TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ግድቡ_የእኔ_ነው

ትላንት ለሊት እንቅልፍ አሸንፏችሁ የUN ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባን መከታተል ያልቻላችሁ በUN የዩትዩብ ቻናል ላይ ይገኛል ገብታችሁ መመልከት ትችላላችሁ።

ጥቂት ትላንት ለሊቱን ስለነበረው ሁኔታ ...

- ኢትዮጵያውን በታላቁ የህዳሴ ግድብ የተጠራውን ስብሰባ በመቃወም ኒው ዮርክ በሚገኘው የተመድ መስሪያ ቤት ሰልፍ አድርገዋል።

- የትላንት ለሊቱን ስብሰባ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የመንግስት ሆነ የግል ሚዲያዎች በንቃት ተከታትለው በፍጥነት የተነሱ ያሳቦችን ለህዝብ ሲያደርሱ ነበር።

- ስብሰባው በቀጥታ በUN ቻናል እንደሚሰራጭ የሰሙ ኢትዮጵያውያን ሙሉ በሙሉ የአስተያየት መስጫውን ተቆጣጥረውት ነበር። አስተያየት መስጫው በኢትዮጵያ ባንዲራ፣ ግንድቡ የእኔ ነው፣ የግድቡን ጉዳይ ወደፀጥታው ም/ቤት ይዞ መሄድ አያስፈልግም በሚሉ መልዕክቶች ተጥለቅልቆ ነበር።

- በርካታ ሀገራት አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩስያ፣ ኬንያ፣ ሜክሲኮ፣ አይርላንድ፣ ህንድ እንዲሁም ሌሎች ሀገራት የድግቡ ድርድር በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እንዲካሄድ ሃሳብ አቅርበዋል።

- የግብፅ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ንግግር አድርገዋል ፤ በንግግራቸው ያነሷቸው ያሳቦች እንደሁል ጊዜው ከእውነታ የራቁ እና ሀገራችንን ተወቃሽ ለማድረግ የሞከሩበት ነበር።

- የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በምክር ቤቱ የኢትዮጵያን አቋም አንፀባርቀዋል፤ እጅግ በሚያስድምም ሁኔታ በግድቡ ዙሪያ ስላለው ሁኔታ እና እውነታ አስረድተዋል።

- ኢትዮጵያውያን ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ባቀረቡት ንግግር ከልባቸው ተደስተው ፣ ኮርተውም ካሰሙት ንግግር በወሰዱት አረፍተነገሮች እና በእሳቸው እና አብረዋቸው በስብሰባው በነበሩ የኢትዮጵያ ተወካዮች ፎቶ ማህበራዊ ሚዲያውን ተቆጣጥረውት አንግተዋል።

@tikvahethiopia