር ታውቋል።

በመክፈቻው መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ከታንዛኒያ ጋር ስታጨወት በመቀጠል ከ ደቡብ ሱዳን ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ ጋር ትጫወታለች።

ሁሉም ጨዋታዎች በአበበ በቂላ ስታዲየም ስደረግ ሙሉ የውድድሩ መርሐ ግብር ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

8:30 ወልቭስ ከ ማንችስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
14 ' ወልቭስ 0 - 1 ማንችስተር ሲቲ

ግሪሊሽ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
21' ወልቭስ 0 - 2 ማንችስተር ሲቲ

                            ግሪሊሽ ⚽️ ሃላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe