የ "ቢቂላ አዋርድ" የሽልማት ሥነ-ስርዓት በአዲስ አበባ . . .
በታላቁ አትሌት አበበ ቢቂላ ስም የተሰየመውና መቀመጫውን ቶሮንቶ ያደረገው የቢቂላ አዋርድ በተለያዩ ዘርፎች፣ በ2023 ለኢትዮጵያ በሙያቸው ጉልህ ድርሻ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅናን ሰጥቶ ነበር።
ቶሮንቶ ላይ በተካሄደው ሽልማት፣ በተለያዩ ምክንያት መገኘት ያልቻሉ ተሸላሚዎች፣ ህዳር 2 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ በሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደ የሽልማት ሥነ-ስርዓት የዕውቅና ዋንጫቸውን ከቢቂላ አዋርድ ተቀብለዋል።
በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ መገኘት ያልቻሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ዋና ስራ አስፈጻሚና የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ግርማ ዋቄ፣ በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ እንዲሁም ቤተልሄም ደሴ እሁድ በተደረገው መርሐግብር ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።
የቢቂላ አዋርድ ለእነማን እውቅና ሰጠ?
ቶሮንቶ ላይ የተካሄደው የቢቂላ አዋርድ፥ በኢትዮጵያ አንፀባራቂ ኮከብ ሽልማት ዘርፍ ለተከበሩ አቶ ከተማ ይፍሩ እውቅና ሰጥቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ ዓለም-አቀፍ የአየር መንገድ ልህቀት ተምሳሌትነት ሽልማትን ተበርክቶለታል።
በአካዳሚክ ልህቀት ሽልማት ዘርፍ አዳም አወቀ፣ ዶ/ር መክሊትና ሊሊያን አበበ ከፍተኛ የአካዳሚክ ችሎታ ያሳዩ በሚል እውቅና ከሽልማት ተቋሙ ተሰጥቷቸዋል።
በፕሮፌሽናል ልህቀት ሽልማት ዘርፍ እንዲሁ በሙያቸዉ ከፍተኛ ልህቀት ነበራቸው ያላቸውን ፍሰሃ አጥላው፣ ዶ/ር ብርሃኑ ቡልቻ፣ ጆሞ ታሪኩና ቤተልሄም ደሴ እውቅናና ሽልማት ሲበረከት የኃይሌ ሚናስ አካዳሚ የልህቀት ትምህርት ተቋም ሽልማትን አሸንፏል።
በተጨማሪም ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ፣ ሊበን ገብረሚካኤል እና ፒፕል ቱ ፒፕል ካናዳ የተሰኘው ተቋም በላቀ የማህበረሰብ አገልግሎት እውቅና ተበርክቶላቸዋል።
Via Yonathan Menkir/ Tikvah Family
👋 @TikvahethMagazine

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከ6 መቶ በላይ ተማሪዎችን የሚያስተናግድ ተቋም አስመረቀ።
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት (Menschen fuer Menschen) በአማራ ክልል ደቡብ ውሎ ዞን ጃማ ወረዳ በ116 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን ቴከኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ተቋም ማስመረቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ኮሌጁ በአንድ የትምህርት ዘመን ከ600 በላይ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም አለው የተባለ ሲሆን የጃማ እና ተጎራባች ወረዳ ማኅበረሰብን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
አዲስ የተመረቀው ማሰልጠኛ ተቋም ወቅታዊ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት አድርገው የተፈበረኩ ማሺነሪዎች የተሟላለት መሆኑን ነው ድርጅቱ በመግለጫው የገለጸው።
ከተያያዝነው የትምህርት ዘመን ጀምሮም በማኑፋክቸሪንግ፣ በኤሌክተሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ፣ በአውቶሞቲቭ እና የእንጨት ስራ ቴክኖሎጂዎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይጀምራል ተብሏል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በጀርመን የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰባስቲያን ብራንዲስ፥ ድርጅቱ ባለፉት አራት አስርተ-ዓመታት 466 ት/ቤቶችን ከነመማሪያ ቁሳቁሶቻቸው እንዲሁም ሰባት የቴከኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛዎችን ከነመማሪያ ማሽነሪዎቻቸው አስገንብቶ ለሕዝብና መንግስት ማስተላልፉን ጠቁመዋል።
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት አገር አቀፍ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬ በበኩላቸው ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ክልሎች የ20 የት/ቤቶች እና የሁለት ቴከኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ተቋማት ግንባታን በማከናወን ላይ የሚገኝ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ተድራሸነቱን ወደ ሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች መስፋፋቱን የገለጹት አቶ ይልማ፥ ድርጅቱ ባስገነባቸው ት/ቤቶች ብቻ በየመቱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች እየተስተናገዱ እንደሚግኙ አስረድተዋል።

TIKVAH-MAGAZINE
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቀድሞ የኢትዮጵያ አምባሳደርን የዓለም አቀፍ ጉዳዮችና የቁጥጥር ኃላፊ አድርጎ ሾመ። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በፈረንሣይ የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራን በታህሳስ 2022 ሳፋሪኮምን ድርጅቱን ለቆ የወጣውን ማቲው ሃሪሰን ሄርቪንን በመተካት የዓለም አቀፍ ጉዳዮችና እና የቁጥጥር ኃላፊው አድርጎ መሾሙ ተገልጿል። አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል እንዲሁም በ…
#Update
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ጉዳዮችና የቁጥጥር ኃላፊ ሆነው ተሹመው ለ7 ወራት ያገለገሉት አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸው ታውቋል። ኃላፊው ለመልቀቃቸው ምክንያት ትኩረት መስጠት በሚሻ የግል ጉዳያቸው የተነሳ መሆኑ ተጠቁሟል።
Credit : Capital , Addis Fortune
👋 @TikvahethMagazine
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ጉዳዮችና የቁጥጥር ኃላፊ ሆነው ተሹመው ለ7 ወራት ያገለገሉት አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸው ታውቋል። ኃላፊው ለመልቀቃቸው ምክንያት ትኩረት መስጠት በሚሻ የግል ጉዳያቸው የተነሳ መሆኑ ተጠቁሟል።
Credit : Capital , Addis Fortune
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እጅግ ውብ እና ዘመናዊ የንግድ ሱቆች ከጊፍት ሪል እስቴት
በ450,000ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ የንግድ ሱቅ ባለቤት ይሁኑ
➢ለ5ቀን ብቻ የተዘጋጀ
እንዲሁም አፓርታማዎች ጥቂት ቀርተውናል
ሱቆች ከ30ካሬ-258ካሬ አማራጭ አለን
### ከምቹ አከፉፈል ጋር 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ለበለጠ መረጃ
☎️ 0921388158
☎️ 0965875223
https://yangx.top/giftrealesta
በ450,000ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ የንግድ ሱቅ ባለቤት ይሁኑ
➢ለ5ቀን ብቻ የተዘጋጀ
እንዲሁም አፓርታማዎች ጥቂት ቀርተውናል
ሱቆች ከ30ካሬ-258ካሬ አማራጭ አለን
### ከምቹ አከፉፈል ጋር 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
ለበለጠ መረጃ
☎️ 0921388158
☎️ 0965875223
https://yangx.top/giftrealesta
#CholeraUpdate: የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል 1 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚሰጥ አስታወቀ።
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ላለው የኮሌራ ወረርሽኝ ቀጣይነት ያለው ሰብዓዊ ምላሽ ለመስጠት አንድ ሚሊዮን ዩሮ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
የአውሮፓ ህብረት ገንዘቡን የሚሰጠው ከድንገተኛ አደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ እንደሆነ ሲጠቀስ በህብረቱ የሰብአዊ መርሃ ግብር አካል ተደርጎ በሀገሪቱ በበሽታው በተጎዱ አካባቢዎችና በሀገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ ተጋላጭ ማህበረሰቦች የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።
የኮሌራ ወረርሽኝ በሀገሪቱ በግጭትና ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ ምክንያት ከፍተኛ የሰብአዊ ፍላጎት ባለባቸው አካባቢዎች እርዳታ መድረስ እንዳልቻለ ህብረቱ ሲጠቁም በ 2023 በኢትዮጵያ በግጭትና በድርቅ የተጎዱ ሰዎችን ለመደገፍ 82.5 ሚሊዮን ዩሮ ለኢትዮጵያ መስጠቱን የአውሮፓ ህብረት አስታውሷል።
በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ባወጣው መረጃ ፥ በኢትዮጵያ ከጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአፋር፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልል (CER) ፣ በሐረሪ፣ በሲዳማ፣ በሶማሌ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል (SER) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በ85 ወረዳዎች ከ24,700 በላይ ሰዎች የኮሌራ በሽታ እንደተገኘባቸው ተመዝግቧል።

በጎንደር፥ ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለ ሰዎች በመድኃኒት እጦት ለችግር ተዳርገዋል ተባለ።
በጎንደር ከተማ 1ሺ 687 በላይ አባላት ያሏቸው ከኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረሰ ጋር የሚኖሩ ሰባት ማኅበራት ሲኖሩ፤ የበጎ አድራጎት ተቋማት የሚያደርጉት የገንዘብ፣ የመድሃኒትና የቁሳቁስ ድጋፍ በመቀነሱ ምክንያት ማኅበራቱ ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን ሰምተናል።
በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ወቅታዊ የሰላም እጦት ምክንያት በቂ የማራዘሚያ መድኃኒትና የኮንደም አቅርቦት በብቃት እየቀረበ ባለመሆኑ መቸገራቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የማኅበራቱ አባላት ተናግረዋል፡፡
ከማኅበራቱ አባላት መካከል የፍሬ ህይወት በጎ አድራጎት ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ወርቁ ጎበዜ፥ አባላቱ ከዚህ ቀደም ለ2 ወራት ያገኙት የነበረው የፀረ-ኤች አይቪ ቫይረስ መድኃኒት በአቅርቦት ችግር ምክንያት አሁን በግማሽ ቀንሶ ለ1 ወር ብቻ እንዲያገኙ እየተገደዱ ነው ብለዋል።
መድኃኒቱን የሚያቋርጡ ሰዎች ለሞት እየተዳረጉ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ፤ የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጓዳኝ በሽታዎች መድኃኒት ሆስፒታል ላይ አለመገኘቱና መድኃኒቶች ከሆስፒታል ውጭ ላይ ሲገኙ ደግሞ ዋጋቸው ውድ በመሆኑ ለመጠቀም እየተቸገሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ለማኅበራቱ በቂ የኮንዶም ስርጭት የለም ያሉት አቶ ወርቁ፤ "በተለይ የማኅበሩ አባላት ኮንዶም ስለማይደርሳቸውና በቂ የገቢ ምንጭ ስለሌላቸው ከዚህ ጋር ተያይዞ ኑሯቸውን ለመደጎም ሴተኛ አዳሪነትን እንደ አማራጭ የሚመለከቱ መኖራቸው ለቫይረሱ ሥርጭት መስፋፋት ሰፊ በር ከፍቷል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከማኅበራት አባላት መካከል የወጋገን የሴቶች ማህበር አባል ወይዘሮ ከበቡሽ ውለታው ደግሞ የማኅበሩ አባላት የመከላከያ ኮንዶም ባለመጠቀማቸው ከኤች አይቪ ነፃ የሆነ ሕፃን ለመውለድ የተጀመረውን ሥራ ፈታኝ እንዳደረገው ያነሳሉ።
የማኅበራቱ አባላት ያለባቸውን ማኅበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከገጠር ወረዳዎችና ከተሞች ራሳቸውን እያጋለጡ የፀረ-ኤች አይቪ መድሃኒት እንዲጠቀሙ እየተደረገ ያለው ጥረት በመድኃኒቱ እጥረት ምክንያት አገልግሎቱን ማቋረጣቸውንም ተናግረዋል፡፡
በኮቪድና በወቅታዊ የሰላም ችግር ምክንያት ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑን የሚያነሱት በጎንደር ከተማ ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከታተልና መቆጣጠርና ግምገማ የስራ ሂደት አስተባባሪ ሲስተር ዘነበወርቅ ንጋቱ፥ የፀረ-ኤች አይ ቪ መድኃኒትና የኮንዶም አቅርቦት ችግር በከተማዋ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡
በቂ የኮንዶም ስር ጭትና የፀረ- ኤች አይ ቪ መድሃኒት ባለመኖሩ በርካታ ሰዎች በከተማዋ ለችግርና ለሞት እየተጋለጡ መሆኑንም ነው የጠቀሱት፡፡
ኤች.አይ.ቪ በኢትዮጵያ፣ በአዲስ መልክ እየተስፋፋ መሆኑ ሲነገር ቫይረሱ በፍጥነት እየተሠራጨ ካሉባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የአማራ ክልል መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ሳቢያ በክልሉ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መድኃኒት ሲወስዱ የነበሩ 65ሺሕ ሰዎች መድኃኒታቸውን ማቋረጣቸው መነገሩ ይታወሳል። አሁን ላይ ያለው የሰላም እጦትም ችግሩን ያባብሰዋል ተብሏል።
መረጃው የተዘጋጀው በጎንደር የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው፡፡

ከስደት ተመላሾች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (NIDP) እና የአለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ከስደት የሚመለሱ ዜጎችን በባዮሜትሪክስ ላይ በተመሠረተው ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ለማድረግ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ፥ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሰላም ህብረተሰቡን እንዲቀላቀሉ ከማስቻሉም በላይ ቀጣይነት ያለው የመልሶ ማቋቋም ስራን ለመስራት የሚያግዝ ነው ተብሏል።
የሁለቱ ወገኖች ጥምረት ከስደት የሚመለሱ ዜጎችን መመዝገብ፣ ማንነታቸውን የማጣራትና የማረጋገጥ ሲሆን ስምምነቱ በአገር ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮችን የመመዝገብ ሂደት ላይ እንዲተባበሩ ጭምር የሚያስችላቸውም እንደሆነ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የIOM ዋና ኃላፊ አቢባቱ ዋኒ ስደተኞች ማንነታቸውን የሚገልፅ ሰነድና ማስረጃ ባለመኖሩ ምክንያት መሰረታዊ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን እንዲሁም አስፈላጊ ጥቅሞችን ለማግኘት መቸገራቸውን አንስተው ይህ አጋርነት ለስደተኞች፣ በሀገር ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎችና ለተጎዱ ማህበረሰቦች ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው ብለዋል።
IOM ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ከጅቡቲ፣ ሊባኖስ፣ ከሳዑዲ አረቢያ ና የመን የተመለሱ ከ1,000 በላይ ስደተኞችን ለዲጂታል መታወቂያ እንዲመዘገቡ ማመቻቸቱ ሲገለፅ መታወቂያው ወደ ማህበረሰባቸው ሲቀላቀሉ አስፈላጊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ይረዳቸዋል ተብሏል።
ኢትዮጵያ በ2026 ስደተኞችና የሀገር ውስጥ ለተፈፈናቃዮችን ጨምሮ ለ90 ሚሊዮን ዜጎች እና ነዋሪዎች ዲጂታል መታወቂያዎችን ለመስጠት መታቀዱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (NIDP) ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ተናግረዋል።

#Update: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ገልጿል። ባንኩ በዘንድሮው በጀት ዓመት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የክፍያ ማስተካከያ ማድረጉ ሲገለፅ ከአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ነፃ የተደረጉ አገልግሎቶች መኖራቸውንም አሳውቋል። በዚህ መሰረት ደንበኞች በመደበኛ መንገድ ከአካውንት ወደ አካውንት ገንዘብ ሲያስትላልፉ የሚቆረጠው የአገልግሎት ክፍያ፦ - ገንዘቡ ከ 1ብር…
#Update : የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያው ላይ በድጋሜ ማስተካከያ ማድረጉን ገለጸ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያዎቹ ላይ በድጋሜ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። ማሻሻያው ባንኩ ከደንበኞቹ አገኘውት ባለው ግብረ መልስ መሰረት የተደረገ መሆኑን ነው የገለጸው።
በዚህም፦
- #በወዲአህ በተከፈቱ ሂሳቦች በቅርንጫፍም ሆነ በሞባይል ባንኪንግ የሚደረግ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አግልግሎት ከክፍያ ነፃ ሆነዋል፤
- #በሙዳራባህ ውል የተከፈቱና እና ለረጅም ጊዜ ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦች (Inactive Accounts) ከክፍያ ሆነዋል።
- በቅርንጫፍ የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል
• ከብር 1 እስከ 10,000 = 5 ብር
• ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 = 10 ብር
• ከብር 100,001 በላይ = 10 ብር ሲደመር በእያንዳንዱ 100 ሺ 5 ብር (ከ100 ብር ያልበለጠ) ሆኗል።
- በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ወደ ሌላ ባንክ ወደሚገኝ ሂሳብ ገንዘብ ለማስተላለፍ ( #RTGS ) 50 ብር የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፤
- ከ P2P የገንዘብ ዝውውር በ ኢትስዊች (ETSWITCH) 5 ብር እና የኢትስዊች ክፍያን በመደመር የአገልግሎት ክፍያ ይከፈልበታል፤
- ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ ከ50 ብር በታች ለማስገባት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ የለም፤
- በሲቢኢ ብር በቀን ከ3 ጊዜ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ሲኖር ገንዘብ የማስገባት አገልግሎት እንደሚከተለው የአገልግሎት ክፍያ ይታሰብበታል፡
• ከብር 50 በታች = ነፃ
• ከብር 51 እስከ ብር 500 = 6.45 ብር
• ከብር 501 እስከ ብር 2,000 = 7.60 ብር
• ከብር 2,001 እስከ ብር 3,000 = 8.18 ብር
• ከብር 3,001 እስከ ብር 4,000 = 9.33 ብር
• ከብር 4,001 እስከ ብር 5,000 = 10.48 ብር
• ከብር 5,001 እስከ ብር 6,000 = 11.63 ብር
• ከብር 6,001 በላይ ከሆነ ከሚገባው ገንዘብ 0.2 በመቶ እንዲሆን መወሰኑን ባንኩ አስታውቋል።

#PuratosEthiopia
ፑራቶስ ኢትዮጵያ ፉድ ኢንዱስትሪ አ.ማ በዓለምአቀፍ ደረጃ የዳቦ ፣ የኬክ እና ቸኮሌት ግብዓቶችን ከ100 በላይ በሆኑ ሀገራት በማቅረብ የሚታወቀው ‘ፑራቶስ ግሩፕ’ አካል ነው።
የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ላይ የሚኖር የገበያ ፍላጎትን ለማርካት እንዲቻል ከሶስት ዓመት በፊት ሀገራችን ኢትይጵያ የተቋቋመው ይህ አምራች ድርጅት በቅርቡ አዳዲስ ምርቶችን ለገበያው አስተዋውቋል።
ኩባንያው ለደንበኞቹ ያስተዋወቃቸው ምርቶች ከዚህ በፊት እያመረተ ሲያከፋፍል ከቆያቸው እንደ ዲያና ዊፒንግ ክሬም (ሻንቲ) ፣ ሱፐር ጋቶ ፣ ሚክሶ ፣ አይስክሬም ፓውደር ፣ ሹገር ፔስት ፣ በስትሮበሪ በቸኮሌት እና በካራሜል ጣዕም የሚመረቱ ኮልድ ግሌዞች እና ቶፒንጎች ላይ ተጨማሪ ሆነው ለዳቦ ቤቶች ፣ ለኬክ ቤቶች እና ሆቴሎች የሚቀርቡ ይሆናል።
የኩባንያው አዳዲስ ምርቶች 3 ሲሆኑ እነዚህም:-
1. ፓንቴራ የዳቦ ማሻሻያ
አምራቾች የሚያመርቱትን ዳቦ የጥራት ደረጃ እና መጠን ከፍ የማድረግ አቅም ያለው
2. ኦሊክስ የፓትራ ቅባት
አምራቾች የመጋገሪያ ፓትራቸውን በቀላሉ ለመቀባት እና ስራቸውን ለመከወን የሚያስችል።
3. ሬድ ቬልቬት ኬክ ሚክስ
የሚክስድ ቤሪ ቃና (Mixed Berry Flavor) ያለው በአይነቱ ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነ ያለቀለት የኬክ ፓውደር።
ተጨማሪ መረጃ የሚፈልግ ከዚህ በታች ባለው አድራሻ ኩባንያውን ማግኘት ይችላል።
09-75-12-25-75
www.puratos-ethiopia.com
🔗 Instagram 🔗 TikTok 🔗 Facbook
(Advertorial )