#ሶጌ
ከትናንት በስቲያ አርብ ታህሳስ 19/2016 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ካማሺ ዞን ቦሎ ጅጋንፎይ/ምዥጋ ወረዳ ሶጌ ከተማ ጠዋት ታጣቂዎች ወደ ከተማው በመዝለቅ ከፍተኛ ጥቃትና መድመት ማድረሳቸውን የወረዳው አስተዳደር ገልጿል።
በጥቃቱ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በወረዳው የሚገኙ 2 ባንኮች (የአዋሽ ባንክ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) መዘረፋቸውንም ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ መጠን ያላቸው 8 ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን አመልክቷል።
በወረዳው የነበሩ ጸጥታ አስከባሪዎች ለግዳጅ ወደ ሌላ ስፋራ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ታጣቂዎቹ በቀላቀሉ ወደ ወረዳው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸው ነው የተነገረው።
በዕለቱ ለ3 ሰዓታት ያህል ከተማውን ተቆጣጥረው እንደነበርና በሶጌ ከተማ ውስጥ የሚገኙ አንድ ፖሊስ ጣቢያ መቃጠሉን፣ ሁለት ባንኮችም መዘረፋውንና ሌሎችም በርካታ የመስሪያ ቤት ንብረቶች መዘረፋቸውን ወረዳው አመልክቷል።
በዛሬው እለት በከተማው መረጋጋት መስፈኑን ተከትሎ ከአካባቢው ሸሽተው የነበሩ ነዋሪዎች ሲመለሱ መዋሉ ተመላክቷል።
ቃላቸውን የሰጡ የወረዳው ነዋሪዎች በዕለቱ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ስለነበር አብዛኛው የከተማዋ ነዋሪ አካባቢውን ለቀው ሸሽተው እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በወረዳው አንድ ፖሊስ ጣቢያ መቃጠሉንና የቁም እንስሳትን ጨምሮ የንብረት ዝርፍያ መፈጸሙን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል፡፡
5 ተሸከርካሪዎች በአንድ ስፋራ መቃጠሉን የገለጹ ሲሆን መጠናቸው ያልታወቀ ሌሎች የወረዳው ተሽከርካሪዎች በታጣቂዎች መወሰዱን አብራርተዋል፡፡
ጥቃቱን በመሸሽ ላይ የነበሩ 4 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን እንደሚያውቁም ጠቁመዋል፡፡
በወረዳው በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ሐይሎች መግባታቸው የገለጹት ነዋሪዎች በአካባቢው አሁንም ወደ ቤታቸው ያልተመለሱ የሸሹ ነዋሪዎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡
አርብ ዕለት በሶጌ ከተማ የደረሰውን ጥቃት በወረዳው አቅራቢያ ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸው የሼኔ ታጣቂዎች መፈጸማቸውን የወረዳው አስተዳደር ገልጿል።
በካማሺ ዞን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ላይ ከደረሱ ወዲህ በአካባቢው ሰላም መስፈኑን የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።
ይህ መረጃ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia