TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ኢንዱስትሪ ፓርኮች

ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር አልመው የተቋቋሙት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከፍተኛ #የሰራተኛ_ፍልሰት እየፈተናቸው ነው ተባለ፡፡ ከቀጠሯቸው ሰራተኞች በሩብ አመት ውስጥ እስከ 98 በመቶ መልሰው የለቀቁባቸው ፓርኮች መኖራቸውን ተሰምቷል፡፡

ለዚህ ዋናው ምክንያት ፓርኮቹ ተመርቀው ስራ ከጀመሩ በኋላ በአካባቢው የቤት ኪራይ በከፍተኛ መጠን #መጨመር ነው ተብሏል፡፡

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለ3 ተከታታይ አመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ያደረገው የክዋኔ ኦዲት ግኝት እንደሚያሳየው በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሰራተኞች ፍልሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው፡፡

እንደ ምሳሌም በቦሌ ለሚ ቁጥር አንድ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ በ2008 ሩብ አመት ከተቀጠሩ ሰራተኞች 42 ነጥብ 5 በመቶ ለቅቀዋል፡፡

በ2009 ዓ/ም ደግሞ በዚሁ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እድል ካገኙት 72 ነጥብ 3 በመቶዎቹ ስራውን ትተው ሄደዋል፡፡

በሶስተኛ አመት 2010 ዓ/ም ከቀደሙት ጊዜ በባሰ ሁኔታ የለቀቁት ሰራተኞች ቁጥር 98 ነጥብ 9 በመቶ መድረሱን የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት ግኝት ያሳያል፡፡

እንዲህ ያለው የሰራተኞች ፍልሰት የኢንዱስትሪ ፓርኮች የተቋቋሙበት ዋና ዓላማ የሆነውን ለዜጎች የስራ እድል መፍጠርን ሳይሳካ እንዲቀር ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የፓርኮቹ ምርታማነትና የወጪ ንግዱ ላይም ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ተነግሯል፡፡

ወሬውን የሰማነው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ የተደረገውን የክዋኔ ኦዲት ግኝትና የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎችን በተመለከተ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ሲመክር ተገኝተን ነው፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ #ሌሊሴ_ነሜ እንዳሉት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ስራ #የሚለቁ ሰራተኞች ቁጥራቸው ከፍተኛ እንዲሆን ያደረገው ዋና ምክንያት የቤት ኪራይ መጨመርና የኑሮ ውድነት ነው ብለዋል፡፡

#የሐዋሳ_ኢንዱስትሪ_ፓርክ ስራ በጀመረ ጊዜ 300 ብር የነበረው የቤት ኪራይ ከ1 ሺህ 100 ብር በላይ ሆኗል ብለዋል፡፡

የኑሮ ውድነቱ ሰራተኛው ፓርኩን ለቆ በተለያዩ የግንባታ ስራዎች ላይ በቀን ሰራተኝነት ለማስራት እንዲመርጥ አድርጎታል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፡፡ በመሆኑም መንግስት ለጉዳዩ እልባት በመስጠት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስራ በጀመሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 45 ሺ ሰራተኞች ተቀጥረው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia