TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#PositivePeaceBuilding

በታዳጊና ወጣት ሰዓሊያን መካከል አወንታዊ ሰላም ላይ ያተኮረ የስዕል ውድድር እየተካሄደ ነው።

80 የሚሆኑ ወጣቶች በ16 ቡድን ተከፋፍለው አወንታዊ የሰላም ግንባታ (Positive peace Building )፤ የአብሮነትና የግጭት አፈታት ሚናን በሥዕል አጉልቶ ለማሳየት የሚያስችል የስዕል ውድድር እየተካሄደ ነው።

በዚህ የስዕል ውድድር አሸናፊዎችን ለመለየት ከተመረጡ ዳኞች በተጨማሪ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦችም ድምጽ እንዲሰጡበት የሚቀርብ ሲሆን በዳኞችና በተመልካቾች ድምጽ ከፍተኛ ውጤት ያገኘው ቡድን አሸናፊ የሚሆን ይሆናል።

ተወዳዳሪዎቹ  ለውድድር የሚያበቃቸውን የሥዕል ሥራ ትላንት ቅዳሜ እንዲሁም ዛሬ በአዲስ አበባ አለ የሥነ ጥበብ እና የዲዛይን ትምህርት ቤት ተካሂዷል።

በውድድሩ የሚሳተፉ ሰዓሊያንን አብሮ የመሥራት የልምድ ማካበት፣ የዕውቀት ሽግግር መፍጠር ተግባብቶ፣ ተደማምጦ የተጨመቀ ሀሳባቸውን በሥዕል መግለጽ ከውድድር ባለፈ ተግባራዊ እንዲያደርጉት የሚጠበቁ ክህሎቶች ናቸው።

ይህንን የስዕል ውድድር ላለፉት 21 ዓመታት በኢትዮጵያ ወጣት ተኮር ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ አጋሮች ጋር ሲሰራ የቆየው ሪዲም ዘ ጀነሬሽን መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ከሲቪል ሶሳይቲ ሰፖርት ባገኘው ድጋፍ ያዘጋጀው ነው።

@tikvahethmagazine