TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ አዟል። በዋስ ጥያቄያቸው ዛሬም ውድቅ ተደርጓል። ቀሲስ በላይ መኮንን በችሎቱ ፥ " ፖሊስ ይዞኝ ሳይሆን እራሴ ነው የሄድኩት " ብለዋል፡፡ " #ብዙ_የሀገር_ጉዳይ በእጄ ስላሉ ጥፋ ብባል እንኳ የምጠፋ ስላልሆንኩ ፤ በጤናዬ ላይ በደረሰው እክልና በቤተሰቦቼ ላይ በደረሰው…
#Update

ከ 'አፍሪካ ህብረት' የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ በ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር የምዝበራ ሙከራ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ የጠየቁት ዋስትና ውድቅ ተደርጓል።

ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ከምዝበራ መኩራው ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ፦

1ኛ. ቀሲስ በላይ መኮንን፣
2ኛ. በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣
3ኛ. በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር፣
4ኛ. አለምገና ሳሙኤል ዲንሳ
5ኛ. የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ ናቸው።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉ ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ውድቅ ተደርጎ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ታይዟል።

ፍርድ ቤት ለግንቦት 29/2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዛሬ ችሎት ተጠርጣሪዎች የተከሰሱበት አዋጅ ከ10 ዓመት በላይ የሚያሳስርና ከባድ ፍርድ የሚያስከትል በመሆኑ ማረሚያ ወርደው ፍርዳቸውን ይከታተሉ ተብሏል።

ቀሲስ በላይ #የጤና_እክል እንዳለባቸው ጠቅሰዋል። በፌደራል ፖሊስ ጊዜያዊ ማቆያ ለመቆየት እንዲችሉ እንዲፈቀድላቸውም ጠይቀዋል።

ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተወከለ መርማሪ የጊዜያዊ ማቆያው ቦታ ጥበት መኖሩን ጠቅሶ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ እንዲደረግ ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ እስከ ቀጣይ ቀጠሮ ግንቦት 29 ቀን ድረስ ባሉበት የፖሊስ ማረፊያ እንዲቆዩ ፈቅዷል።

4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት የፌደራል ፖሊስ ተገቢ ጥረት አድርጎ አፈላልጎ እንዲያቀርባቸው ታዟል።

መረጃው ከኤፍቢሲና ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የተወሰደ ነው።

https://telegra.ph/fbc-05-27-2

@tikvahethiopia