TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#ጥቆማ

የአውራ አምባ ማይክሮ ፋይናንስ በአዲስ አበባ ለሚከፍታቸው ቅርንጫፎች በ4 የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

በመሆኑም ከላይ ተያያዙትን መረጃዎች በመመልከት እስከ መስከረም 18/ 2017 ድረስ ማመልከት እንድትችሉ ጥቆማ ቀርቧል።

አድራሻ፦ ለገሃር አመልድ ህንፃ አማራ ባንክ የሚገኝበት 2ኛ ፎቅ የአውራ አምባ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ቅርንጫፍ።

በኢሜል ለመላክ [email protected] መጠቀም ትችላላችሁ ተብሏል።

Via @tikvahmagbot

@tikvahethmagazine
እስራኤል በቤሩት ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት ከፍተኛ የሂዝቦላህ መሪዎችን ጨምሮ 31 ሰዎች ተገደሉ።

በደቡባዊ ቤይሩት በሚገኝ ህንጻ ላይ በትላንትናው ዕለት እስራኤል ባደረሰችው ሄዝቦላን ኢላማ ያደረገ የሚሳኤል ጥቃት ቢያንስ 31 ሰዎች መሞታቸውን የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፍራስ አቢያድ ተናግረዋል።

ከሟቾቹ መካከል የሂዝቦላህ አዛዥ ኢብራሂም አቂልን ጨምሮ ሌሎችም በስም ያልተጠቀሱ አዛዦች ይገኙበታል ተብሏል።

ከጥቃቱ በኋላ በአቅራቢያው ያሉ ሕንፃዎች ለግማሽ ሰዓት ያህል መናወጣቸውን የዓይን እማኞች መናገራቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል።

በቤይሩት የሚገኘው የሲኤንኤን ቡድን ከፍርስራሹ ስር ያሉትን ሰዎች ለመታደግ እና የቆሰሉትን በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ተመልክቷል።

• አቂል ማን ነበር?፡

አሜሪካ በ1983 የአሜሪካ ኤምባሲ ጥቃት 63 ሰዎች ሞት እንዲሁም በቤይሩት የባህር ኃይል ጦር ሰፈር ላይ በደረሰው የሂዝቦላ የቦምብ ጥቃት፣ 241 የአሜሪካ ወታደሮች ሞት እጁ አለበት ስትል ትከሳለች።

ባለፈው አመት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለእሱ መረጃ ለሰጠ እስከ 7 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።

እስራኤል ጥቃቱን ለምን ፈፀመችው፡-

በሰሜን እስራኤል በገሊላ የሚገኙ ማህበረሰቦችን ለመውረር እና ለመያዝ እንዲሁም ሲቪሎችን እና የእስራኤል ወታደሮችን ለመግደል አቂል እና አዛዦቹ የዕቅዱ ንድፍ አውጪዎች መሆናቸውን የእስራኤል ጦር ገልጿል።

በጥቃቱም የሂዝቦላህ ቁንጮ የሆነው አቂል ከበርካታ አዛዦች ጋር ተገድሏል ሲሉ የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ተናግረዋል።

@tikvahethmagazine
የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ በቀጣዩ ምርጫ እንደማይሳተፍ አሳወቀ።

በዩጋንዳ 2026 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እወዳደራለው ያለው የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ አባቱን በምርጫ ሂደት ላይ እንደሚደግፍምና በቀጣዩ ምርጫ ላይ እንደማይሳተፍ አሳውቋል።

የ80 ዓመቱ ሙሴቬኒ ከ1986 ጀምሮ በስልጣን መንበራቸው ላይ ይገኛሉ። ልጃቸውም፥ የዩጋንዳ መከላከያ ሃይል መሪ ሲሆን በርካቶች "ሙሁዚ ካይኔሩጋባ" ን የሙሴቬኒ አልጋ ወራሽ ይሆናል ብለው ይጠብቁታል።

ይህንን ተከትሎ ሙሁዚ "በ2026 በምርጫ ውድድር ላይ እንደማልሳተፍ ማሳወቅ እፈልጋለሁ" ሲል ተናግሯል። በጦር ሠራዊቱ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ገልጿል።

ሙሴቬኒ ቀጣዩን ምርጫ በማሸነፍ ሰባተኛ የስልጣን ዘመናቸውን ይቀጥሉ እንደሆነ ያሉት ነገር ባይኖርም የልጃቸው አስተያየት ፖርቲያቸው በቀጣዩ ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት እጩ አድርጎ እንደሚያቀርብ ፍንጭ የሰጠ ነው ተብሏል።

ልጃቸው ካይኔሩጋባ "ከፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ በኋላ ማንም ሲቪል ዩጋንዳ እንዲመራ የፀጥታ ሀይሉ አይፈቅድም። ቀጣዩ መሪ ወታደር ወይም ፖሊስ ብቻ ይሆናል" ሲልም ተናግሯል።

ሙሴቬኒ እ.ኤ.አ በ 1986 ፕሬዝዳንት ሚልተን ኦቦቴን ከስልጣን ካስወገዱ በኋላ ነበር ወደ ስልጣን የመጡት። በ2021 ደግሞ ለ6ኛ የስልጣን ዘመን ተወዳድረው በ58% ድምጽ በድጋሚ ተመርጠዋል።

@tikvahethmagazine
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ከለሊቱ 06፡00 ሰዓት እስከ ነገ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲቢኢ ብር አገልግሎት በሲስተም ማሻሻያ ምክንያት በጊዜያዊነት አገልግሎት እንደሚቋረጥ ገልጿል።

@tikvahethmagazine
እንዳያመልጦ!!!!

መኖሪያ ቤቶን በፒያሳ ያድርጉ

ለመኖሪያም ሆነ ለኢንቨስትመንት ምቹ በሆነዉ ፒያሳ ከሊሴ ት/ቤት አጠገብ በመገንባት ላይ የሚገኝ አማራጭ የመኖሪያ አፓርትመንት በገበያ ላይ ከቴምር ሪል ስቴት

👍 ከአንድ እስከ ሶስት መኝታ

👍ከ500,000 ብር ጀምሮ

👍 ከአራተኛ ፍሎር ጀምሮ

👍 በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ

👍 በ3 ዓመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ

ለበለጠ መረጃ
0911966922
0973272829
Telegram: https://yangx.top/hizkish
WhatsApp: https://wa.me/251911966922
ለቢዝነሶ ወይም ለግሎ ዌብሳይት ይፈልጋሉ?

እኛ ዛየን ዌብ (Zion Web) እንሰኛለን። ደረጃውን የጠበቀ ዌብሳይት ዲዛይን አድርገን በአጭር ጊዜ ውስጥ በተመጣጣኝ ዋጋ እናስረክባለን።
አሁኑኑ ደዉለዉ 📞0922501644 or @muzika23

1. ከአንድ አመት ዌብ ሆስቲንግ
2. እስከፈለጉት ድረስ የድርጅቶ ኢሜል አድሬስ ለእርሶ እና ለሰራተኞቾች

አሁኑኑ ደዉለዉ የድርጅቶን ዌብሳይት ያስጀምሩ 📞 0922501644 or @muzika23

🏢 SarBet Beside Effoi Pizza
📥 https://yangx.top/zionwebs
#NewsUpdate

ትላንት ምሽቱን የሂዝቦላ ታጣቂ ኃይል በእስራኤል ላይ ተኩስ ከፍቶ አድሯል። የምሽቱ የሮኬት ጥቃቶች ኢንዱስትሪ እና ወታደራዊ ቦታዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ሲል የእስራኤል ጦር ገልጿል።

መነሻቸውን ከሊባኖስ አድርገው ወደ ሰሜናዊ እስራኤል ክፍል የተተኮሱት ሮኬቶች መካከል 105 ሮኬቶችን ማክሸፉንም ጨምሮ ገልጿል። ይህም ሆኖ ግን በተወሰኑ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

ሄዝቦላህ በበኩሉ ባለፈው ሳምንት ለደረሰው የፔጀር እና የዎኪ ቶኪ ጥቃት አጸፋ በደርዘን የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል መተኮሱን ተናግሯል።

እስራኤል በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ እንዲዘጉ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። በቡድን መሰባሰብንም ገድባለች።

@tikvahethmagazine
#Telegram 🇺🇦

ዩክሬን የቴሌግራም የመልእክት መላላኪያ መድረክን ለመንግስት እና ወታደራዊ ሰራተኞች እንዲሁም ለመከላከያ ሴክተር እና ወሳኝ የመሠረተ ልማት ሰራተኞች በተሰጡ ኦፊሴላዊ መሳሪያዎች ላይ አገልግሎት ላይ እንዳይውል አግዳለች።

እገዳው የግል የሞባይል ስልኮችን አያካትትም ተብሏል።

እግዱ የወጣው በ2022 በዩክሬን ላይ ሙሉ ወረራ በጀመረችው ሩሲያ የሚፈጠረውን ስጋት “ለመቀነስ” ነው ሲል የሀገሪቱ ኃያል የብሄራዊ ደህንነት እና መከላከያ ምክር ቤት ተናግሯል።

የደህንነት ምክር ቤቱ "ጠላት ቴሌግራምን ለሳይበር ጥቃት፣ለተንኮል አዘል ሶፍትዌሮች ስርጭት፣ለሚሳኤል ጥቃት ቦታ ጥቆማ በንቃት ይጠቀማል" ሲል ለእገዳው ምክንያቱን አስቀምጧል።

ቴሌግራም የዩክሬን እና የሩሲያ የመንግስት እና የጦር ባለስልጣናት በስፋት የሚጠቀሙት የመረጃ መለዋወጫ መተግበሪያ ነው።

እገዳው ተግባራዊ እንዲሆን በዩክሬን ከፍተኛ የመረጃ ደኅንነት ባለሥልጣናት፣ ወታደራዊ እና የህግ አውጭዎች ባደረጉት ስብሰባ ከስምምነት ላይ መደረሱን ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።

የወታደራዊ መረጃ ሃላፊው ኪሪሎ ቡዳኖቭ እንደገለጹት የተሰረዙ መልእክቶችን እና የተጠቃሚዎችን ግላዊ የመልእክት ልውውጦችን የሩስያ ሃይሎች ማግኘት መቻላቸውን የሚያሳዩ ተአማኒ ማስረጃዎች አሉ ብሏል።

"የመናገር ነፃነትን ሁሌም እደግፋለሁ ነገር ግን የቴሌግራም ጉዳይ የመናገር ነፃነት ጉዳይ አይደለም፣ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ነው" ሲል ቡዳኖቭ ተናግሯል።

ቴሌግራም መጠቀም የስራቸው አካል የሆኑ ባለስልጣናት ከእገዳው ነፃ ይሆናሉ ተብሏል።

ቴሌግራም ለቢቢሲ በሰጠው መግለጫ "ሩሲያን ጨምሮ ለየትኛውም ሀገር ምንም አይነት የመልዕክት መረጃ አላቀረበም" ብሏል።

አክሎም አንድ ጊዜ የተሰረዙ መልእክቶች ከተሰረዙ በኋላ ዳግም የሚታዩበት በቴክኒክ ደረጃ ምንም አይነት መንገድ የለም ሲልም ገልጿል።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የዘመን መለወጫ በዓላት በ #ኢትዮጵያ 🇪🇹

🎆 ጊፋታ (የዎላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ)

🎆 ማሽቃሮ (የካፊቾ የዘመን መለወጫ በዓል)

🎆 ያሆዴ (የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል)

🎆 መሳላ (የከምባታ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል)

🎆 የጎፋ ''ጋዜ'' ማስቃላ እና የኦይዳ ''#ዮኦ'' ማስቃላ በዓል

🎆 ሄቦ (የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል)

🎆 ዮ__ማስቃላ (የጋሞ ብሔር ዘመን መለወጫ)

🎆 ጋሪ ዎሮ (በቦሮ-ሺናሻ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል)

እንኳን አደረሳችሁ!

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ኃይል በሚያገኝበት ሁኔታ ላይ የዳሰሳ ጥናት ተጀመረ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአሶሳ ከተማ እንዲሁም በክልሉ የሚታየውን ሰፊ የኃይል አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል በሚገኝበት ዙሪያ የዳሰሳ ጥናት መጀመሩ ተገልጿል።

ከህዳሴ ግድብ እስከ አሶሳ ድረስ ያለውን 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ መስመር ለመዘርጋት የዳሰሳ ጥናቱ መጀመሩን የተቋሙ ኃላፊ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ አረጋግጠዋል።

ይህ ፕሮጀክት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚታየውን የኤሌክትሪክ አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ በረጅም ጊዜ የተቀመጠ አማራጭ ነው ተብሏል።

የዳሰሳ ጥናቱ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚፈጅ እንዲሁም የአዋጭነት ጥናት ጭምር ሲሆን አራት ወራትን ይፈጃል ተብሏል።

ተግባራዊነቱ ተረጋግጦ ወደ ግንባታ ከተገባም ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ሦስት አመት ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ እንደሚችል ሪፖርተር ዘግቧል።

@tikvahethmagazine
#Update

° እስራኤል በዛሬው እለት ሂዝቦላ ይንቀሳቀስባቸዋል ባለቻቸው ከ800 በላይ ቦታዎች ላይ ጥቃት ከፍታለች።

° የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር በጥቃቱ ቢያንስ 270 ሰዎች መሞታቸውን ሲግልጽ፤ 21 ህጻናት ናቸው ብሏል።

እስራኤል በዛሬው እለት "የሂዝቦላ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ናቸው" ባለቻቸው ከ8 መቶ በላይ በሚቆጠሩ ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ከፍታለች።

ጥቃቱ የጋዛ ግጭት ከጀመረ በኋላ ከፍተኛው ነው ሲባል በቀጠናው ውጥረት ነግሷል።

ከሟቾቹ መካከል ምን ያህሉ ሲቪሎች ወይም የሂዝቦላህ ታጣቂዎች እንደሆኑ ግልፅ ባይሆንም እስራኤል ጥቃቶቹ ያነጣጠሩት ሂዝቦላ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ ገልጻለች።

እስራኤል የጥቃት ትኩረቷን ወደ ሰሜናዊ ድንበር አዙራለች የተባለ ሲሆን በኢራን ይደገፋል የተባለው የሂዝቦላ ጦር ሃማስን በመደገፍ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን እያስወነጨፈ ነው ተብሏል።

የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ባሰራጩት የቪዲዮ መልእክት "የሰሜን አካባቢ ነዋሪዎችን በሰላም ወደ ቤታቸው በመመለስ ሂደት ውስጥ ግባችን ላይ እስክንደርስ ድረስ ጥቃቶቹ ይቀጥላሉ" ሲሉ ተናግረዋል።

በጥቃቱ ቢያንስ 270 ሰዎች መሞታቸው ሲገልፅ ከ1,024ሰዎች በላይ መቁሰላቸውን የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከተጎጂዎቹ መካከል ሴቶች እና ህጻናትን እንደሚገኙነት የሊባኖስ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። የሊባኖስ ነዋሪዎች ሂዝቦላህ የጦር መሳሪያውን ከሚያከማችባቸው ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ እስራኤል ማሳሰቢያ ሰጥታለች ተብሏል።

የሂዝቦላ ጦር ለጥቃቱ ሰጠሁት ባለው አፀፋዊ ምላሸ በእስራኤል ወታደራዊ ካምፖች ላይ ሮኬቶችን ማስወንጨፉን ገልጿል።

እስራኤል ይህን መሰል ጥቃት ስትፈጽም ከ2006 በኋላ ይኽ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

@tikvahethmagazine
#ሊባኖስ

በሊባኖስ እና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ
ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ
በሊባኖስ፤ የቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤት የጥንቃቄ መልዕከት አስተላልፏል።

ፅ/ቤቱ "በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ እንዲሁም በቤይሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተጠናከረው ቀጥለዋል" ብሏል።

ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤቱ የሁኔታውን አሳሳቢነት ተረድቶ፣ የዜጎቻችን ደህንነት ለማስጠበቅ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን እየተከታተለ እንደሚገኝም አሳውቋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች ዜጎች እንድትወስዱ ሲል አሳስቧል።

1. በአብዛኛው የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይቻላሉ ተብለው ከሚታሰቡ ቦታዎች እራስን ማራቅ፣

2. ከሊባኖስ መንግስት የሚሰጡ መመሪያዎችን እና አቅጣጫዎችን መተግበር ወይም ማከበር፤

3. አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ የበለጠ እየከፋ የሚሄድ ከሆነ በቀጣይ የምንወስዳቸውን እርምጃዎችን ይፋ ስለምናደግ ከቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ የፌስ-ቡክ ፔጅ የሚለቀቁ መረጃዎችን በየጊዜው መከታተል፣

4. ማንኛውንም የከፋ ሁኔታ በሚገጥማችሁ ወቅት በቆንስላው ቀጥታ የስልክ መስመር +9615467166 እና በWhatsapp ቁጥር ማሳወቅ ጠቃሚ ይሆናል።

@tikvahethmagazine
በደመራ እና በኢሬቻ በዓላት ለሚያስተባብሩ 310ሺህ ወጣቶች ስምሪት ተሰጠ።

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበር ለሚያስተባብሩ 310 ሺህ ለሚሆኑ የከተማው ወጣቶች የስራ ስምሪት ተሰጥቷል።

ስምሪቱን የሰጡት፥ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም ፀጥታ ቢሮ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በመሆን ነው።

ወጣቶቹ፥ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው በተሰጣቸው ስምሪት መሰረት እንዲሰሩና በበዓላቱ እንዳይያዙ የተከለከሉ ነገሮችን እና በኮሪደር ልማት የተሰሩ የልማት ስራዎችን  እንዲቆጣጠሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።

መረጃው የአ/አ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine