TIKVAH-ETHIOPIA
እባካችሁ አሽከርካሪዎች ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ! ትላንትና ሀሙስ በሰሜን ሜጫ ወረዳ በ " አምቦ መስክ " ቀበሌ አቅጣጫውን ከባህር ዳር ወደ ማርቆስ ያደረገ ሰሌዳ ቁጥር " አማ 17492 " የሆነ ተሽከርካሪ ወይም ኮስትር ተሽከርካሪ እና መነሻውን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ያደረገ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ጋር ግጭት ተፈጥሮ በተሳፋሪዎች…
" ተማሪዎቹ በሰላም ገብተዋል "
ዛሬ " የሰሜን ሜጫ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን " እና " የመራዊ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት " ትላንት በአምቦ መስክ ቀበሌ ከባህር ዳር ወደ ደብረ ማርቆስ ያደረገ ኮስተር ተሽከርካሪ እና #ከሰከላ_ወረዳ የ12ኛ ክፍል ተማሪዌችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ተጋጭተው " ከቀላል እስከ ከባድ " ጉዳት መድረሱን አሳውቀው ነበር።
ከዚህ በተጨማሪ ፤ የሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መዝገቡ ስመኘው ለብስራት 101.1 ሬድዮ ጣቢያ በትራፊክ አደጋው የተጎዱ ሌሎች ሰዎች መኖራቸውን እና በተማሪዎች ላይ ከደረሰው ጉዳት መካከል በ5 ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱንና ፈተና ላይ ከመቀመጥ የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።
ዛሬ ከሰዓት ደግሞ የሰከላ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ በላይነህ አድማስ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ በነበረው የህዝብ ተሽከርካሪ ላይ ፤ " የትራፊክ አደጋ የደረሰ ቢሆንም በተማሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አላደረሰም " ብለዋል።
ተማሪዎቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው ሌላ መኪና ተቀይሮላቸው በሰላም ወደተመደቡበት መግባታቸውን አረጋግጠናል ብለዋል።
ወላጆች ክስተቱን በመስማት እንዳይደነግጡ እና ተማሪዎችን ለማግኘት በሚል አላስፈላጊ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ መልዕክቱን የማዳረስ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል።
በተጨማሪ ፤ የሰከላ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እሱባለው መንግስት ፤ በትራፊክ አደጋው ተማሪዎች ተጎዱ ተብሎ የተሰራጨው ስህተት ነው ብለዋል።
ተማሪዎችን ይዞ የነበረው ቅጥቅጥ አይሱዙ መንገድ ከመልቀቅ ፣ ፍሬቻና ስፖኪዮው ከመጎዳት ውጭ ጉዳት አልደረሰበትም ብለዋል። ተማሪዎች ላይ ቀላል የሚባልም ጉዳት እንዳልደረሰ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ዛሬ ጥዋት መረጃውን ለህዝብ ያሰራጩት የሰሜን መጫ መንግስት ኮሚኒኬሽ እና የመራዊ ኮሚኒኬሽን ከማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ምንም ነገር ሳይሉ #መረጃውን_ማጥፋታቸውን ተመልክቷል።
ዋናው የተማሪዎቹ ሰላም መሆንን እና ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባታቸው ነው ፤ የተለያዩ የኮሚኒኬሽን ቢሮዎች ለህዝብ የሚያሰራጩትን መረጃ እንዲናበብ ማድረግ እንዲሁም ትክክለኛውን ሁኔታ በዝርዝር አረጋግጠው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
መሰል የመረጃዎች ስርጭት ቤተሰቦችንም የሚረብሽ በመሆኑ በመንግስት የኮሚኒኬሽን አካላት የሚሰጥ መረጃ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል።
ከዚህም ባለፈ ፤ ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ተቋማት የማድረስ ስራ እየተሰራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የትራፊክ እንቅስቃሴው በእጅጉ ጨምሯልና አሽከርካሪዎች ከምን ጊዜው በላይ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘነጉ።
@tikvahethiopia