TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#የሹመት_መረጃዎች

1. አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አሳውቋል። በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ የነበሩት አምባሳደር ተስፋዬ እንግሊዝን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሀገራቸውን ያገለገሉ ነባር ዲፕሎማት ናቸው።

2. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ዙር፣ 1ኛ ዓመት፣ 12ኛ መደበኛ ጉባዔው በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የቀረቡለትን የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር እና ምክትል ዋና ኦዲተር ሹመቶችን በሙሉ ድምፅ አጽድቋል። በዚሁ መሰረት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ጫንያለው የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር፤ አቶ አበራ ታደሰ ኢቲቻ ደግሞ የመ/ ቤቱ ምክትል ዋና ኦዲተር ሆነው ተሾመዋል።

@tikvahethiopia