TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
#UpdateSport የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ሲለያዩ ደጋፊዎች አላስፈላጊ ምልክቶችን በማሳየት ከጨዋታው በፊትም መጠነኛ ግጭት መከሰቱ ተገልጧል። የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የመቀሌ 70 እንደርታ እግር ኳስ ቡድኖች ጨዋታ ከዚህ ቀደም በጸጥታ ስጋት የተነሳ ተሰርዞ የፕሬሚየር ሊጉም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ተደርጎ ነበር።

Via #DW
@tikvahethsport
#UpdateSport መከላከያ እና ደቡብ ፖሊስ ደደቢትን ተከትለው ከፕሪሚየር ሊጉ ወርዱዋል። #FBC

@tikvahethsport
#UpdateSport የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮቸ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የቅዱስ ጊዮርጊስን የሜዳ ተጠቃሚነት ለማሳጣት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሊያደርገው የነበረን ጨዋታ በዝግ ወይም አዳማ ተጫወቱ በማለት ሁለት ጊዜ እንዲቋረጥ አድርጎል ብሏል፡፡

ይህን ጨዋታ ከዚህ በፊት የተቋረጡ የሌሎች ክለቦች ጨዋታወችን ባስተናገደበት ሁኔታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን አላስተናገደም ሲል በፌዴሬሽኑ ላይ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

እንዲሁም በ29ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ለፋሲል ከነማ የተሰጠው ፎርፌ አግባብነት የሌለውና አድሏዊ መሆኑንም ነው በመግለጫው ያመላከተው፡፡

አዲስ ከመጡት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ጋር በመተባበር፣ በመቻቻል እና በመተጋገዝ ለመስራት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷልም ነው ያለው፡፡

በመሆኑም ፌዴሬሽኑ የወሰናቸውን ኢ – ፍትሃዊ እርምጃዎችን እንዲመረምር እና ያላአግባብ የተወሰነበትን ፎርፌ እንዲያነሳ የጠየቀ ሲሆን ያቀረባቸው ቅሬታዎች ምላሽ እስከሚያገኙ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮች ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡

Via #fbc
@tikvahethsport