TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ዐቢይ_ጾም

ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ2016 ዓ/ም የዐቢይ ጾመን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ጾም ማለት እህልንና የእንስሳት ውጤቶችን ከመመገብ መከልከል ብቻ አይደለም፤ የእንስሳት ውጤት የሆኑትን ላለመመገብ ከምንወስነው በላይ እኩያት ፍትወታትንና ኃጣውእን ላለማስተናገድ በቁርጥ መወሰን ይጠበቅብናል፡፡

ስንጾም መገዳደልን፣ መጣላትን፣ መለያየትን፣ መገፋፋትን በሆነ ነገር መጐምጀትን እርም ብለን በመተው ዲያብሎስን የምናሸንፍበት የአሸናፊነት ኅሊና መላበስ አሰብን፣ ከክፉ ጎሊና እና ተግባር የተለየን ያህል በአንጻሩ ደግሞ በጎ ነገርን ለመስራት በእጅጉ መበርታት ይጠበቅብናል፡፡

ዲያብሎስ ተስፋ ቆርጦ የሚሸሸው ይቅር ይቅር ስንባባል፤ ለሰላምና ለአንድነት፣ ለፍቅርና ለስምምነት ስንቆም ነው፣ ከዚህም ጋር በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ጸያፍ የሆነው ግብረ ኃጢአት በዚህች ምድር እንዳይፈጸም ማኅበረ ሰባችን በተጠንቀቅ ሲቆም ነው፤ እንደዚሁም ደም መፋሰስ፣ አለመተማመንና በሴት ልጆቻችን የሚደርሰው አካላዊ፣ መንፈሳዊና ሞራላዊ ጥቃት ሲቆም ነው፡፡

ጸማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ፣ ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡

ይህ ዓይነት መልካም ሥነ ምግባር በእያንዳንዱ የማኅበረ ሰብ አእምሮ ቦታ አግኝቶ ሲተገበር ትክክለኛውን ጾም ጾምን ማለት እንችላለን፣ ዲያብሎስም በእርግጠኝነት በዚህ ይሸነፋል፣ የሰው ጣዕመ ሕይወትም በዚህ ይለመልማል፣ ምድሪቱም በእግዚአብሔር በረከት ትሞላለች፡፡ ይህ ቅዱስ ተግባር በወርኃ ጾሙ በደንብ እንድንተገብረው ለመላው ኢትዮጵያውያን በተለይም ለኦርቶዶክሳዊው ማኅበረ ሰብ መንፈሳዊና አባታዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ዐቢይ_ጾም

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የ2016 ዓ.ም የዓብይ ጾም መግቢያን በማስመልከት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ጌታችን ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ወንጌሉን ይሰብክ ዘንድ የአባቱን ተልእኮ ሊፈጽም ነፍሳትን ለማዳን የጠፉትን ለመፈለግ ተልእኮ ሲሆን ዲያብሎስ ያቀረበለት ጥያቄ ፈታኝነቱ አምላክን ከማገልገልና እርሱን ከማምለክ ይልቅ ለእኔ ተገዛ አገልጋይ ሁን የሚል አንድምታ ያለው ነው፡፡

የጌታችን ኢየሱስ መልስ ግን ከሰይጣን ጋር መስማማትን ሳይሆን እግዚአብሔር አምላክን ማምለክ ለእርሱ ብቻ መስገድና ለእርሱ አገልጋይ መሆን እንደሚገባ አስረግጦ ይናገራል፡፡

ዛሬም የብዙዎቻችን ፈተና እግዚአብሔር አምላክ በሰጠን ስልጣን ባስቀመጠን የኃላፊነት ቦታ ላይ በፍቅር እናገለግላለን ? ሲሾም ያልሰራ ጡረታ ሲወጣ ይጸጸታል እንላለን ወይንስ ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል በሚል ዓይነት ስልጣናችንን አላገባብ እየተጠቀምን ነው ? ሌሎች በአገልግሎታችን ይደሰታሉ ? አምላክን ያመሰግናሉ ? ወይስ በእኛ የአገልግሎት አሰጣጥ ይማረራሉ ? ይህ የጾም ወቅት ራሳችንን የምናይበት እና የምንፈተንበት ጊዜ ነው፡፡

ኃላፊነት ከሰሩበት ካገለገሉበት በረከቱ ለሁላችንም ነው፤ ፈተናችን የሚሆነው መስራት በሚገባን ጊዜና ቦታ ለሕዝባችን ማገልገል ሲገባን ስልጣናችንን ለማሳየትና ሌላ ተጨማሪ ከፍያ ተጨማሪ ክብር ከፈለግን፣ በማገልገላችን ልንከበር ሲገባ ቦታው ላይ በመቀመጣችን ብቻ ክብር ካልተሰጠን የሚል ስሜት ከተሰማን፣ ፈተናውን ወደቅን ማለት ነው፡፡

ፈተና የምንወስደው ለማለፍ እንጂ ለመውደቅ አይደለም፤ በዚህ የጾም ወራት ፈተናችንን ለማለፍ ልንዘጋጅ ይገባል፡፡ እንዲሁ የሚደረግ ጾም የለምና ለጥያቄአችን መልስ እንድናገኝና እግዚአብሔርን በማዳመጥ ፈቃዱን ለማድረግ እንጹም፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ፈተናችንን አልፈን ፣ ንስሐ በመግባት ከእርሱና ከሰዎች ሁሉ ጋር ታርቀን ካለን ላይ ለወገኖቻችን አካፍለን እርሱ ወደፈለገው የፍቅርና የሰላም ኑሮ መኖር እንድንችል ጾምና ጸሎታችንን ይቀበልልን፡፡

ለትንሳኤው ብርሃን በሰላም ያድርሰን፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ዐቢይ_ጾም

" በወርኃ ጾም ከመልካም ኅሊና የሚመነጭ መልካም ስራ ማከናወን ግድ ይለናል፤  ምክንያቱም ጾምን የምንጾመው መልካም ኅሊና ኖሮን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝና ለመገዛት ነው " - ቅዱስነታቸው

የጾመ ኢየሱስ ሱባዔ (
ዐቢይ ጾም)ን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከቅዱስነታቸው መልዕክት ፦

" ጾመ ኢየሱስ እያልን በየዓመቱ የምንጾመው የታላቁ ጾማችን ዓላማ ዲያብሎስን ለማሸነፍ ነው፤ የዲያብሎስ ማሸነፊያ ስልት የመልካም ኅሊና ልዕልና ነው፤ ሰውነታችን በመብልና በመጠጥ ሲደነድን መልካም ኅሊና በውስጣችን ዓቅም ያጥረዋል፤ መልካም ኅሊና ሲያጥረን ዲያብሎስ ዘው ብሎ ይገባና ወደ ክፉ ኅሊና፣ ከዚያም ወደ ግብረ ኃጢኣት ይወስደናል፤ በዚህ ጊዜ እኛ ተሸናፊዎች እሱ ኣሸናፊ ይሆናል፤ በአንጻሩ ደግሞ ሰውነታችን ከመብልና ከመጠጥ ሲለይ መልካም ኅሊና፣ ቊጥብነት፣ ማስተዋልና ማመዛዘን በውስጣችን ትልቅ ጉልበት ያገኛሉ፤ እነሱ ጐለበቱ ማለት ዲያብሎስ መግቢያ አጣ ማለት ነው፤ እሱ ካልገባ ግብረ ኃጢኣት አንፈጽምም፤ በዚህ ጊዜ ዲያብሎስ ተሸናፊ እኛ ኣሸናፊዎች እንሆናለን፤ ስለሆነም ጾምን የምንጾመው በዚህ ስልት ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ  ነው።

ከዚህ አኳያ ዲያብሎስን ለማሸነፍ መጾም ግድ ስለሆነ ጌታችን በከፈተልንና ባሳየን መንገድ እንጾማለን፤ እንግዲህ በወርኃ
ጾም ከመልካም ኅሊና የሚመነጭ መልካም ስራ ማከናወን ግድ ይለናል፤  ምክንያቱም ጾምን የምንጾመው መልካም ኅሊና ኖሮን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝና ለመገዛት፣ ከዚያም ከቃሉ በተነገረን መሠረት የተራቡትን ልንመግብ፣ የተራቈቱትን ልናለብስ፣ የተጣሉትን ልናስታርቅ፣ ፍትሕ ያጡትን ፍትሕ እንዲያገኙ ልናደርግ፣ ለንኡሳን የሕብረተ ሰብ ክፍሎች የተለየ ትኵረት ልንሰጥ፤ እኩልና ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል በሰው ልጆች መካከል ልናረጋግጥ፣ ሰብኣዊ ክብር እንዳይነካ ጦርነት፣ ጥላቻ፣ አደገኛ የቃላት ውርወራና መነቃቀፍ እንዲቀር ልናደርግ ነው ፤ በዚህ መንፈስ ጾሙን ከጾምን ጾማችን ግቡን መትቶአል፤ ዲያብሎስም ተሸንፎአል ማለት ነው፤ ስለሆነም በዚህ መንፈስ ጾሙን ልንጾም ይገባል፡፡

ወርኀ ጾሙን የተራበውን በመመገብ የተራቈተውን በማልበስ በኃላፊነት ያለን የኅብረተሰብ መሪዎችም ፍትሕንና እኩልነትን በማስፈንና ከነገሮች ሁሉ በፊት ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ በመስጠት ጾሙን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን። "

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia