TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የስራ ማቆም አድማ መቱ...

#የኮይሻ_ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ ከአምስት ሺህ በላይ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አዱማ ከመቱ ሁለተኛ ሳምንት መያዙን ተናገሩ፡፡
 
ሰራተኞቹ ሥራ አቆምን ያሉት በሚደረስባቸው የአስተዳደር በደል ፣ ከደመወዝና ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዙ ችግሮች ሲሆን በደል አድርሰውብናል ያሏቸው ስድስት የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች እንዲባረሩ ይጠይቃሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ጥያቄቸው ተገቢ ባይሆንም ከምግባቸው ላይ የሚቀነሰውን ገቢ ግብር ሳሊኒ ኩባኒያ እንዲሸፍን፤ በደመወዛቸው ላይ ደግሞ 450 ብር እንዲጨመር ተማምነናል ብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ መቀጠል ስላለበት ይህንን የማይቀበሉ ሠራተኞች እንደሚሰናበቱ ተወስኗልም ተብሏል፡፡

በህግና በማስረጃ እንጂ የደቦ ፍትህ በመፈለግ ስድስት የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች ይባረሩ ማለታቸው ስህተት ነው ብሏል፡፡

Via #VOA24
@tsegabwolde @tikvahethiopia