#update ሜቴክ ስሙን ሊቀይር ነው⬇️
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወታደራዊ ምርት የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በማስረከብ በአዲስ ስያሜ ሊደራጅ ነው።
ከተቋቋመ ጀምሮ በጥቂት ጊዜ በርካታ የመንግስት ፕሮጀክቶችን እንዲይዝ ተደርጎ የነበረው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከብቃት፣ እጦትና ከብክነት ጋር ተያያዘ ስሙ ሲነሳ ቆይቷል።
እጁ ላይ የነበሩ በርካታ የስኳር ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ አቅቶት ፕሮጀክቶቹን ሲቀማ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሃይድሮ መካኒካል ስራዎችን ወስዶ መስራት ባለመቻሉም ቢሊየን ብሮች እንደባከኑ ተሰምቷል።
ከዚህ ሁሉ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር የኮርፖሬሽኑን አመራሮች ከመቀየር አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰድበት እያደረገ ነው።
የኮርፖሬሽኑ የኮመርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ #አብዱልዓዚዝ_መሀመድ ለfbc፥ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የኮርፖሬሽኑን አደረጃጀት ማስተካከል ነው።
ይህም በሜቴክ ስር ወታደራዊ ምርቶችን ሲያመርቱ የነበሩ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በመስጠት ቀሪዎችን በስሩ የሚያስቀጥል መሆኑንም ይናገራሉ።
በዚህ መሰረት ሜቴክ አዲሱን ስያሜ ይዞ የሲቪልና የንግድ ምርቶችን ብቻ የሚያመርት ሲሆን፥ የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል አዲስ ስያሜ ሊሰጠው እንደታሰበም ተናግረዋል።
ለዚህ አዲስ አደረጃጀት ረቂቅ ደንብ የተዘጋጀ ሲሆን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸቀደ በኋላ ወደ ትግበራ እንደሚገባም ነው የተናገሩት።
#ሜቴክ እስካሁን 14 ኢንዱስትሪዎችን ሲያስተዳድር የቆየ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ወታደራዊ ምርቶችን የሚያመርቱ አራት ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር እንዲያስረክብ በመንግስት ተወስኗል።
ሆሚቾ ኢንዱስትሪ፣ ደጀን አቪየሽን፣ ጋፋት አርማመንት እና ልዩ ትጥቆች አምራች ኢንዱስትሪ የተባሉትን ነው ለመከላከያ ሚኒስቴር እንዲያስረክብ የተወሰነው።
ቀሪ ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎች በሜቴክ ወይም ወደፊት የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል ስያሜ በሚሰጠው ተቋም ውስጥ የሚተዳደሩ ይሆናል።
ከዚህ ውስጥ ደግሞ ቢሸፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ወታደራዊም የሲቪል ምርቶችንም ስለሚያመርት በማን እጅ መሆን ይኖርበታል የሚለውን ጉዳይ ለማጥናት ኮሚቴ መቋቋሙን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
አዲሱ ኮርፖሬሽንም ሀገሪቱን ወደ ኢንዱስትሪ የሚያንደረድሩ ምርቶች ላይ የሚሰማራ ይሆናል ብለውናል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ።
የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል ስያሜ አግኝቶ እንዲቋቋም የታሰበው ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ካፒታሉ እንደሚሻሻልለትም አቶ አብዱልዓዚዝ አንስተዋል።
ሜቴክ ከአመታት በፊት ሲቋቋም በ10 ቢሊየን ብር የተጠየ ካፒታል ነበር፤ ከዚህ ውስጥ የተከፈለው 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሲሆን፥ አሁን ወታደራዊ ምርት አምራቾቹ ሲቀነሱ የተከፈለ ካፒታሉ ዝቅ ይላል፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም ካፒታሉ ይከፈልለታልም ነው ያሉት አቶ አብዱላዚዝ።
አዲሱ ኮርፖሬሽን ከብቃት ማነስና ከብክነት ጸድቶ ለመሄድም እንደበፊቱ ኮርፖሬሽኑ አቅም ሳይኖር ብዙ ስራን ከመውሰድ ይልቅ፥ የተወሰኑ ዘርፎች ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ የሰው ሀይሉን በአግባቡ ለመጠቀም ታስቧል ብለዋል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia