TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል #ልዩነትንና #መከፋፈልን ለመፍጠር በተለያየ መንገድ የሚደረገውን አፍራሽ እንቅስቃሴ መላው ዜጋ በጋራ መታገል አለበት ሲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ #ለማ_መገረሳ ተናገሩ። አቶ ለማ ይህንን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በተገኙበት ከቡኖ በደሌ ዞን ነዋሪዎች ጋር በበደሌ ከተማ ዛሬ በተካሄደው ውይይት ላይ ነው። በዚሁ ወቅት አቶ ለማ የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያን ለመገንባት ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሏል፤ በአሁኑ ወቅትም አንድነቷን አስጠብቆ ለማቆየት ከሌሎች ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ ይሰራል ብለዋል። “የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያን አንድነት የማስጠበቅ ግዴታ አለበት” ሲሉም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia