TIKVAH-ETHIOPIA
" ዞናችን ሰላም ነው ! ...ሰብዓዊ መብት የሚባለው መቼ መጥቶ አጣራ ? " - የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የኢሰመኮን መግለጫ በተመለከ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አባይነህ አበራ " ኢሰመኮ ያወጣው ሪፖርት መሰረት የሌለውና በመረጃ ያልተደገፈ " ሲሉ አጣጥለዋል። " እንደዛ አይነት ነገር (ኢሰመኮ በመግለጫው ያነሳቸው ጉዳዮች) ጋሞ ዞን ውስጥ…
#አርባምንጭዙሪያ
የተለያዩ ጥያቄዎችን አንግበዉ ጫካ የገቡ አካላት በተደጋጋሚ በሰላም እጅ አንዲሰጡ ቢጠየቁም መቀበል አልፈለጉም ሲል የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በአርባምንጭ ዙሪያ የሚስተዋለዉ ግጭት የሰብአዊና ቁሳዊ ጥፋት እያስከተለ ለአመታት ቢዘልቅም አሁንም መፍትሄ እንዳልተገኘለትና ችግሩ የአካባቢዉን ማህበረሰብ የእለትተእለት እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከነዋሪዎች ተረድቷል።
በዚህ ጉዳዩ ላይ በርካታ ጥያቄዎችና ጥቆማዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መቅረቡን ተከትሎ ሁኔታዉን ለማጥራት በቦታው ያለዉን የጸጥታ አካል ለማነጋገር ተሞክሯል።
የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሰላም መስተካከል ስለምን አልቻለም ? በሚል ጥያቄ የቀረበላቸዉ የወረዳዉ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበዉ አዳል ፤ ችግሩን ለመፍታት መንግስት ያቀረበዉ የሰላም ጥሪ በአካባቢዉ ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ አካላት እንዳልተቀበሉትና ይባሱኑ በአካባቢዉ ሰላም ለማስከበር በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ጥቃት መፈጸማቸዉን ይገልፃሉ።
በቅርቡ በደቡብ ክልል አድማብተና ሀይል ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ መሞከራቸዉንና የተወሰነ ጉዳት ቢያስከትሉም በተወሰደባቸዉ የመልስ ምት ተበታትነው መሸሻቸዉን የሚገልጹት ኮማንደር ክበበው ይህ ህዳር 19/2016 ከተፈጸመ ወዲህ የጸጥታ አካሉ አካባቢዉን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ አካባቢዉን ወደሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ያነሳሉ።
አሁን ላይ ከማህበረሰቡ ጋር ጠንካራ ዉይይት እየተደረገ መሆኑንና ጫካ ገብተዉ ችግር የሚፈጥሩ አካላትም እጃቸዉን በሰላም እንዲሰጡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሁሉ ስምምነት ላይ መደረስ እንደተቻለ አመልክተዋል።
በአካባቢው የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ነዋሪዎች ያሉ ሲሆን ችግሮች ሰፍተዉ በአካባቢው የተዘረጋዉን መዋቅር አስካለመቀበልና ከጸጥታ አካላት ጋር እስከመታገል ተደርሷል።
በዚህም የተማረረዉ የአካባቢዉ ህዝብ የችግሩን መጠናከር ተከትሎ ወደአካባቢዉ ከተሞች መሸሽ መጀመሩን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ቤተሰብ አባል የላከው ዘገባ ያስረዳል።
@tikvahethiopia