#update የባለስልጣናት ሀብት⬇️
የፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በመጀመሪያ ዙር የ450 የመንግሥት ባለስልጣናትና ሠራተኞችን ሃብት ለህዝብ -ክፍት ለማድረግ የሶፍትዌር #ሙከራ ላይ መሆኑን አሳውቋል።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ አየልኝ ሙሉዓለም እስካሁን የ150 ሺህ ባለስልጣናት እና የመንግስት ሠራተኞች ሃብት በመመዝገብ ለህዝብ ክፍት የማድረጊያ ሶፍትዌር ከህንድ ኩባንያ ጋር በመተባበር ወደ ትግበራ መግባቱን ገልጸዋል።
የሶፍትዌር ትግበራው ለሙስና የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ የሆኑ ተቋማት ሃላፊዎችንና ሠራተኞችን ሀብት ይፋ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።
እስካሁን የ80 ግለሰቦች የሀብት መረጃ ወደ ሶፍትዌሩ መመዝገባቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ የማሻሻያ ስራዎች ከተጠናቀቁ በኋላ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ተናግረዋል።
ሙከራው ሲጠናቀቅ ማንኛውም ግለሰብ የሚፈልገውን የሀብት ምዝገባ መረጃ በስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ቢሮዎች በአካል ቀርቦ መመልከት እንደሚችልም ነው የጠቀሱት።
የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት የሚሆንበት ጊዜ ባይጠቀስም በቅርቡ እንደሚጀመር ግን ኮሚሽነር አቶ #አየልኝ ጠቁመዋል።
የሀብት ምዝገባ መረጃዎች እስከዛሬ ለህዝብ ክፍት ያልተደረገው ከስራው ውስብስብነትና በሶፍትዌሩ አለመጠናቀቅ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ላለፉት ዓመታት በሰው ሃይል እጥረት፣ በስራው ውስብስብነትና አቅም ማነስ ምክንያት የሀብት ማጣራት ስራ እንዳልሰራም ነው ኮሚሽነሩ ያነሱት።
አቶ አየልኝ በዘንድሮው በጀት ዓመት የ80 ግለሰቦች ሀብት እየተጣራ እንደሚገኝ ገልጸው ከዚህም ውስጥ የ23ቱ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

“ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱን ለመፍጠር እንጂ በስፋት ለማምረት አቅም የላትም” - ፕሮፌሰር ጆን ቤል
ዩናይትድ ኪንግደም ኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] ለመከላከል የሚያስችል የክትባት መጠን ለማምረት አቅም እንደሌላት ነገር ግን ክትባቱን ለመፍጠር “አመቺ ቦታ” መሆኗን የአገሪቱ መንግሥት ግብረ ኃይል አባል ፕሮፌሰር ጆን ቤል ተናግረዋል።
በቅርቡ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማምረት ይቻል እንደሆነ የተጠየቁት ፕሮፌሰሩ በሰጡት መልስ ላይ ጥያቄው መሆን ያለበት ውጤታማ ይሆናል ወይ ነው ካሉ በኋላ “እስከ ግንቦት ድረስ ሊገኝ አይችልም” ሲሉ ወቅቱ ገና መሆኑን አመልክተዋል።
"ዋናው ጉዳይ ተገቢው #ሙከራ መደረጉ ላይ ነው፤ ምክንያቱም ክትባትን በተመለከተ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑ በጣሙን አስፈላጊው ነገር ነው” ሲሉ ፕሮፌሰር ቤል ተናግረዋል።
"ነገር ግን በግንቦት ወር አጋማሽ ወይም መጨረሻ ላይ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል ማስረጃ ማግኘት #ከቻልን ሥራው የሚጀመር ይመስለኛል። ከዚያም ነሐሴ አጋማሽ ላይ ፍጻሜን ያገኛል” ሲሉ አመልክተዋል።
ምንጭ ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

አጫጭር መረጃዎች፦
- በUK በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ክትባት #ሙከራ ለሁለት በጎ ፍቃደኞች በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል።
- በፈረንሳይ ተጨማሪ 516 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 21,856 ደርሷል።
- በጣልያን የሟቾች ቁጥር ጨምሯል። ባለፉት 24 ሰዓት 464 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። ተጨማሪ 2,646 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 638 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተድርጓል። ቁጥሩ ባለፉት 2 ቀናት ከተመዘገበው ዝቅተኛ ነው። በሀገሪቱ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 18,738 ደርሷል።
- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ48,000 በልጧል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ865,000 በልጧል።
- በደቡብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓት 9,796 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ 318 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3,953 ደርሷል።
- በሴኔጋል ባለፉት 24 ሰዓት 387 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 37 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 479 ደርሰዋል። 257 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
- በሩዋንዳ 1,343 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 154 ደርሰዋል። በሌላ በኩል ተጨማሪ 3 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 87 ደርሰዋል።

የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ በUK ፦
- በዛሬው ዕለት በዩናይትድ ኪንግድም የኮሮና ቫይረስ ክትባት #ሙከራ ለሁለት በጎ ፍቃደኞች ተሰጥቷል።
- ዛሬ በሙከራ ደረጃ የተሰጠው ክትባት በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ነው።
- ይህ የኮሮና ቫይረስ ክትባት 80% ውጤታማ እንደሚሆን በሳይንቲስቶች ተስፋ ተጥሎበታል።
- የUK ጤና ሚኒስትር ማት ሀንኮክ ከቀናት በፊት በሰጡት አስተያየት "ስለ ሂደቱ እርግጠኛ መሆን አደማይቻል ፤ የክትባት ዝግጅት የሙከራ እና የስህተት ሂደት" መሆኑ አስገንዝበው ነበር።

#ጥንቃቄ
ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሀገራችን ድረ-ገጾች ላይ የመረጃ መበርበር #ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል የተባለ ቡድን አሁን ላይ 37 ሺህ በሚደርሱ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።
ይህን ያሳወቀው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ነው።
ተቋሙ ባወጣው መረጃ "ሳይበር ሆርስ ግሩፕ" የተሰኘው የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች ላይ ለመልቀቅ ዝግጅት ማድረጉ እንደተደረሰበት ገልጿል።
ቫይረሱ "ብላክ ፒራሚድ ዋር" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን 37 ሺህ በሚደርሱ የሀገራችን ኮምፒውተሮች ላይ ማነጣጠሩ ተገልጿል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሁሉም የሳይበር ምህዳሩ ተጠቃሚዎች ተገቢውን የሳይበር ደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
@tikvahethiopia