TIKVAH-ETHIOPIA
#ፎቶ ⬆️ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ደረጃ እያካሄደው የሚገኘውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት 3ኛ ቀን መርሀ ግብር ዛሬ አከናውኗል። ዛሬ በከተማ ደረጃ " #ታዋቂ ፣ #ተጽዕኖ_ፈጣሪ " ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ተገኝተው በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ስለ ሂደቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል ተብሏል። በተመሳሳይ በተለየ ቦታ ላይ ከ112 ወረዳዎች ከ11 የህብረተሰብ የተወጣጡ ተሳታፊዎች በየማኅበረሰብ ክፍላቸውን…
#Update
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ለ7 ቀናት ሲያደርገው የነበረውን የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ዛሬ አጠናቋል።
በማጠቃለያው መርሐ ግብር ላይ የተገኘው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቧል።
Q. የ7ቱ ቀናት በአ/አ ደረጃ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደትና ውጤቱ ምን ይመስላል ?
ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ፦
“ ትኩረቱ የነበረው 3 ነጥቦች ላይ ነው።
የመጀመሪያው ትኩረት በቅንነት ፣ ያለአንዳች መከልከል ፣ ያለመሸማቀቅ ሕዝባችን እንዲወያይ ነበር።
ሁለተኛው ደግሞ የአካባቢን ሁኔታ መሠረት ያደረገ ከጀንዳ ማቅረብ ነበር።
ሦስተኛው ተወካይ መምረጥ ነበር። በአጠቃላይ ሁሉም የተሳካ ነበር። ”
Q. በአ/አ ደረጃ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ምንድን ናቸው ?
ዶክተር ዮናስ አዳዬ ፦
“ አጀንዳዎቹን በሙሉ ሰብስበን፣ ኮሚሽኑ ካጠናቀረ በኋላ እነዚህ የአዲስ አበባ እነዚህ የእነዛ ብሎ መናገር ይሻላል።
አሁን ባለበት ሁኔታ ግን መናገሩ አስፈላጊ አይደለም። ምክንያቱም ሌሎች የሚያስቡትን ማበላሸት ስለሚሆን። ”
Q. በአዲስ አበባ የተደረገው የተወካዮች መረጣ ከኃይማኖትና ፆታ ስብጥር አንፃር ምን ይመስላል ?
ዶክተር ዮናስ አዳዬ ፦
“ እኛ እስከገባን፣ እስካደረግነው ሥራችን ድረስ ፦
° ፆታን፣
° አካል ጉዳተኝነትን፣
° ሃይማኖትን
° የማህበረሰብ ክፍሎችንም፣ ሌላው ቀርቶ የብሔር ስብጥርን የወከለ ይመስላል።
ሴቶችን ለማካተት ተብሎ የታቀደው 30 በመቶ ነው።
በአገራችን የሴቶቻችን ብቃት ምን ያህል ነው? ምን ያህሉ ተማሩ ? በተለያዩ ዘርፎች ሴቶቻችን ብዙ አልተማሩም። ስለዚህ 50 በመቶ ብንል እንዋሻለን። ”
Q. ኢሕአፓ ከምክክሩ እንዳገለለ፣ ኦፌኮና ኦነግ በምክክሩ ዙሪያ ቅሬታ አላቸው። ከጅምሩ የሚስተዋሉ እንዲህ አይነት ተቃርኖዎች ምክክሩን አያደናቅፉትም ? ኮሚሽኑ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየሰራ ነው ?
ዶክተር ዮናስ አዳዬ ፦
“ ስንጀምር ከ60 ፓርቲዎች አብረውን ለመስራት የተስማሙት 2 ወይም 3 ፓርቲዎች ነበሩ። አሁን ደግሞ የቀሩት 3 ወይም 4 ናቸው። 50 ፓርቲዎች ከእኛ ጋር እየሰሩ ነው።
ለምን ? ከተባለ አካሄዳችንን አይተዋል። አካታች፣ ለማንም ያልወገንን ግን ለኢትዮጵያ የወገን፣ ለእውነት የቆምን መሆናችንን ተገንዝበው መጥተዋል።
አሁንም #ለኦፌኮም #ለኦነግም ደብዳቤ ጽፈን ሰጥተናል እንዲመጡ። እና እነርሱ ባይመጡም ሌሎቹ አብረዋቸው የነበሩ እየመጡ እንዳሉ ማዬት ይቻላል።
እንደዚህ አይነት አለመግባባቶች ካሉ፣ ቢኖሩም ብዙም አይገርመንም። ምክክሩም ያስፈለገው እንዲህ አይነት መከፋፈል ስለነበረ ነው። ”
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia