TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ነፃነት_እና_እኩልነት_ፓርቲ

ፓርቲ እና መንግስት ይለዩ!!

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ገዥው ፓርቲ ድርጅታዊ ስራዎቹን ከመንግስት መዋቅር ውጪ እንዲያካሂድና ከባለሀብቶች ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከመንግስት መዋቅር ውጪ በፓርቲው አደረጃጀት ስር ብቻ እና ብቻ እንዲያካሂድ ጥሪ አቀረበ፡፡

በተመሳሳይ ፓርቲው በፌደራል እና በክልል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከሚሰሩ አባላቱ የሚሰበስበውን የአባልነት መዋጮ ከመንግስት መዋቅር ውጪ በፓርቲው ጽ/ቤቶች እና አደረጃጀት እንዲያከናውን አሳስቧል።

የመንግስት መዋቅርን በመጠቀም የሚደረግ እንቅስቃሴ የፖለቲካ ሜዳውን ያልተስተካከለ የሚያደርግ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎችን የፖለቲካ እንቅስቃሴ አሉታዊ በሆነ መንገድ የሚጎዳ መሆኑን አመልክቷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia