TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ ፤ ፒያሳ የሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት (ተርሚናል) መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ ፥ " ህብረተሰቡ ደህንነቱ ተጠብቆ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያገኝበትን የከተማ አውቶብስ #ተርሚናል አስጀምረናል " ብሏል።

ቀድሞ በፒያሳ እና አከባቢው ሲሰጡ የነበሩ አስር የከተማ አውቶብስ መስመሮች ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ገብተው በአንድ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩ ተጠቁሟል።

ህብረተሰቡ በሙዚየሙ በ " ምስራቅ ጀግኖች በር "  በመግባት ወደ ፦
- አየር ጤና፣
- ካራ ቆሬ፣
- ቦሌ ቡልቡላ፣
- ሳሪስ፣
- ኮልፌ ቀራኒዮ፣
- አጃምባ፣
- ጀሞ 3፣
- ሃና ማርያም፣
- ቱሉዲምቱ
- ዩኒሳ የሚሄዱ የብዙሃን ትራንስፖርት (አውቶብስ) ማግኘት እንደሚችል የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ጠቁሟል።

@tikvahethiopia