TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam2016

ከጥቂት ቀናት በኃላ የሚሰጠውን ሀገር አቀፉን የመውጫ ፈተና " ካለንበት ዩኒቨርሲቲ / ተቋም በርካታ ኪሎ ሜትሮችን ርቀን ተጉዘን እንድንፈተን #መመደባችን ተነግሮናል " ያሉ ተመራቂ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቀረቡ።

ቅሬታቸውን ካሰሙት መካከል የተወሰኑት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ ጥቁር አንበሳ ' ስኩን ኦፍ ሜዲስን ' ተመራቂ ተማሪዎች ናቸው።

ተማሪዎቹ የካቲት 6 /2016 ዓ/ም መሰጠት የሚጀምረውን ፈተና ለመፈተን ከአዲስ አበባ ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ሚርቀው ወሎ ዩኒቨርሲቲ እንደተመደቡ እንደተነገራቸውና ጉዳዩ ፍፁም ያልጠበቁት ዱብእዳ እንደሆነ አስረድተዋል።

" የምርቃት ቀናችን 10 ቀናት እየቀሩት የመውጫ ፈተና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ420 ኪ/ሜ ርቀን በወሎ ዩኒቨርስቲ እንደምንፈተን ተነግሮናል፤ ይህ ፍፁም ያጠበቅነውና ያልተለመደ ነው " ብለዋል።

ከተቋማችን እጅግ ርቀን ፈተናውን እንድንወስድ ተመድበናል ያሉት ተማሪዎች ፤ " ላለፉት 8 ዓመታት እዚህ ቀን ላይ ለመድረስ ከነቤተሰቦችን ከፍተኛ መስእዋትነት ከፍለናል፤ ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፈናል " ያሉ ሲሆን ቤተሰቦችም የልጆቸውን ድካም ፍሬ ለማየት እየተጠባበቁ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ተመራቂዎቹ ፦
- አሁን ባለው ሁኔታ ረጅም ጉዞ ማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዳልሆነ እየታወቀ፤
- ለምርቃት የቀረው አጭር ቀን ሆኖ ሳለና በርካታ ካምፓሶች በአዲስ አበባ እያሉ፤
- የብሄራዊ የመውጫ ፈተናው በኦንላይ እንደሚሰጥ እየታወቀ፤
- የደህንነታችን እና በዚህ የምርቃት ወቅት የቤተሰብ ኢኮኖሚ ጉዳይ ፍፁም ታሳቢ ሳይደረግ ለምን እንደዚህ ያለው ውሳኔ እንደተላለፈ በፍፁም ሊገባን አልቻለም፤ ማብራሪያም ሊሰጠን የወደደ አካል የለም ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም " ይህ ወደ ሌላ ቦታ ሄዳችሁ በኦንላይ የሚሰጠውን ፈተና ትወስዳላችሁ " የሚለው ነገር ተገቢ ባለመሆኑ እርምት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ከ ' ስኩል ኦፍ ሜዲስን ' ተመራቂዎች በተጨማሪ የተወሰኑ የምህንድስና ተማሪዎችም ተመሳሳይ ቅሬታቸውን አድርሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመራቂ ተማሪችዎች ጋር በውስጥ የደረሰ የመፈተኛ username ፣ password  እንዲሁም የመፈተኛ ጣቢያ (ዩኒቨርሲቲ) የያዘ ፋይል ደርሶት ተመልክቷል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ ከሌሎች ተቋማት ተመራቂዎች መሰል ቅሬታዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሰዋል።

አንዳንድ ተመራቂዎች አሁን ካሉበት ዩኒቨርሲቲ ርቀው እንደሚፈተኑ በተወካዮቻቸው በኩል እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

በተመሳሳይ እነዚህ ተመራቂዎች ፤ በዚህ ወቅት ወደሌላ ቦታ እንዲጓዙ ተደርገው የኦንላይን ፈተና የሚወስዱበት ምክንያት ምንም ግልፅ እንዳልሆነላቸውና ይህ ነገር ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ማሰብና ማስተካከል እንደሚገባ አስገንዘበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችን ለማነጋገርና መረጃ ለመስጠት ጥረት ያደርጋል።

በአመቱ አጋማሽ ላይ የሚሰጠው የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ተራዝሞ ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወሳል።

በዚህ ሳምንት የሞዴል ፈተና ይሰጣል።

@tikvahethiopia