TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
መሪዎቹ በለንደን...🚌

በንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ወቅት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና የሀገራት ተወካዮች #በአውቶብስ እንዲጓጓዙ ሲደረግ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በራሳቸው ጥይት መከላከያ ባላት " ዘ ቢስት " የተሰኘችው ሊሞዚን እንዲጓዙ መደረጉ መነጋገሪያ ሆኗል።

ዛሬ የንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊ ስርዓተ ቀብር ተፈፅሟል።

ለዚሁ የቀብር ስነስርዓት ለንደን የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ተወካዮች ለስነስርዓቱ በአውቶብስ እንዲጓዙ የዩኬ (UK) መንግስት አመራር ሰጥቶ እንደነበር ተሰምቷል።

መንግስት ይህን ያደረገው ከደህንነት አንፃር ሲሆን በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሀገራት መሪዎች በአንድ ጊዜ መገኘታቸው ሁሉም የራሳቸውን መኪና እንዲጠቀሙ ማድረግ ከደህንነት አንፃር የማይታሰብ እንደሆነበት ነው የተነገረው።

ከሌሎች መሪዎች በተለየ ግን የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ባይደን በራሳቸው የግል መኪና " ዘ ቢስት " እንዲጓዙ መደረጉ መነጋገሪያ ሆኗል።

በተለይ የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ፣ የታንዛኒያዋ ሳሚያ ሱሉሁን ጨምሮ አፍሪካ መሪዎች በአንድ ባስ ውስጥ ሆነው የሚታዩበትን ፎቶ ከባይደን ጋር በማነፃፀር " ለአፍሪካ መሪዎች የተሰጠው ዝቅተኛ ክብር " በሚል በርካታ አፍሪካውያን ሲቀባበሉት ውለዋል።

ምንም እንኳን በስፋት የአፍሪካውያን መሪዎቹ አንድ አውቶብስ ውስጥ ያሉበት ፎቶ ቢታይም የቤልጂየሙ ንጉስ እና ንግሥት፣  የስፔኑ ንጉሥ እና ንግሥት ፣ የስዊድን ንጉሥ እና ንግሥት እና የኔዘርላንድ ንጉሥ እና ንግሥት የግል መኪናቸውን አልተጠቀሙም ተብሏል።

የቻይና ልዑካንም በአውቶብስ እንዲጓዙ መደረጉ ተነግሯል።

የመረጃ ምንጭ ዘ ኢንዲፔንደንት እና ሌሎች ፤ ምስል ከሶሻል ሚዲያ ፤ አንደኛው ምስል ቅንብር የKenyans.Co.ke ነው።

@tikvahethiopia