TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " በአንዋር መስጂድ የነበሩ በቁጥር እጅግ በርካታ ሰዎች በሰላም እንዲወጡ ተደርጓል " - የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ እና የበላይ አመራሮች በአንዋር መስጂድ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የማረጋጋት ስራ በመስራት አንድ ሸሂድ (መስዋእት) የሆነ ሙስሊም እና ጉዳት የደረሰባቸውን ወደ ሆስፒታል…
መንግሥት ምን አለ ?
መንግሥት በታላቁ አንዋር መስጂድ " ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ " የሚንቀሳቀሱ #የሴራ_ቡድኖች የሰላቱን ሰላማዊ ሥነ-ሥርዓት ለማስከበር በተሰማሩ የፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት በማድረስ በተነሳ ረብሻ የሰው ህይወት መጥፋቱን እና ጉዳት መድረሱን ገለፀ።
የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ዛሬ ምሽት መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው ፤ ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ መስጅዶች የተካሄደው የጁምአ ሶላት በሰላም ተጠናቋል ብሏል።
በታላቁ አንዋር መስጅድ የጁምዓ ሶላት በሰላም ተጠናቆ ህዝብ ሙስሊሙ እየተመለሰ ባለበት ሁኔታ ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ " ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ " የሚንቀሳቀሱ #የሴራ_ቡድኖች የሰላቱን ሰላማዊ ሥነ-ሥርዓት ለማስከበር በተሰማሩ የፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት ለማድረስ በተነሳ ረብሻ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በተወሰኑ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል።
በንብረት ላይም እስከ አሁን ግምቱ ያልተወቀ ኪሳራ ደርሷል ያለው ግብረኃይሉ ለፀጥታ ሥራ በተሰማሩ 63 የፖሊስ አመራር እና አባላት ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጿል።
ግብረ ኃይሉ " ፀረ-ሰላም ኃይሎች " ሲል የጠራቸው አካላት የእምነቱ ተከታዮች በህጋዊ መንገድ ያቀረቡትን ጥያቄ በመጥለፍ የራሳቸውን እኩይ ዓላማ ለማሳካት ረብሻውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛመት ያደረጉት ጥረት የፀጥታ ኃይሉ፣ ህዝበ ሙስሊሙ እና የሀይማኖቱ አባቶች በጋራ በመሆን ባደረጉት ርብርብ መቆጣጠር ተችሏል ብሏል።
ግብረ-ኃይሉ ፤ የከተማውን ብሎም የሀገሪቱን ሠላምና ደህንነት ለማስከበር የጀመረውን ህግ የማስከበር ሥራ #አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት እና በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ " ፀረ-ሰላም ኃይሎች " ላይ የጀመረውን ምርመራም በመቀጠል በቀጣይ ውጤቱን ለህዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
@tikvahethiopia