የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፲ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ዛሬ ተከብሯል።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትን 10ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከብሯል።
በትላንትናው ዕለትም ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በማስመልከት ዜና መዋዕል ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክና ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የተሰኙ መጽሐፍት ተመርቀዋል።
መጽሐፍቱ የቅዱስነታቸውን የሕይወት ታሪክ፣ ባለፉት ፲ ዓመታት በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ሥራዎችን፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን፣ ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ፲ ዓመታት በስኬት ያከናወነቻቸው ዋና ዋና ተግባራት እና የገጠሟትን ተግዳሮቶች ተከትሎ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተላለፉ መልዕክታትን አጠቃሎ የያዘ መሆኑ ተገልጿል።
መጻሕፍቱን በውጪው ዓለም የሚገኙ ምዕመናን በቀላሉ አግኝተው ማንበብ ይችሉ ዘንድም በቤተ ክርስቲያን ድረ ገጽ https://www.eotceth.org ላይ እንዲጫን መደረጉን የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል።
ፎቶ: ተሚማ
@tikvahethmagazine

የቅን ልቦች ለትግራይ ክልል በጦርነቱ ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ አደረገ።
የቅን ልቦች በጎ ሥራ ድርጅት በትግራይ ክልል በጦርነቱ ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ ለማድረግ ያሰባሰበውን ቀሳቁስ መቀሌ በማድረስ አስረክቧል።
ማኅበሩ ያሰባሰባቸው የድጋፍ አይነቶች፦
- የሴቶች የንህፅና መጠበቂያ 15 ኩንታል፤
- አልባሳት 25 ቦንዳ
- 22 ዊልቸር
- የ2.2 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና መድኃኒቶች ናቸው።
በተጨማሪም ለጎዳና ተዳዳሪዎች ቁርስ ማብላት ስራን ከኬራዲዮን የአረጋዊያን እና ህፃናት መርጃ እና ቪዥን ፎር አክሽን ጋር በጋራ በመሆን በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ አድርገዋል።
አጠቃላይ ማኅበሩ ያሰባሰበው ድጋፍ የ5.6 ሚሊየን ብር የሚገመት መሆኑን የማኅበሩ መስራችና ፕረዘዳንት ተስፋዬ ስንሻ ለቲክቫህ ገልጸዋል። መንግስት እና የሲቪክ ማኅበራት የትግራይ ክልል በጦርነቱ የተጎዱትን ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

መቄዶንያ የ1 ሚልዮን ዶላር ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ማዘጋጀቱን ገለጸ።
መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በጅምር ላይ ያለውን ህንጻ በማጠናቀቅ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ የ1 ሚልዮን ዶላር ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ማዘጋጀቱን የማእከሉ መስራች የክብር ዶክተር ቢንያም ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል።
በመግለጫው እሁድ የካቲት 26 ከቀኑ 9 ሰአት ጀምሮ በኮሜድያን እሸቱ አማካኝነት በዶንኪ ትዩብ በቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የገቢ ማሰባሰቢያው ዋና አላማ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን ህንጻ በርና መስኮት ለመግጠም ከሚያስፈልገው 3.5 ሚልዮን ዶላር ላይ 1ሚልዮን ዶላር ለመሰብሰብና ህንጻውን በማጠናቀቅ ማዕከሉ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት አድማሱን በማስፋት ለብዙኃን መድረስ መሆኑ ተነግሯል።
ከ2.3 ቢልዮን ብር በላይ የሚፈጀው G+12 ዘመናዊ ሆስፒታልና የአረጋውያን መኖሪያ ህንጻ በተጀመረ በ3 ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ግንባታው 70% መጠናቀቁ ተገልጻል።
ከ7,500 በላይ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን በውስጡ በመያዝ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ማዕከሉ በቀጣይ 20 ሺህ ለማድረስ የታቀደ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በቀን አንድ ሚልዮን ብር ወጪ እንዳለው በመጠቆም በዕለቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ተጠይቋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው የኦሞራቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድጋይ አስቀመጡ።
የግንባታው አጠቃላይ ወጪ 20 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን ወጪው ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ-ሠናይ ድርጅት እንደሚሸፈን ተገልጿል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ከ1 ዓመት እስከ 2 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደምጠበቅም በመርሃ ግብሩ ተጠቅሷል። (ENA)

የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና ጥቆማ መስጫ ሶፍትዌር ይፋ አደረገ
በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የበለፀገው የሙስና ጥቆማ መስጫ ሶፍትዌር በፌደራል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳር መካከል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።
በ5 ሀገርኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋ 24 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጥ የተነገረለት ይህ አገልግሎት ለአይነ ሥውራን ዜጎች ምቹ በሆነ መልኩ በድምጽ ታግዘው አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ተደርጎ መሰራቱ ተብራርቷል።
ሶፍትዌሩ “የሕዝብ አስተያየት መቀበያ ሲስተም "Public Feedback System” የሚል መጠሪያ ስያሜ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፤ ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል የሶፍትዌሩን ዌብሳይት አድራሻ https://epfs.gov.et በመጠቀም አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መንግስት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለው ገደብ እንዲነሳ ተጠየቀ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ስራቸውን በአግባቡ ለህዝቡ ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት እየፈጠረ በመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ መጠየቁን ለቲክቫ በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡
ከሰሞኑን መንግስት በአንዳንድ የኢንተርኔት የግንኙነት መተግበሪያዎች ላይ የጣለው ገደብ መገናኛ ብዙሃን መረጃ የማሰባሰብ፤ የማደራጀትና ተደራሽ የማድረግ ላይ ተግዳሮት ከመፍጠሩ ባሻገር የሰበሰቡትን መረጃ በሀገርና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ተደራሲያን ኢንተርኔትን እንደ ዋነኛ የመረጃ ማሰራጫ የሚጠቀሙ መገናኛ ብዙሃን ስራቸውን በአግባቡ ለመከወን መቸገራቸውን በመግለጫው ተመላክቷል።
በመሆኑም ሰሞኑን በሀገሪቱ ከተፈጠረው ኃይማኖታዊ አለመግባባቶች ጋር በተያያዘ የችግሩን ስፋትና ክብደት ከግምት በማስገባት ሊቀለበስ የማይችል አደጋን ምክንያት በማድረግ ካልሆነ በስተቀር ሕግን መሰረት በማድረግ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ መንግስት ገደብ ሊያደርግ እንደማይገባ ምክር ቤቱ እንደሚያምን አሳውቋል።
ከዚህ አንፃር በአንዳንድ የኢንትርኔት መረጃ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች ላይ የተጣለው ገደብ ሶስት ሳምንታትን ያስቆጠረ ከመሆኑም በላይ ገደቡ የተደረገበትን ምክንያት የሚመለከተው መንግስታዊ አካል የሰጠው ግልጽ ማብራሪያ ባለመኖሩ የጠቅላላ ህዝቡን መረጃ የማግኘትና የማሰራጨት መብት ላይ ገደብ ለመጣል የሚያበቃ አማራጭ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ገልጿል።

TIKVAH-MAGAZINE
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው የኦሞራቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድጋይ አስቀመጡ። የግንባታው አጠቃላይ ወጪ 20 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን ወጪው ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ-ሠናይ ድርጅት እንደሚሸፈን ተገልጿል።…
#ማስተካከያ
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ 20 ሚሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡን ተዘግቦ ነበር።
ለትምህርት ቤቱ የሚውለው ወጪ ሙሉ ለሙሉ የሚሸፈኘው ሰዎች ለሰዎች (Menschen für Menschen) በተሰኘው ድርጅት መሆኑን የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
"ወጪው በደቡብ ክልል መንግስትና ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ-ሠናይ ድርጅት በጋራ እንደሚሸፈን ተገልጿል።" በሚለው ዘገባ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግም ጠይቀዋል።
ሰዎች ለሰዎች (Menschen für Menschen) ድርጅት የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ በሆኑት በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም ተቋቁሞ ላለፉት 40 ዓመት በላይ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እና ድጋፎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

ኢቢሲ ከ"ፍቅር እስከ መቃብር" ደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ ቤተሰብ ወኪሎች ጋር ተወያየ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ኢቢሲ/ ከ"ፍቅር እስከ መቃብር" ደራሲ የክቡር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ "ፍቅር እስከ መቃብር" የተሰኘውን ልብ ወለድ መጽሐፍን ወደ ፊልም ለመቀየር የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ የደራሲው ቤተሰብ ወኪሎች ለኮርፖሬሽኑ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት በዛሬው ዕለት ከወኪሎቹ ጋር ውይይት ማካሄዱን አሳውቋል።
የኢቢሲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት የሥራ ኃላፊዎች እና የደራሲው ቤተሰብ ወኪሎች የሆኑት ወ/ሮ ማህሌት ንጉሥ፣ አቶ ግርማ አስፋው እንዲሁም አቶ ኃይለመለኮት መዋዕል በተገኙበት በተደረገው በዚህ ውይይት መግባባት ላይ መደረሱን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከሰሞኑን የደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ወራሾች፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) መጽሐፉን ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ቀይሮ “የማስተላለፍ መብት የለውም” ሲሉ ለተቋሙ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው ነበር።
ደራሲው ይህን ስምምነት ከ“ሜጋ ማስታወቂያ ኢንተርፕራይዝ” ጋር ተዋውለው የነበረ ቢሆንም፤ ድርጅቱ ከዓመታት በኋላ “ከስሞ በመዘጋቱ” በመጽሐፉ ላይ የባለቤትነት መብት ያላቸው ወራሾቻቸው እንደሆኑ በመጥቀስ ተቃውሟቹውን ያሰሙ ሲሆን ኮርፖሬሽኑም፤ በጉዳዩ ላይ የተቋሙ አመራሮች ውይይት ካደረጉ በኋላ ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጥ ማስታወቁን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር መዘገቡ ይታወሳል።

አሐዱ ባንክ እና የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ።
አሐዱ ባንክ እና የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውቀዋል። በፊርማ ስምምነቱ እንደተገለጸው ሁለቱ ተቋማት በቴክኖሎጂ፣ በሀብት አሰባሰብ፣ በደንበኞች ምልመላና በሌሎች ዘርፎች በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል ምቹ መደላድል መፍጠር የሚያስችል እንደሚሆን ተብራርቷል።
@tikvahethmagazine
አሐዱ ባንክ እና የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውቀዋል። በፊርማ ስምምነቱ እንደተገለጸው ሁለቱ ተቋማት በቴክኖሎጂ፣ በሀብት አሰባሰብ፣ በደንበኞች ምልመላና በሌሎች ዘርፎች በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል ምቹ መደላድል መፍጠር የሚያስችል እንደሚሆን ተብራርቷል።
@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
የስኳር ኢንዱስቲሪዎችን ወደግል ለማዛወር የወጣው የሽያጭ አማካሪነት ቅጥር የጨረታ ውጤት ይፋ ሆነ። የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በሥሩ ከሚተዳደሩ የስኳር ኢንዱስቲሪዎች መካከል ወደግል ባለሀብቶች ለማዛወር ያወጣው የሽያጭ አማካሪ ቅጥር ጨረታ ኧርነስት ኤንድ ያንግ ግሎባል ሊሚትድ (Ernst & Young Global Limited) ማሸነፉን ኤጀንሲው አስታውቋል። ኧርነስት ኤንድ…
#Update
መንግስት ባለፈው ነሐሴ ወር ስምንት የስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር ጨረታ ማውጣቱን ተከትሎ ከ20 በላይ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ፍላጎታቸውን ማሳየታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።