TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
" ከ ቼልሲ ውጪ አንድም ክለብ አላወራሁም "

የ ፕርሚየር ሊጉ መሪ ቼልሲ ጀርመናዊ የ መሐል ተከላካይ አንቶኒ ሩዲገር የ ቼልሲ ቀጣይ ቆይታውን አስመልክቶ አስተያየቱን ሰጥቷል ።

" ለ እኔ አሁን የ እግር ኳስ ህይወቴ በጣም አስፈላጊው ውሳኔ ይሆናል ፣ ከ ቼልሲ በስተቀር ከ ሌላ ክለብ ጋር አላወራሁም " ሲል ተናግሯል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ጨዋታ አሰላለፍ !

የ:ኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች የ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል እየተመራ ዛሬ ከ ሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ የ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

የመጀመሪያ 11 ቋሚ ተሰላፊዎች

ግብ ጠባቂ        
1. እየሩሳሌም ሎራቶ 

ተከላካዮች         
1. ብዙአየሁ ታደሰ       
2. ብርቄ አማረ
3. ቤተልሔም በቀለ
4. ናርዶስ ጌትነት( አምበል)    
                              
አማካዮች    
1. ማዕድን ሳህሉ     
2. ገነት ሀይሉ           
3. መሳይ ተመስገን  

አጥቂዎች     
1. አረጋሽ ካልሳ        
2. ቱሪስት ለማ                      
3. ረድኤት አስረሳኸኝ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የ ቴሌቪዥን ሽፋን አያገኝም !

ነገ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የሚጀምረው የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በየትኛውም ቴሌቭዥን የ ቀጥታ ስርጭት #እንደማይኖረው ታውቋል፡፡

ውድድሩ ባለፉት አመታት የ ቀጥታ ስርጭት ሲያገኝ ቢቆይም አሁን ላይ አስቸኳይ #ሀገራዊ ስራዎች በ መብዛታቸው ምክንያት የቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት አይኖርም፡፡

የ አበበ ቢቂላ ስታድዬም መያዝ ከሚችለው በ #ከፊል ተመልካች እንዲገባ ስለተፈቀደ የ ስፖርት ቤተሰቡ በ አካል በ መገኘት መታደም ይቻላል፡፡

Credit :- #AFF

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለ 34 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከ ዩጋንዳ አቻው ጋር ላለበት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ቅድመ ዝግጅት ለማካሄድ ይረዳው አሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረጉ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች መስከረም 14 ቀን 2014ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ወሎ ሰፈር በሚገኘው…
ሉሲዎቹ ጨዋታቸውን መቼ ያካሂዳሉ ?

በ ሞሮኮ አስተናጋጅነት በ 2021 የ ውድድር አመት ለሚካሄደው የ አፍሪካ ዋንጫ ሉሲዎቹ የ ማጣርያ ውድድራቸውን ከ ዩጋንዳ ጋር እንደሚያደርጉ ይታወሳል ።

ሉሲዎቹ የ መጀመሪያ ጨዋታቸውን ከ ሜዳቸው ውጪ በ ሴንት ሜሪ ስታዲየም ካምፓላ ላይ ጥቅምት 10 ሲያካሄዱ የ መልሱ ጨዋታው በ ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ጥቅምት 16 እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
5 ' ሩዋንዳ 0 - 0 ኢትዮጵያ

*ከ 20 ዓመት በታች የ አለም ዋንጫ ማጣርያ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
20 ' ሩዋንዳ 0 - 1 ኢትዮጵያ

*ከ 20 ዓመት በታች የ አለም ዋንጫ ማጣርያ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
28 ' ሩዋንዳ 0 - 2 ኢትዮጵያ
ረድኤት አስረሳኸኝ

*ከ 20 ዓመት በታች የ አለም ዋንጫ ማጣርያ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ዋልያዎቹ አዲስ ማልያ ይፋ ሆነ !

የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ UMBRO የ ትጥቅ አምራች ጋር በመሆን ያስመጣውን አዲስ ማልያ ከ ደቂቃዎች በፊት በ ጁፒተር ሆቴል አስተዋውቋል ።

የ ሉሲዎቹ እና ዋልያዎቹ ተጫዋቾች በ ስፍራው በመገኘት አዲሱን ማልያን ማስተዋወቅ ችለዋል ።

ብሔራዊ ቡድናችን የሚለብሳቸው የተጫዋቾች እና ግብ ጠባቂ መለያዎች በ ምስሉ ላይ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሩዋንዳ 0 - 4 ኢትዮጵያ
ረድኤት አስረሳኸኝ
አረጋሽ ካልሳ
ቱሪስት ለማ

*ከ 20 ዓመት በታች የ አለም ዋንጫ ማጣርያ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ሩዋንዳ 0 - 4 ኢትዮጵያ
ረድኤት አስረሳኸኝ
አረጋሽ ካልሳ
ቱሪስት ለማ

Photo :- Ethiopian Football Federation

*ከ 20 ዓመት በታች የ አለም ዋንጫ ማጣርያ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ ወደ ባህር ዳር መቼ ይጓዛሉ ?

የ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ ደቡብ አፍሪካ አቻቸው ጋር ላለባቸው የ አለም ዋንጫ የ ምድቡ ሶስተኛ ጨዋታ ዝግጅታቸውን በ ባህር ዳር እንደሚያደርጉ ይታወሳል ።

ዋልያዎቹ በነገው ዕለት አመሻሻ ወደ ባህር ዳር በ ማቅናት ዝግጅታቸውን ማድረግ እንደሚጀምሩ ለማወቅ ተችሏል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና አሰልጣኙ የ ጨዋታ ቅጣት ተላለፈበት !

የ ካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማን ከ ካዲዝ ጋር የተመለከተውን ቀይ ካርድ ተከትሎ ለ ሁለት ጨዋታዎች ቡድኑን እንደማይመሩ ተገልጿል ።

ይህንንም ተከትሎ ሮናልድ ኩማን ከ ሌቫንቴ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ጋር በሚያደርጉት ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ቡድናቸውን በ አሰልጣኝ ቦታ ላይ አይመሩም ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ለ ጋርድዮላ ከፍተኛ አክብሮት አለኝ "

በ ሳምንቱ ከሚጠበቁ የ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች መካከል የ ሊጉ መሪ ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት የ #ነገ ጨዋታ ተጠቃሹ ነው ።

ከ ጨዋታው አስቀድሞ አስተያየታቸውን ለ ጋዜጠኞች የሰጡት ቶማስ ቱሄል አክብሮታቸውን ለ ፔፕ ጋርድዮላ ገልፀዋል ።

" ለ ፔፕ ከፍተኛ አክብሮት አለኝ ፣ በ አሰልጣኝነት ጉዞ ከ መጀመሪያዋ ቀን አንስቶ በ ባርሴሎና ፣ ባየር ሙኒክ እና ማንቸስተር ሲቲ ለ ፈጠረው ትልቅ ተፅዕኖ ትልቅ አክብሮት አለኝ " ሲል ቶማስ ቱሄል ሀሳባቸውን ሰጥተዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዳኒ አልቬስ ከ ክለቡ ጋር ተለያየ ! ብራዚላዊው የ ቀድሞው የ ባርሴሎና ስኬታማ የ ቀኝ መስመር ተጫዋች ዳኒ አልቬስ ከ አሁኑ ክለቡ ጋር መለያየቱ ተገልጿል ። በ ሀገሩ ብራዚል ለ ሳኦ ፖሎ እየተጫወተ የሚገኘው ዳኒ አልቬስ የ ደሞዝ ክፍያው መዘይገቱን ተከትሎ ክለቡን መልቀቁ ይፋ ሆኗል ። @tikvahethsport @kidusyoftahe
ዳኒ አልቬስ በዚህ አመት አይጫወትም !

በ ባርሴሎና ቤት በርካታ ድሎችን ያጣጣመው ብራዚላዊው የ ቀኝ መስመር ተጫዋች ዳኒ አልቬስ ደሞዝ በ ወቅቱ ሳይከፈለው በ መቅረቱ ከ ሳኦ ፖሎ ክለብ ጋር መለያየቱ ይታወሳል ።

ስሙ ከ በርካታ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቢቆይም ዳኒ አልቬስ የ ውድድር ዓመቱን ለየትኛውም ክለብ እንደማይፈርም ይፋ አድርጓል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !

8:30 ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ

8:30 ማንችስተር ዩናይትድ ከ አስቶን ቪላ

10:00 ስፔዚያ ከ ኤሲ ሚላን

1:00 ኢንተር ሚላን ከ አታላንታ

1:30 ብሬንትፎርድ ከ ሊቨርፑል

4:00 ፒኤስጂ ከ ሞንትፔሊዬ

4:00 ሪያል ማድሪድ ከ ቪያሪያል

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ ከተማ ከተማ ዋንጫ በ ዛሬው ዕለት በ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በ ድምቀት ይጀመራል ።

በ መክፈቻ ጨዋታ ከ ምድብ አንድ ወደ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ያደጉት አዲስ አበባ ከተማ እና መከላከያ በ 8:00 ሰዓት የ መጀመሪያ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ ።

በዚህ ሲቲ ካፕ ውድድር ሁለቱም ክለቦች በሚኖራቸው ተሳትፎ ለ 2014 ዓ.ም ለሚጠብቃቸው የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አቋማቸውን እንደሚለኩበት ይጠበቃል ።

በ ሁለተኛ ጨዋታ በ 10:00 ሰዐት በ ምድብ አንድ የተደለደሉት ኢትዮጵያ ቡና እና ጅማ አባጁፋር ይጫወታሉ ።

#AAFF

@tikvahethsport @kidusyoftahe