TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
60.8K photos
1.54K videos
215 files
4.23K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ⬆️ዛሬ ማለዳ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ ማምሻውን የሚደረገውን የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ምክንያት በማድረግ የቡና፣ የባህርዳር ከነማ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን ጨምሮ ከሌሎች ክለቦች ደጋፊ ማህበር ተወካዪች ጋር የሻይ ቡና ቆይታ አድርገዋል። አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው ስፓርታዊ #ጨዋነት ዙሪያም ምክክር አድርገዋል። እግር ኳሱ መዝናኛ መሆኑ መረሳት እንደሌለበትና ከ90 ደቂቃ የመዝናኛ ልዩነት ባለፈ ከምንም አይነት የብሄርና የፖለቲካ ፅንፍ ጋር ሊገናኝ እንደማይገባ እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩ እግርኳሱና አጠቃላይ የስፖርቱ ዘርፍ እንዲያድግ ማድረግ ስላለበት እገዛ ተወያይተዋል።

ምንጭ፦ Mayor Office of Addis Ababa
@tsegabwolde @tikvahethiopia