#DrAlQaradawi
የሙስሊም ምሁራን ፌዴሬሽን መስራችና ፌዴሬሽኑን ለ14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት እውቁ የእስልምና ምሁር ግብፃዊ ዶክተር ሼክ ዩሱፍ አል ቃራዳዊ በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።
ህልፈታቸውን ልጃቸው አብዱል ራህማን ዩሱፍ አል ቃራዳዊ አረጋግጠዋል።
ዶ/ር አልቃራዳዊ ህይወታቸው ያለፈው ኳታር፤ ዶሃ ውስጥ ነው።
እኤአ 2004 የተቋቋመውን (እሳቸው መስራች ነበሩ) ዓለም አቀፉ የሙስሊም ምሁራን ፌዴሬሽን ከተቋቋመበተ ጊዜ አንስቶ ለ14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት መርተዋል።
ዶ/ር አልቃራዳዊ ከሙስሊም ወንድማማቾች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን የኳታር ዜግነት ተሰጥቷቸው ህይወታቸው እስክታለፍ ድረስ ኑሯቸውን በኳታር፣ዶሃ አድርገው ነበር።
አልቃራዳዊ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ወቅት በግብፅ በ1926 ነበር የተወለዱት።
ገና በለጋ እድሜያቸው እስላማዊ ትምህርትን መከታተል የጀመሩት አልቃራዳዊ በፀረ ቅኝ አገዛዛ ላይ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር። በ1950 ዎቹ ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴና ከሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ ጋር በተገናኘ ብዙ ጊዜ ለእስር ተዳርገው ነበር።
ከ120 በላይ መፅሀፍትን ያሳተሙት ዶ/ር አል ቃራዳዊ ለእስልምና ባበረከቱት አስተዋፆ 8 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን መሸለም እንደቻሉ ተገልጿል።
ዶ/ር አል ቃራዳዊ በክፈለ ዘመኑ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የእስልምና ሊቃውንት አንዱ እንደነበሩ ተዘግቧል።
በህይወት በነበሩበት ወቅት በተለያዩ ሚዲያዎች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ አመለካከታቸውን ሲያጋሩ የነበረ ሲሆን በሚያነሷቸው ሀሳቦች የሚደግፏቸው እንዳሉ ሁሉ ሀሳባቸውን የሚቃወሙም ነበሩ።
የዶ/ር አልቃራዳዊን ህልፈት ተከትሎ ፤ የተርክዬ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለልጃቸው አብዱል ራህማን በመደወል የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው አፅናንተዋል።
@tikvahethiopia