TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በዩናይትድ ኪንግደም (UK) የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከቢቢሲ " ኒውስ ሀወር " ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ያደረጉት ቃለ ምልልስ ! @tikvahethiopia
አምባሳደሩ ምን አሉ ?

" ኤርትራ ችግር ናት ብዬ አላስብም ፤ ህወሓት ነው የቀጠናው ችግር፤ አሜሪካ ግጭቱን በማስቆም ረገድ ግልፅ ከሆነች በህወሓት ላይ ጫና ማሳደር ይገባታል " - አምባሳደር ተፈሪ መለሰ

በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከቢቢሲ ኒውስ ሀውር ጋር ቆይታ አድርገው የነበረ ሲሆን በዚህም ወቅት አሁን ስላለው ሁኔታ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስቶላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ፤ የተኩስ አቁሙ ከታወጀ በኃላ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ በየቀኑ ጥሩ በሚባል ሁኔታ እየሄዱ ነበር ብለዋል። በአየር በረራዎችም መድሃኒትን ጨምሮ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች ሲጓጓዙ እንደነበር ገልፀዋል። ይህ ሁሉ ወደ ሰላም ጥረቱ ለማምራት ሲሆን ለዚህ ጥረት ምላሹ ግን  ያ አልነበረም (ሰላም አልነበረም) ሲሉ የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል።

የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሃመር በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ እንዳሉ እና ጉብኝታቸውን በተመለከተ የተጠየቁት አምባሰደሩ ...

" ከዚህ በፊትም እዚያው ነበሩ ፤ የአውሮፓ ህብረት እና የዩናይትድ ኪንግደም ልዩ ልዑካንም ኢትዮጵያ ነበሩ ህወሓት /TPLF ወደ ሰላም ጠረጴዛውን እንዲመጣ ለማበረታት። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ገና ከጅምሩም አቋሙ ገልጽ ነው በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል " ሲሉ መልሰዋል።

አሜሪካ፤ ኤርትራ ወደ ግጭቱ ዳግም መግባቷን በመግለፅ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር መስራቷን እንድታቆም እና በኢትዮጵያ በኩል የሚፈፀሙ የአየር ጥቃቶች እንዲቆሙ ጠይቃለች በሚል ለተነሳው ....

" ይህ በቀላሉ እውነት አይደለም። ኤርትራ ሉአላዊ ሀገር ነች ፤ ከህወሀት ጋርም የራሳቸው ታሪክ አላቸው። እንደሚታወቀው ከኤርትራ ጋር ያለውን አለም አቀፍ ድንበር የሚቆጣጠሩት የህወሓት ሃይሎች ናቸው እንጂ የኢትዮጵያ ጦር አይደለም፤ ድንበሩ ለኛ ነው እኛ ግን እየተቆጣጠርነው አይደለም " ብለዋል።

የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ህወሓትን ለመደምሰስ እንደሚፈልግ ተናግሯል በዚህስ ላይ ...

" የኤርትራን መንግስት ወክለን ልንናገር አንችልም። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ግን እነሱም ህወሓት ወደ ዋና ከተማዋ አስመራ በተኮሳቸው ሚሳኤሎች እና ሮኬቶች ተተንኩሰዋል። (በህወሓት) "

የኢትዮጵያ ወታደሮች ኤርትራ ውስጥ ሰፍረዋል ? በሚል ለቀረበ ጥያቄ ...

" አይ ፤ /No / ፤ ያ መረጃ የለኝም " ሲሉ መልሰዋል።

የኢትዮጵያ ወታደሮች እዛ እንዳሉና ከፕሬዜዳንት ኢሳያስም ትዕዛዝ እንደሚቀበሉ የሚገልፁ ሪፖርቶች አሉ በሚል ለተነሳው ሀሳብ...

" ያን ለማመን ይከብዳል ምክንያቱም ጦራችን #ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለ እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሀገራት እንደነበረው ለሰላም አስከባሪ ሃይል #ካልተጠራን በስተቀር ወታደሮቻችን ኤርትራ የሚሄዱበት ምንም ምክንያት የለም " ብለዋል።

የኤርትራስ ወታደሮች በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ወይ  ? ለሚለው ጥያቄ ...

" አይ / no / " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በትግራይ ያለው ከበባ እንዲያበቃ በኢትዮጵያ ያሉ የኤርትራ ወታደሮች ይውጡ በሚለው ላይ ምላሹ " የሉም " የሚል ነው ? በሚል ለቀረበው ጥያቄም ...

" ጥሩ ! እኛ እስከሚገባን ምንም አይነት እገዳ የለም። በዓለም አቀፍ ህግ የዓለም አቀፍ ድንበሮቻችንን የመከላከል ኃላፊነት አለብን (መንግስት ኃላፊነት አለበት) ነገር ግን አሁን ላይ ከኤርትራ ጋር ባለው ድንበር ላይ እየተፈጠረ ላለው ነገር ተጠያቂ አይደለንም " ብለዋል።

ለአዲስ የተኩስ አቁም እድል ይኖር እንደሆነ ተጠየቀው ...

" መንግስት እስካሁን በመከላከል አኳኋን ላይ ነው ያለው። በትግራይ ውስጥ ጥቃት እየፈፀምን አይደለም ፤ እስካሁን በመከላከል ላይ ነን ፤ እንዲሁም ህወሓት ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ እንዲመጣ ጥሪ እያደረግን ነው፤  ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህን እንዲያደርግ እናበረታታለን ምክንያቱም በጦርነት ምንም መፍትሄ የለም። " ሲሉ መልሰዋል።

አሜሪካ ኤርትራ ዳግም ወደ ግጭት ገብታለች በሚል ከማውገዟ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ባሉት የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ምን መልዕክት ደረሰ በሚል ለተነሳ ጥያቄም ...

" ኤርትራ ችግር ናት ብዬ አላስብም ፤ ህወሓት ነው የቀጠናው ችግር። አሜሪካ ይየሶስተኛውን ዙር ግጭት / ጦርነት በማስቆም ረገድ ግልፅ ከሆነች በህወሓት ላይ ጫና ማሳደር ይገባታል። " ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia