TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#የካቲት11

45ኛው ዓመት ህወሓት የተመሰረተበት የየካቲት 11 በዓል የተለያዩ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊስት ኃይሎች፣ የፌደራልና የክልል መንግስት አመራሮች፣ ነባር ታጋዮች እና ምራሁራን በተገኙበት የፓናል ውይይት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በሌላ መረጃ፦

45 ተኛው ዓመት የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግል የጀመረበት የካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ ከጎረቤት ሀገር ሱዳን የመጡ እንግዶች ጋር የፓነል ዉይይት ተካሂዷል፡፡

#ትግራይቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ መግባትን ጨምሮ " የትኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለማድረግ " በቂ ምክንያት እንዳለው ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው የፕሪቶሪያው ስምምነት አካል የሆኑት የፌደራል መንግሥት እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ " በትግራይ ያለው ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱን እና የፕሪቶሪያ ስምምነት መፍረስ የሚያስከትለውን…
#ትግራይ

" እነዚህ ሰዎች አብደት ላይ መሆናቸውን ሊነገራቸው ይገባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

🚨 " እኔ ልለው የምችለው ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ አስከፊ ነው !! "


የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህም ቃለ ምልልስ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

➡️ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ መግባትን ጨምሮ የትኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለማድረግ በቂ ምክንያት አለው።

➡️ የፌደራል መንግሥት እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በትግራይ ያለው ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱን እና የፕሪቶሪያ ስምምነት መፍረስ የሚያስከትለውን ትልቅ ችግር ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

➡️ የሠራዊቱ አመራሮች የታገዱት ከመንግሥት ውሳኔ ውጪ መላ ሕዝባችንን እና ወጣቱን ወደ ግርግር፤ የፀጥታ ኃይላችንን ወደ እርስ በርስ ግጭት ብሎም ሕዝባችንን ወደማይወጣበት አዘቅት የሚያስገባ አደገኛ እንቅስቃሴ ባለመቆሙ ነው።

➡️ አመራሮቹ " ውሳኔ " ያሉትን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉንም እርምጃዎች መውሰድ በመጀመራቸው እንደታገዱ ሆነዋል።

➡️ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ሰብረው እየገቡ ነው፣ ጊዜያዊ የአስተዳደር ኃላፊዎችን እያነሱ ነው፣ ይህ ደግሞ በሕዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በይበልጥም በራሱ በሠራዊቱ ውስጥ ውዥንብር ፈጥሯል።

➡️ ጥያቄው " ፕሬዝዳንቱን ወይም የካቢኔ አባላትን ከሥልጣን የማንሳት እና አለማንሳት " አይደለም፤ ከሁሉም በላይ በፕሪቶሪያ ስምምነት የተገኘውን ትንሽ ሰላም የማስጠበቅ ነው።

➡️ የውጭ ኃይሎች በዚህ ውስጥ ተሳታፊ ናቸው ብለን የምናምንበት ምክንያት አለን። አሁንም ይህ ውሳኔ ይቆማል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

➡️ የዓዲግራት ከንቲባ ቢሮ ይዘዋል። ይህን ለማድረግ ያቀዱት ዓዲግራት ላይ ብቻ ሳይሆን መቐለ ላይ ማድረግም ይፈልጋሉ።

➡️ የትግራይን ሕዝብ ኃይል በመጠቀም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በሕገወጡ የህወሓት አንጃ ስም መያዝ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው እና ወደ ተጨማሪ ጥፋት የሚያመራ ነው።

➡️ እብደታቸውን ለማስቆም የቻልኩትን ሁሉ ለማድረግ እየሞከርኩ ነው ያለሁት። እብደቱን የማስቆም አቅም አለኝ ወይ ? የሚለው የተለየ ጉዳይ ነው፣ ነገር ግን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ ገብቶ እነዚህ ሰዎች አብደት ላይ መሆናቸውን ሊነገራቸው ይገባል።

➡️ " የወረዳ ምክር ቤቶች እንደገና ሊዋቀሩ ይገባቸዋል " የሚል ጥያቄ ይነሳል በሕግ እና በመመሪያ መፍታት እንደምንችል በግልፅ ተናግሯል።

➡️ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከተናገራቸው እጅግ በጣም አስቂኝ ነገሮች ውስጥ አንዱ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሕግ እና ሥርዓትን ለማስከበር በሚያደርገው ውሳኔ ላይ እንቅፋት ሆኗል" የሚል ነው። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች በሕገወጥ የወርቅ እና የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ወደ እስር ቤት ማስገባት የሚለውን ሃሳብ ሲቃወሙ ቆይተዋል። በትግራይ ሕዝብ ላይ ለተፈፀመው ዘግናኝ ወንጀል ምንም መፍትሔ ሳያበጁ እና አሁን በየመንደሩ ማህተም መንጠቅ ሕግ እና ሥርዓትን እንደማስከበር ተደርጎ መወሰዱ ከንቱ ነው።

➡️ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ግጭት እንዲፈጠር አልፈልግም። የሚፈጠር ከሆነም የትግራይ ሕዝብ የገፈቱ ቀማሽ እንዲሆን አልፈልግም። የትግራይ ሕዝብ በዚህ ዓይነት ውዥንብር ውስጥ እንዲገባ አልፈልግም፣ አንዳንድ ባልደረቦቼ ይህንን ሀሳብ ውስጥ ያስገቡ አይመስሉም፣ ወይም የትኛውንም ክፍተት ለመጠቀም ያሰቡ ይመስላሉ፣ እና እኔ ልለው የምችለው ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ አስከፊ ነው።

#ትግራይቴሌቪዥን #ቢቢሲ

@tikvahethiopia