TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
293 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
የ15ዓመቱ ህፃን ጓደኛውን "ከዛፉ ጋር እጇን አስሬ አንቄ ገድያታለሁ" ቢልም ቤተሰቦቿ አሁንም ፍለጋ ላይ ናቸው።

ከላይ በምስሉ የምትመለከቷት የ14 ዓመት ታዳጊ ዊንታ አስመሮም ትባላለች። በትምህርቷ ጎበዝ፣ በጓደኞቿ የምትወደድ ለእናትና አባቷ የመጀመሪያ ልጅ ስትሆን የስካውትም አባልና አሰልጣኝ ነበረች።

እሁድ ግንቦት13  ላንቻ ከሚገኘው ቤታቸው ጠዋት 1:00ሰዓት አካባቢ ወደ አደይ አበባ ት/ቤት ትሄዳለች፤ እንደተለመደው እስከ 4:00ሰዓት የስካውት ስልጠና ለተማሪ ጓደኞቿ ከሰጠች በኋላ ከት/ቤት ብትወጣትም ወደ ቤት ሳትመለስ የት እንደሄደችም ሳይታወቅ ለቀናት ደብዛዋ ይጠፋል።

እናትና አባት ወዳጅ ጎረቤት ለፍለጋ ቢሰማሩም አየናት የሚል ሰው ያጣሉ። ቤተሰብ ሲጨንቀው የቅርብ ጓደኛዋ ነው የተባለ አንድ ተማሪ ህፃን ልጅ ሲጠይቁት "እኔ አላውቅም ግን ከጠፋች በኋላ በቴሌግራም እንዳወራትና ደህና እንደሆነች ነግሮና አረጋግቶ የተፃፃፉትንም መልዕክት ያሳያቸዋል።

ከቀናት በኋላ ግን ቤተሰብ ስለተጠራጠረና በጣም ስለተጨነቀ ፖሊስ ይዘው በመሄድ እንደገና ተማሪው ጓደኛዋን አጥብቀው ይጠይቁታል።

ለመጨረሻ ጊዜ ከሱ ጋር እንደነበረችና አንድ ወጣት አስፈራርቶ እንደወሰዳት ልጁም እጁ ላይ ንቅሳት ያለበት እንደሆነ ምልክቱን ተናግሮ ቤተሰብ ከፖሊስ ጋር ሆኖ እንደገና ዊንታን ፍለጋ ይጀምራል፤ ግን "እዚህ አየናት"የሚል ሰው ይጠፋል።

የ15 ዓመቱ ህፃን ተማሪ በፖሊስ ቁጥጥር ውስጥ ሆኖ እንደገና ምርመራ ሲደረግበት "የስካውት አባላት ተማሪዎች ልብስ የሚያሰሩበትን የተሰበሰበ ገንዘብ ዊንታ ጋር እንደነበር ያስረዳል።

ያንን ብር ስለተቀበላት ብሩን መልስ እንዳትለው፤ እሁድ አሰልጥና ስትወጣ ደውሎ ቀጥሯት እጇን ከዛፉ ጋር አስሮ በስካርቭ አንቆ እንደገደላት በማግስቱም ቦታው ላይ ተመልሶ ሲሄድ ማስኳንና ሹራቧን ብቻ እንዳየ ይናገራል። በቴሌግራም ተፃፃፍን ብሎ ያሳያቸውም ሁለቱም ስልክ እሱ ጋር ስለሆነ በሁለቱም ፅፌ ነው ይላቸዋል።

ቤተሰብና ፖሊስ ወዲያውኑ ቦታው ላይ ሲደርሱ ለብሳው የነበረ ሹራቧንና ማህተቧን (ከነመስቅሏ) መሬት ላይ ያገኙታል። እናትና አባት ልባቸው ቆስሎ ወዳጅ ጎረቤት መሞቷን አምኖ "ዊንታዬ ብለው እያነቡ ጥቁር ለብሰው ለቅሶ ተቀመጡ። ፖሊስም መሬት ላይ የነበረውንም ትንሽ አጥንት ሰብስበው ይዘው ሄደው ለምርመራ ሰጡ።

ቤተሰብ ተስፋ ቆርጦ ለቅሶ ከተቀመጡ ከ3ቀናት በኋላ ፖሊስ የምርመራው ውጤት እንደደረሰና "አጥንቶቹ የእንስሳት እንጂ የሷ እንዳልሆነ" ተናገሩ። በአነፍናፊ ውሻ ቢፈለግም ምንም አይነት የመሞቷ ማስረጃ ቦታው ላይ ይታጣል።

እናትና አባት ሀዘኑን ረገብ አድርገው ልጃቸውን ፍለጋ በተስፋ እንደገና መንከራተት ጀመሩ፤ አንዴ "ለሰው ሰጠኋት አንዴ ገድያታለሁ" የሚለው ህፃን ተማሪ ጓደኛዋ፥ በፖሊስ ቁጥጥር ውስጥ ሆኖ ምርመራ ላይ ቢሆንም የአይን ማረፊያ ልጃቸውን ያጡት እናትና አባት "በህይወት እናገኛታለን"በሚል ተስፋ ሀዘናቸውን ዋጥ አድርገው በፀሎትና ልመና 16ቀናት ዊንታን ፍለጋ ላይ ናቸው።

ከገደላትስ አስክሬኗን የት አደረገው?

ለፈላጊ ቤተሰቦቿ ጥቆማ ለመስጠት፦

0911873116 - አስመሮም                       
0980441768 - ዛፋ                          
0911760048 - ሚካኤል

(መረጃው ከባይሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት ማኅበር ገጽ የተገኘ ነው።)

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሰኔ 5 እንገናኝ!

• የኤልቬት የ2015 ክረምት የመጀመሪያ ዙር ተመዝጋቢዎቻችችን ሰኔ 5 ስልጠናቸውን ያጀምራሉ!

• አሁንም አልረፈደም፤ እስከ ሰኔ 3 ድረስ በሚፈልጉት ክህሎት ተመዝግበው የመጀመረያ ዙር ሰልጣኝ ይሁኑ።

• ከኤልቬት ጋር ሰልጥነው ፣ በሰለጠኑበት ይሠራሉ!

በተመጣጣኝ ክፍያ፣ በብቁ መምህራን የሚሰጡ የተለያዩ የዲጂታል ክህሎቶች ከኤልቬት የስልጠና ማዕከል!

የስልጠና ማዕከል አድራሻ፡
መገናኛ (ከዘፍመሽ ወደ ሾላ ገበያ በሚወስደው መንገድ፣ ከግሬስ ሲቲ ሞል ቀጥሎ፣ ሲሳይ ፕላዛ 3ኛ ፎቅ)
https://maps.app.goo.gl/hzjnfoGPKx2eu1d76

ለበለጠ መረጃ፡ @elev8_Support
ወይም: +2519 67 00 67 83
#HIV_AIDS 🇪🇹

በ2015 በጀት ዓመት 11ሺህ ወገኖች  በኤች አይ ሺ ኤድስ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተገልጿል። በተጨማሪም 8 ሺህ 300 ሰዎች አዲስ በኤች አይሺ መያዛቸውን፣ ከነዚህም ውስጥ 69 በመቶዎቹ ከ15 እስከ 30 አመት የእድሜ ክልል ላይ ያሉ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጄነራል ይልማ መርዳሳ አቶ ግርማ ዋቄን በመተካት የኢዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።

የኢትዮጵያ አየር ሀይል አዛዥ ጀነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል።

ጀነራል ይልማ መርዳሳ “የአፍሪካ አቪዬሽን ኢንደስትሪ አባት” በመባል የሚታወቁት አቶ ግርማ ዋቄን በመተካት ነው የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙት፡፡

ጀነራል ይልማ መርዳሳ የቦርድ ሰብሳቢ ከመሆናቸው በፊት ባላፉት ሁለት ዓመታት የአየር መንገዱ ቦርድ አባል ነበሩ፡፡

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሴኩሪቲ ካሜራ ሽያጭና ነፃ ገጠማ
0911284606
security camera CCTV (ባለ 4 አና ባ 8 ካሜራ)
ለቤትዎ፤ ለድርጅት፤ ለሱቅ፤ ለፋርማሲ፤ ለዳቦ ቤት፤ ለቡቲክ፤ ለህንጻዎ ፤ ለመጋዘንዎ አና ለንብረትዎ የአመታት ልምድ ባለው ድርጅታችን ሴኩሪቲ ካሜራ ያስገጠሙ
-4 ካሜራዎች
-4 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች  35,000 ብር
-8 ካሜራዎች
-8 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች 50,000 ብር
በአንበሳ ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት አውቶብሶች ተቃጠሉ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በትላንትናው ዕለት በአንበሳ አዉቶቢስ የተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥና የነዳጅ መቅጃ ማዕከል ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት አዉቶቢሶች መቃጠላቸው ተገልጿል።

የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ እንደሚያመለክተው የተቃጠሉት አዉቶቢሶች ከቅጥር ጊቢ ዉጭ ቆመዉ የነበሩ መሆናቸው የገለጸ ሲሆን በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም አስታውቋል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሰላሳ አንድ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተዋል ተብሏል።

የእሳት አደጋዉ ወደ ነዳጅ ታንከርና ጋራዡ  ላይ ተሳፋፍቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉንና የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠርም 1:30 ሰዓት መፍጀቱን ኮሚሽኑ ገልጿል።

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በዘንድሮ የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ምን ለውጦች ተደረጉ?

በጅቡቲ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የመሪዎች ጉባኤ ከ57 ዓመታት በፊት የተመሰረተበትን ስምምነት በአዲስ ተክቷል።

በአዲሱ ስምምነት መሰረት ከአሁን በኋላ፤ አባል ሀገራት የኢጋድ ሊቀመንበርነትን ይዘው የሚቆዩት ለአንድ ዓመት ብቻ ይሆናል። አባል ሀገራቱ  የሊቀመንበርነቱ ስልጣን በዙር የሚደርሳቸው እንደ ስማቸው ቅደም ተከተል እንደሚሆንም ተገልጿል።

የአምስት ሀገራት መሪዎች በተሳተፉበት በዚህ ጉባኤ የዋና ጸሀፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን የስራ ዘመን ለተጨማሪ አራት ዓመታት አራዝሟል። ዶ/ር ወርቅነህ ኬንያዊውን ማህቡብ ማሊምን በመተካት የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ሆነው የተሾሙት በህዳር 2012 ዓ.ም ነበር።

በጉባኤው ላለፉት አራት ዓመታት ኢጋድን በሊቀመንበርነት ስትመራ የቆየችው ሱዳን ኃላፊነቱን ለጅቡቲ አስረክባለች። ኢትዮጵያ ይህን የኃላፊነት ቦታ ለሱዳን አሳልፋ ከመስጠቷ በፊት ለዘጠኝ ዓመታት ኢጋድን በሊቀመንበርነት መምራቷ ይታወሳል። 

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኦስማን ሳለህን አማካኝነት በጉባኤው የተሳተፈችው ኤርትራ፤ በዛሬው የጅቡቲ ጉባኤ ከ16 ዓመታት በኋላ የኢጋድ አባልነት እንቅስቃሴዋን በይፋ እንደጀመረች የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል። 

በእንደዚህ አይነት ጉባኤዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በኮቪድ 19 በመያዛቸው ምክንያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኦዲንጎ ጄጄ አቡባካር ኡጋንዳን ወክለው ተገኝተዋል።

ዋና መቀመጫውን በጅቡቲ ያደረገው ኢጋድ፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስምንት አባል ሀገራት አሉት። ጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን እና ኡጋንዳ የክፍለ አህጉራዊው ድርጅት አባል ሀገራት ናቸው።

Credit : Ethiopia Insider, 📸 IGAD Secretariat

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-MAGAZINE
#HIV_AIDS 🇪🇹 በ2015 በጀት ዓመት 11ሺህ ወገኖች  በኤች አይ ሺ ኤድስ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተገልጿል። በተጨማሪም 8 ሺህ 300 ሰዎች አዲስ በኤች አይሺ መያዛቸውን፣ ከነዚህም ውስጥ 69 በመቶዎቹ ከ15 እስከ 30 አመት የእድሜ ክልል ላይ ያሉ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። t.me/tikvahethmagazine
አሜሪካ፣ በኢትዮጵያ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመቆጣጠር 112 ሚሊዮን ዶላር መመደቧን አስታወቀች።

አሜሪካ፣ በኢትዮጵያ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመቆጣጠር የሚያስችል፣ ተጨማሪ 112 ሚሊዮን ዶላር (ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ) መመደቧን አስታውቃለች።

ድጋፉ በተለይ በወጣቶች ዘንድ፣ በፍጥነት እየተዛመተ ያለውን ኤችአይ.ቪን፣ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር አንደሚያግዝ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

በጤና ሚኒስቴር የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፈቃዱ ያደታ፣ ኤች.አይ.ቪ በኢትዮጵያ፣ በዐዲስ መልክ በመሠራጨት ላይ እንደኾነ ከቪኦኤ አማርኛው ክፍል ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

የትግራይ ክልልን መነሻ አድርጎ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሔደውን ጦርነት ጨምሮ በሀገሪቱ የተከሠቱ ግጭቶች፣ የኤች.አይ.ቪን መስፋፋት በመከላከል እና በመቆጣጠር እንቅስቃሴ ላይ፣ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ነው የገለጹት።

በዐማራ ክልል፣ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መድኃኒት ሲወስዱ የነበሩ 65ሺሕ ሰዎች፣ በጦርነቱ የተነሣ መድኃኒታቸውን ማቋረጣቸውን፤ በትግራይ ክልልም ከጦርነቱ በፊት የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት ተጠቃሚ ከነበሩ ከ46 ሺሕ በላይ ሰዎች መካከል 13 ሺሕ የሚኾኑቱ፣ የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ቪኦኤ በዘገባው ተመላክቷል።

ቫይረሱ በፍጥነት እየተሠራጨ ካሉባቸው አካባቢዎች መካከል፣ የጋምቤላ እና የዐማራ ክልሎች እና የዐዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀዳሚነት ተጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ አሁን ወቅት፣ ከ610 ሺሕ በላይ ዜጎች ከቫይረሱ ጋራ እንደሚኖሩ፣ ከ500 ሺሕ በላይ የሚኾኑቱ ደግሞ ከቫይረሱ ጋራ እንደሚኖሩ አውቀው መድኃኒት በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#SamiTech
ታላቅ ቅናሽ!!
https://yangx.top/samcomptech

ላፕቶፕ ለመግዛት አስበዋል ? እንግዲያዉስ ስለላፕቶፕ በቂ ገለፃ እና ማብራርያ ልንሰጥዎት እንዲሁም የሚፈልጉትን ላፕቶፕ በጥሩ ዋጋ አቅርበንሎታልን !

ላፕቶፕ ከትዉልድ ትዉልድ ( from generation to generation) ይለያያል ስንል ምን ማለታችን ነዉ ? የዚች ቻናላችን አባል ይሁኑና ይደዉሉ! በሰፊዉ እንወያይበታለን : https://yangx.top/samcomptech

አዳዲስ ላፕቶፕ ለአጭር ጊዜ በሚቆይ  ታላቅ ቅናሽ ፤ ከአንድ አመት ዋስትና እና  ከመልካም መስተንግዶ ጋር ያገኛሉ።

ለድርጅቶች እና በብዛት ለሚወስዱ ደንበኞች በማይታመን ቅናሽ ባሉበት ቦታ እናደርሳለን !!

ስልክ ፦ 0928442662
             0940141114

https://yangx.top/samcomptech
በፋርም አፍሪካ የተዘጋጀ የዶሮ እርባታ ስልጠና

• ለአዲስ ስራ ጀማሪዎች በሙሉ ፤ እስከ ሰኔ 7 ድረስ ተመዝግበው በዶሮ እርባታ  ይሰልጥኑ።
• ከፋርም አፍሪካ ጋር ሰልጥነው ፣ በሰለጠኑበት ይሠራሉ!
. ከስልጠና ቡኋላ ወደ ስራ ሲገቡ ነፃ የማማከር እና ክትትል ያገኛሉ

በተመጣጣኝ ክፍያ፣ በብቁ ዶክተር አሰልጣኞች የሚሰጡ የተለያዩ የእርባታ ስልጠናዎች ከፋርም አፍሪካ የስልጠና ማዕከል!

አድራሻ፡
ከእንግሊዝ ኤምባሲ ወደ ምስራቅ አጠቃላይ በሚወስደው መንገድ ላይ ንግድ ባንክ ያለበት ህንጻ ላይ 3ኛ ፎቅ

https://yangx.top/farm_africa
https://yangx.top/farm_africa

ለበለጠ መረጃ፡
ወይም: +2519 68 99 99 93
+251 972342651
ፎቶ📸: የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በሚዛን ማረሚያ ተቋም በመታረም ላይ ያሉ የህግ ታራሚዎችን አዲስ ወደተዘጋጀው ማረሚያ እንዲገቡ ማድረጉን አስታውቋል።

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በ50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባ የመጀመሪያው ዓለምአቀፍ የግል ዳታ ማዕከል ተመረቀ።

ዊንጉ አፍሪካ በአዲስ አበባ የአይቲ ፓርክ ኮርፓሬሽን (Et- IT Park) ውስጥ በሚገኝ 15000 ካ.ሜ ላይ በ50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የገነባውን ዳታ ማዕከል አስመርቋል።

ግንባታውን ለማጠናቀቅ 24 ወራት የፈጀው ይኸው የዳታ ማዕከል የኢትዮ ቴሌኮም፣ ሳፋሪኮምን የኢንተርኔት ማዕከል በጋራ የሚጠቀም ፈጣንና አስተማማኝ የመረጃ ቋት ነው ተብሏል።

“ኤፍ ዲ አይ ኢንተለጀንስ” በቅርቡ ባካሄደው ጥናት፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዳታ ማዕከል ግንባታ ዘርፍ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ  ከዓለም 2ኛ ደረጃን መያዟ መዘገቡ ይታወሳል።

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በሳይንሳዊ መንገድ አዘጋጀው ያላቸውን 3 መድኃኒቶች፤ በሰዎች ላይ እንደሚሞክር ገለጸ።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የባህል መድኃኒቶችን በሳይንሳዊ መንገድ እያዘጋጀ መሆኑንና በተያዘው ዓመት በሳይንሳዊ መንገድ የተቀመሙ ሦስት የባህል መድኃኒቶች በሰዎች ላይ እንደሚሞከር አስታውቋል።

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ንጉስ ታደሰ የአንኮበር ቤተ መንግሥት የሚገኝበት አከባቢ በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች ሊባል በሚችል መልኩ ለመድኃኒት ቅመማ የሚውሉ ዕፅዋት የሚገኙበት ሥፍራ እንደሆነ መለየቱን ጠቁመዋል።

ዩኒቨርሲቲው፥ የዕፅዋቱን ቅመማ እና መድኃኒትነት የሚያውቁ ረጅም ዕድሜ ያላቸው አባቶች እና እናቶች አሁንም በአካባቢው መኖራቸውን እንደ ዕድል በመጠቀም አብሮ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። 

የባሕላዊ መድኃኒቶችን የአቀማመም ሥልት በማጥናት ሳይንስ በሚቀበለው መልኩ ለማድረግ የተለያዩ ምርምሮች እየተሠሩ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤  በርካታ መድኃኒቶች በቅመማ እና በሙከራ ደረጃ እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

በአይጦች እና በሌሎች ከሰው ጋር ተመሳሳይ የሰውነት ሥርዓት ባላቸው እንስሳት ላይ ሙከራቸው ተጠናቆ በሰው ላይ ሊሞከሩ የተዘጋጁ ሦስት መድኃኒቶች በያዝነው ዓመት ሙከራቸው ይጠናቀቃልም ብለዋል።

መድኃኒቶቹ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሙከራ ደረጃዎችን ሲያጠናቅቁ ወደ ምርት እንደሚገቡ የተገለጸ ሲሆን ለምን በሽታ መድኃኒትነት የተዘጋጁ እንደሆኑ በዘገባው አልተጠቀሰም።

t.me/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አምስተኛ (5ኛ) ዙር የዶሮ እርባታ ስልጠና

ለክቡራን ደንበኞቻችን የአምስተኛ(5ኛ)  ዙር የዶሮ እርባታ ስልጠና ከሰኔ 12-14/2015 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ሙሉ ቀናት ስለሚሰጥ ፍላጎቱ ያላችው እና ወደ እርባታ ውስጥ መግባት የምትፈልጉ ከዚህ በታች ያለውን ማስንፈጠርያ በመንካት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

https://forms.gle/5Kua3e5LChxtiYe67

የስልጠና ቦታ፡ አዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ( ሲኤምሲ)

ክፍያ፡ 1300 ETB (መመዝገቢያ፡ ስልጠና፣ ማንዋል እና የሶስት ቀን ሻይ ቡና (Refreshment ) አካቶ።)

ማስታወሻ፦ ያሉን ቦታዎች ውስን በመሆናቸው ቅድሚያ ተመዝግቦ ክፍያውን  ላጠናቀቀ ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን በታላቅ አክብሮት መግለፅ እንወዳለን፡፡

ለበለጠ መረጃ
ስልክ፡ 0116677008 / 0114304747
ቴሌግራምhttps://yangx.top/trustagroconsult
#SamiTech
ታላቅ ቅናሽ!!
https://yangx.top/samcomptech

ላፕቶፕ ለመግዛት አስበዋል ? እንግዲያዉስ ስለላፕቶፕ በቂ ገለፃ እና ማብራርያ ልንሰጥዎት እንዲሁም የሚፈልጉትን ላፕቶፕ በጥሩ ዋጋ አቅርበንሎታልን !

ላፕቶፕ ከትዉልድ ትዉልድ ( from generation to generation) ይለያያል ስንል ምን ማለታችን ነዉ ? የዚች ቻናላችን አባል ይሁኑና ይደዉሉ! በሰፊዉ እንወያይበታለን : https://yangx.top/samcomptech

አዳዲስ ላፕቶፕ ለአጭር ጊዜ በሚቆይ  ታላቅ ቅናሽ ፤ ከአንድ አመት ዋስትና እና  ከመልካም መስተንግዶ ጋር ያገኛሉ።

ለድርጅቶች እና በብዛት ለሚወስዱ ደንበኞች በማይታመን ቅናሽ ባሉበት ቦታ እናደርሳለን !!

ስልክ ፦ 0928442662
             0940141114

https://yangx.top/samcomptech