TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow የሀሳብ ቅኝት የተሰኘው በሀሰተኛ መረጃ እንዲሁም የጥላቻ ንግግርን ለመግታት የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ያተኮረው ልዩ የወጣቶች መድረክ በሸራተን አዲስ መካሄድ ጀምሯል። ዝግጅቱን ኦላይን መከታተል ለምትፈልጉ https://fb.watch/g3zmdGYwI6/ @tikvahethmagazine
#የሐሳብ_ቅኝቶች

የሐሳብ ቅኝቶች የተሰኘው የወጣቶች መርሐግብር የመጀመሪያ ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል።

በመድረኩ " ሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር " ን ለመግታት የሚደረጉ ጥረቶች ከተሳታፊዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

እንዲሁም ልዩ ልዩ መርሐግብሮች ተከናውነዋል።

በነገው ዕለት የዝግጅቱ ሁለተኛ ክፍል የሚቀጥል ሲሆን በዕለቱ ለመገኘት #ከተመዘገቡ በተጨማሪ #ላልተመዘገቡ ተሳታፊዎች ጭምር እንዲሳተፉ እድሉ ተመቻችቷል።

ነገ ከጠዋቱ 3:00 ላይ በ " ሸራተን አዲስ ሆቴል " በመገኘት መሳተፍ ትችላላችሁ። ዝግጅቱ ምንም አይነት መግቢያ የሌለው (ነፃ) መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

በተጨማሪም ለተሳታፊዎች የተሳትፎ " ሰርተፊኬት " በማጠቃለያው መርሐግብር የሚሰጥ ይሆናል።

@tikvahethiopia
" በ1 ዓመት ጊዜ 300 በልብ ሕመም ለሚሰቃዩ ሕፃናት ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንሰጣለን " - አቶ ብርሃን ተድላ

" ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል " በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 300 በልብ ሕመም ለሚሰቃዩ ሕፃናት ነጻ የሕክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ከሰሞኑን ገልጿል።

ሕክምናው በህፃናት እና በአዋቂ  የልብ ቀዶ ህክምና ከ25 ዓመት በላይ ልምድ ባላቸው እና 16 ሺህ በላይ ቀዶ ህክምናዎች ባደረጉት፣ ከህንድ አገር በመጡት ዶ/ር ሙስኮኒ ኮፓላ የሚመራ ነው ተብሏል።

ይህንን ህክምና ከሚፈልጉ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ማዕከል #ከተመዘገቡ ህጻናት መካከል ነው በየዓመቱ ለ300 ህጻናት ያለ ክፍያ የቀዶ ጥገና ሕክምና የሚሰጠው።

የሆስፒታሉ መስራች ባለቤት አቶ ብርሃን ተድላ ፤ የልብ ሕሙማን ሕፃናት ችግር በአንድ ሆስፒታል ጥረት ብቻ እንደማይቀረፍ ገልጸው አቅም ያላቸው ወገኖች ቢያንስ አንድ ልጅ በማሳከም አስተዋፅኦ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

የነፃ ሕክምናው ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ላይ የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ  ታደሰ ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሆስፒታሉ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia