TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#DStvEthiopia

⚽️የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከ5 ቀናት በኋላ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ!

አዳዲሱ ተጫዋቾች ያስፈረሙት ቡድኖች ሊጉን ለመጀመር ዝግጁነታችውን አሳውቀዋል!

🤔እናንተስ ከሊጉ የትኛውን ተጫዋች ለማየት ጓግታችኋል?

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን  ወደ ሜዳ ያሳድጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#Ethiopia

ዛሬ ፓሪስ ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት ሦስት የፍጻሜ ውድድሮች ይደረጋሉ።

አሁን 3:00 ለይ የወንዶች የማራቶን ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ፦

🇪🇹 በአንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
🇪🇹 በአትሌት ዴሬሳ ገለታ
🇪🇹 በአትሌት ታምራት ቶላ ትወከላለች።

ምሽት 2:50 የወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ የሚካሄድ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ፦

🇪🇹 በአትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት
🇪🇹 በአትሌት አዲሱ ይሁኔ
🇪🇹 በአትሌት ቢኒያም መሀሪ ትወከላለች።

ምሽት 3:15 የሴቶች 1500 ሜትር ፍፃሜ ይደረጋል ፤ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ
🇪🇹 በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 በአትሌት ድርቤ ወልተጂ ትወከላለች።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
🔈 #የመምህራንድምጽ

° “ የደመወዝና የቤት ችግርን በተመለከተ የተገባልን ቃል አልተፈጸመም ” - የዩኒቨርሲቲ መምህራን

° “ ተደራጅተው መጠየቅ ነው ጠቃሚ የሚሆነው ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር


የመኖሪያ ቤት ግንባታ እና የደመወዝ ጭማሪን በተመለከተ ተገብቶልን የነበረው ቃል እስካሁን አልተፈጸመልንም ሲሉ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰሙ።

" ምንም እንኳን በይፋም ባይሆንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ፤ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት ስብሰባ ቃል ገብተው ነበር " ያሉት መምህራኑ ሆኖም ጭማሪ እንዳልተደረገላቸው ገልጸዋል፡፡

ከጭማሪው ጋር በተያያዘ ካሁን በፊት በጠቅላይ ሚንስትሩ ትዕዛዝ  ከመምህራን ማህበር ፥ ከትምህርት ሚንስትር እና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተዉጣጣ ኮሚቴ ተሰይሞና ተጠንቶ ተግባራዊ ሊደረግ የነበረ ባለ ሶስት አማራጭ የደሞዝ ስኬል አማራጭ እንደነበር አንስተዋል።

" የገንዘብ ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ይህ ጥናት ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ለተወካዮቻችን ገልጸው የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ አልተደረገም " ብለዋል።

" ከዛ በኋላ ህዳር 26 ጀምሮ አድማ ተደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ጥር 2015 ዓ.ም ላይ ሐምሌ 1/2015 ጀምሮ ጭማሪ ይደረጋል ያሉ ቢሆንም እስካሁን የተደረገ ጭማሪ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" በሀገራችን ከፍተኛ ወጭ ወጥቶበት ለዩኒቨርሲቲ መምህራን የተጠና ደመወዝ ተግባራዊ ሳይደረግ ቀርቷል። " ያሉት መምህራኑ ተግባራዊ እንደማይደረግ ከታወቀ ፦
° ጥናቱን ለምን አጠኑት ?
° ለምንስ ከፍተኛ ወጭ ወጥቶ እንዲጠና ተደረገ ?
° ከተጠና በኋላስ ለምን ተግባራዊ ሳይደረግ ቀረ ?
° ከአሁን በፊት የተጠናውን ጥናት ተትቶ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከመጡ ጀምሮ ባለሙያ መድቤ እያስጠናሁ ነው ያለሁት ጥናት በሚቀጥለው ህዳር 2017 ይጠናቀቃል ማለት ምን ማለት ነው ? ሲሉ ጠይቀዋል።

እንዲሁም ነሐሴ 30/2015 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር አመራሮች በተገኙበት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዩኒቨርቲ መምህራን የቤት ችግር በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ መግለጻቸውን ማኀበሩ በወቅቱ ማስረዳቱን አውስተዋል፡

ቃል ሲገባላቸው ቢቆይም እስካሁን በተግባር የተገለጸ ነገር እንደሌለ፣ በዚህም የኑሮ ውድነቱ መቋቋም እንዳልቻሉ አስረድተው፣ " የደመወዝና የቤት ችግርን በተመለከተ የተገባልን ቃል አልተፈጸመም " ሲሉ አማረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም መምህራኑ ላደረባቸው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ለመሆኑ መምህራኑ ተገብቶልን ነበር ያሉት ቃል በተግባር ከምን ደረሰ ? ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር (ኢመማ)ን ጠይቋል፡፡

የማኀበሩ ፕሬዚንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ምን ምላሽ ሰጡ ?

" ዩኒቨርሲቲ ላይ አንዳንድ ከእሳቸው (ከጠ/ሚ አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ማለታቸው ነው) ጋር ያወራናቸው ገዳዮች ነበሩ፡፡

ከክልል ርዕሳነ መስተዳድር ጋር አውርቻለሁ እንሄድበታለን ብለው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን በተደጋጋሚ ማግኘት አይቻልም፣ አገሪቷ ያለችበት ኮሚትመንትም ብዙ ነው፡፡

እንደዛም ሆኖ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ከከተማ አስተዳደር ጋር ተመካክረን ችግሩን የፈቱበትን ሁኔታ ሼር እየተደራረጉ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡

ስለዚህ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ያለውን የመምህራን ቅሬታ ፈርዘር የምንሄድበት ነገር እንዳለ ይሰማኛል። " ብለዋል።


ለቅሬታው መፍትሄ ለመስጠት የተኬደበት ነገር አለ ? የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጭራሽ ጥያቄያችን ተዘንግቷል የሚል ቅሬታ አላቸው ፤ ለሚለው ጥያቄያችን ፕሬዚዳንቱ ምላሽ ሰጥተዋል።

" እኛ መቼም ችግሩ እንዲፈታ ነው የምንፈልገው፡፡ ያ ደግሞ እንዲሆን የራሳችንን ክትትል ነው የምናደርገው፡፡ ወዲያው ደግሞ የሚፈለገው ሁሉ ላይሆን ይችላል።

እሳቸው (ጠ/ሚ አቢይ (ዶ/ር) ማለታቸው ነው) ያሉት ነገር አለ፡፡ እኛም ያልነው አለ፡፡ ከምን ደረሰ? እንዴት እንፍታ? ብለን መከታተላችን አይቀርም፡፡ ግን ደግሞ ትምህርት ሚኒስቴርም የራሱን አስተዋጽዖ ቢያደርግ መልካም ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚያዋጣቸው በየራሳቸው ማኀበር በየኒቨርሲቲ ደረጃ እደረጀን ነው ባልተደራጁባቸው እንዲደራጁ፣ ተደራጅተው መጠየቅ ነው ጠቃሚ የሚሆነው " ብለዋል።

ከዩኒቨርሲቲ በታች ባሉ የትምህርት ተቋማት የመምህራን የቤት ችግር እየተፈታ መሆኑን ማኀበሩ ያስረዳ ሲሆን፣ ከመምህራኑ ቅሬታ ጋር በቀጣይ ይቀርባል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ  : ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም በተለያዩ የግል ባንኮች ያለው የዛሬው ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ከላይ ተያይዟል።

(ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ/ም)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣ በአትሌት ዴሬሳ ገለታ ፣ በአትሌት ታምራት ቶላ የተወከለችበት የፓሪስ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር እየተካሄደ ይገኛል። Via @tikvahethsport @tikvahethiopia
#Ethiopia የወንዶች ማራቶን ሊጠናቀቅ 9 ኪሎ ሜትር ይቀረዋል።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ታምራት ቶላ እና ደሬሳ ገለታ ውድድሩን ከፊት ሆነው በመምራት ላይ ይገኛሉ።

ወቅታዊ ደረጃቸው 1ኛ ታምራት ቶላ ደሬሳ ገለታ 2ኛ ናቸው።

ታምራት በርቀት እየመራ ነው። ጥሩ ጥንካሬና ጉልበት ያለውም ይመስላል።

መጨረሻውን ያሳምረው። ውድድሩ በዚህ ካለቀ የወርቅ ሜዳሊያ ልናገኝ እንችላለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ 🥇 ወርቅ አገኘች !! @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ወርቅ አገኘች።

ሀገራችን በኦሎምፒኩ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ በማራቶን በጀግናው አትሌትላችን ታምራት ቶላ አማካኝነት አግኝታለች።

ምንም እንኳን በፓሪስ እየተመዘገበ ያለው ውጤት አንገት የሚያስደፋ ቢሆንም ዛሬ በወንዶች ማራቶን የተገኘው ውጤት የሚያኮራ ነው።

አትሌት ታምራት እጅግ በሚደንቅ ብቃት ነው ወርቁን ወደ ኢትዮጵያ እጅ ያስገባው።

አትሌት ታምራት ተጠባባቂ የነበረ ሲሆን የአትሌት ሲሳይ ለማን መጎዳት ተከትሎ ነው በውድድሩ ሊሳተፍ የቻለው።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
#Ethiopia

በማራቶን ውድድር ላይ " ተጠባባቂ ነህ " ተብሎ የተያዘውና ለውድድሩ የተመረጠ ሌላ አትሌት መጎዳቱን ተከትሎ ሀገሩን ወክሎ የተሳተፈው ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ወርቅ ማምጣት ብቻ ሳይሆን በሚደንቅ ብቃት የኦሎምፒክ ሪከርድም ጭምር ነው የሰበረው።

ጀግናው አትሌት ታምራት ከአትሌት ገዛኸኝ አበራ በኋላ (ከ24 ዓመታት በኃላ) ነው የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገራችን ያስገኘው።

ሌላው አንጋፋው ኢትዮጵያ ሁል ጊዜ በስራው የምታመሰግነው የ42 ዓመቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ ደረጃ ይዞ እጅግ ከባድ የነበረውን የፓሪስ ማራቶን አጠናቋል።

አትሌት ደሬሳ ገለታም 5ተኛ ደረጃ በመውጣት እጅግ በጣም አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት አስመዝግቧል።

ምንም እንኳን ዛሬ በወንዶች ማራቶን የተገኘው ውጤት አስደሳችንና የሚያኮራ ቢሆንም በፓሪስ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ኢትዮጵያን የሚመጥናት አይደለም።

በጭቅጭቅና ንትርክ በተሞላው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ያገኘችው እስካሁን 3 ሜዳሊያ ብቻ ነው። 1 ወርቅ እና 2 ብር ብቻ።

የአትሌቲክሱ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ ያሉ ችግሮች እና ኢትዮጵያን ዝቅ ያደረጉ ነገሮች ሁሉ ተፈትሸው መለወጥ እንዳለባቸው የፓሪስ ኦሎምፒክ በግልጽ አመላክቷል።

ከሚዲያ በዘለለ ስለዚህ ሀገር አትሌቲክስ ሁሉም " የሀገር ክብር ያሳስበኛል " የሚል ቁጭ ብሎ ተነጋግሮ በአስቸኳይ ለውጥ ማምጣት አለበት። እንዲህ ከቀጠለ በዓለም ደረጃ የነበረን ክብር የማናጣበት ምክንያት የለም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

" የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን የላኩት ማስረጃ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ምክትል ሊቀመንበርና  የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅሬታ ደብደቤ አቀረቡ።

ምክትል ሊቀ-መንበሩ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም በህወሓት " በልዩ ሁኔታ " የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ዙሪያ ነው ለቦርዱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት።

" በህወሓት የምዝገባ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተላከው ደብዳቤ ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው በግለሰቦች የተላከ ነው " ብለዋል።

ም/ ሊቀ መንበሩ አቶ ጌታቸው ፥ " የተወሰኑ ግለሰቦች ከድርጅቱ አሰራር ውጪ በቡድን በመሆን የፈረሙት እንጂ እኛ ለምዝገባ ብለን የፈረምነው ማንኛውም ሰነድ የለም " ሲሉ አክለዋል።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓት አስመልክቶ ለተወሰኑ ግለሰቦች የሰጠው እውቅና የተጭበረበረ በመሆኑ ዳግም ሊያጤነው ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia