TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አውሎ #ኢትዮፎረም
ከሳምንት በፊት ተይዘው የነበሩት የአውሎ ሚዲያ እና የኢትዮ ፎረም ባለሙያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለቢቢሲ ተናግሩ።
ጠበቃ ታደለ የሚዲያ ባለሙያዎቹ ከታሰሩ ከ1 ሳምንት በላይ ቢያልፍም እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና ያሉበትን ቦታ ቤተሰቦቻቸው ማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል።
የሚዲያ ባለሙያዎቹ የተያዙት በፌደራል ፖሊስ መሆኑን እና በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ወቅት በተለምዶ ሜክሲኮ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርምራ ማዕከል መወሰዳቸውን ተናግረዋል።
"እስከ አርብ ሰኔ 25 ድረስ ቤተሰብ ሲጠይቃቸው እና ምግብ ሲያደርስ ነበር። ከዛ በኋላ ግን 'ተለቀዋል እዚህ የሉም' ተብለዋል። ቤተሰብ ሊያገኛቸው አልቻለም። ፍርድ ቤትም እስካሁን አልቀረቡም" ሲሉ ገልፀዋል።
የሚዲያ ባለሙያዎቹ ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ከመደረጉም በላይ የተያዙበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንዳልተነገራቸው ጠበቃ ታደለ ተናግረዋል።
ጠበቃ ታደለ፥ "የባለሙያዎቹን እስር በተመለከተ ፖሊስ በአንድ መገናኛ ብዙኃን ሲጠየቅ ባለሙያዎቹ የታሰሩት ከአሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት ስላላቸው ነው የሚል ምላሽ እንደሰጠ አንብቤያለሁ። ከዛ ውጪ ግን ለእኛ በግልጽ አልተነገረንም" ብለዋል።
ጠበቃው፥ "ቤተሰብ በጣም ተጨንቆ ወደ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሄደው አቤቱታ አቅርበው ነበር። ሰኞ እና ማክሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብለን እየጠበቅን ነበር ግን ሳይቀርቡ ቀርተዋል" ሲሉ ገልፀዋል።
በአገሪቷ ሕጎች ላይ የዘፈቀደ እስር ሊኖር እንደማይገባ የገለፁት ጠበቃ ታደለ፤ ደንበኞቻቸው በተያዙ በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ነበረባቸው ነገር ግን አልቀረቡም በዚህም የአገሪቷ ሕግ ተፈጻሚ ሳይሆን ቀርቷል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። #BBC
@tikvahethiopia