TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthEthiopia " በእኛ ደረጃ የደረሰን ኦፊሻል መረጃ የለም። ቅሬታም የለም። ስለዚህ ዞኖቹን አናግራቸዋለሁ " - አቶ ወገኔ ብዙነህ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ውስጥ በመዋቅር ጥያቄ ምክንያት " ወጣቶች በጅምላ ታስረው ይገኛሉ " ሲሉ የታሳሪ ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። አንድ ለደኅንነታቸው ሲባል ሥማቸው እዳይጠቀስ የጠየቁ ምንጭ፤ በቅርቡ ተዋቀረ ወደተባለው ኮሬ ዞን (የቀድሞው…
#Update
" ተበደልኩ የሚል አካል እኛ ጋ መምጣት ይችላል " - አቶ ወገኔ ብዙነህ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ዳኖ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ' ለምን የመዋቅር ጥያቄ ጠየቃችሁ ' በሚል በፖሊስ እየተደበደቡ እየታሰሩ ስለመሆናቸውን ገልጸዋል።
ሰዎች ሸሽተው ጫካ ገብተዋልና የክልሉ መንግሥት ይድረስልን ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ፦
- ኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ማታ አንድ ሰው ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ወደ አርባ ምንጭ ሪፈር ተጽፎለታል።
- ኅዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከትምህርት ቤት ሲመለስ የነበረ አንድ ተማሪ ተደብድቧል። በተመሳሳይ በእርሻ ቦታ የነበረ አንድ አርሶ አደር ተደብድቧል።
- በአንድ ቀን ሰባት ከዎች ታስረዋል። ከዞኑ የመጡ ፓሊሶች ናቸው እንዲህ ያደረጉት ብለዋል።
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንድ አባት ልጃቸው ሰሞኑን ያልጥፋቱ እንደታሰረ ገልጸው፣ የተማሩና ለማኅበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ባለስልጣናት ጭምር ' እናንተ ናችሁ ሕዝቡን የመዋቅር ጥያቄ እንዲያነሳ የምታደርጉት ' ተብለው እየታሰሩ እንደሆነ፣ አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት ድርቅ ጉዳት እንዳደረሰባቸው አሁን እንኳ የእርሻ ወቅት ቢሆንም በጸጥታ ምክንያት ማረስ፣ ማረም እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
ፖሊስ የሚያሳድዳቸው ለምን እንደሆነ እንዲያብራሩ ሲጠየቁም ከአምስት በላይ ነዎሪዎች ምላሽ የሰጡት፣ " የመዋቅር ጥያቄ ለምን ጠየቃችሁ ? " በሚል ነው። የመዋቅር አደረጃጀት ሲሰሩ ደግሞ ሕዝቡን አላወያዩም፣ አሁንም እንዲያወያዩን እንፈልጋለን ሲሉ ነው።
ነዋሪዎች " እየደረሰብን ነው " ያሉትን ጥቃት በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ ጥያቄ አቅርቧል።
የሰላምና ጸጥታ ቢሮው ኃላፊው ምን አሉ ?
አቶ ወገኔ ፤ ፖሊስ እያደረሰው ነው ስለሚባለው ጥቃት መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል።
" ተበደልኩ የሚል አካል እኛ ጋ መምጣት ይችላል " ብለዋል።
በደብዳቤ ጭምር ጥያቄ እንዳቀረቡላችሁ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል ፤ ለዚህስ ጉዳይ ምን አይነት ምላሽ አላችሁ ? ለሚለው ጥያቄ፦ " በፍጹም የደረሰኝ የለም፣ ስልኬን ያውቁታል ቴሌግራም ላይ ጥያቄያቸውን አታች ያድርጉልኝ " ሲሉ ተናግረዋል።
የመዋቅር ጥያቄን በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ ፤ " እኔ ነኝ ዞኑን አደራጅቼ ላውንች አድርጌ የመጣሁት። መንገድ ቆፍረው ወግተው በሌላ መንገድ ነው የወጣሁት። እንደዚህ አይነት ኬዞች እንዳሉ አውቃለሁ " ብለው፣ ፖሊስ አደረሰው ስለሚባለው ጥቃት የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ፣ ሁኔታውን ግን እንደሚከታተሉ አስረድተዋል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ወጣቶች በጅምላ እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች በገለጹት መሠረት ጠይቀናችሁ ክትትል እናደርጋለን ብላችሁ ነበር ለምን ችግሩን መቅረፍ አልተቻለም ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ወገኔ፣ " ከዚህ በፊት ከእናተ ባገኘነው ጥቆማ ኮሚዩኒኬት አድርገን ' መንገድ የዘጉ፣ መሳሪያ አውጥተው ለማስፈራራት የሞከሩ የተወሰኑ ሰዎች ላይ ሕግ የማስከበር ሥራ ሰርተናል የሚል ነው እንጂ የአስተዳደር ጥያቄ መጠየቅ በእንደዚህ አይነት መንገድ በፍጹም የወሰድነው እርምጃ የለም ' የሚል ነው ከዞኑ እያገኘሁት ያለሁት ምላሽ " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ የዞን አመራሮችን ለመነጋገር ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካም። አሁንም የዞን አመራሮችን ምላሽ ለማግኘት እንጥራለን።
@tikvahethiopia

#MekelleUniversity
የመቐለ ዩኒቨርስቲ በ29ኛ ዙር ከ2000 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ። ከተመራቂ ተማሪዎች 40 በመቶ ሴቶች ናቸው።
ዩኒቨርስቲው ከተማሪዎች ምረቃ ጎን ለጎን 29ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉም አክብረዋል።
በምረቓው ስነ-ሰርአት የዩኒቨርስቲው ፕረዚደንት ተወካይ ዶ/ር ዓብደልቃድር ከድር ንግግር አድርገው ነበር።
ባለፉት 3 አመታት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት የደረሰው ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት እጅግ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰዋል።
ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በተገኘው አንፃራዊ እርጋታ ዪኒቨስቲው ተስተጓጉሎ የነበረውን የመማር ማስተማር ስራ ፈጥኖ መጀመሩን ገልጸዋል።
የ17 ወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው የነገ ተስፋ አንግበው ወደ ስራ በመመለስ ተማሪዎችን ለዛሬ ምረቃ ላበቁ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።
ዩኒቨርስቲው የድህረ ጦርነት እቅድ በማዘጋጀት ፤ ከፌደራልና በአገሪቱ ክልሎች እንዲሁም በውጭ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲ በመነጋገርና በመፃፃፍ ያለፉት 3 የጦርነት አመታት የሚያካክስ ስራ ለመስራት በከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል።
ዩቨርሲቲው በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በመረዳት የፌደራል መንግስት የመደበለት አነስተኛ በጀትና የሰራተኞች ውዙፍ ደመወዝ በአፋጣኝ በመመለስ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ስራውና ተልእኮው እንዲመለስ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር ሰክሬተሰሪያት ሃላፊና የመቐለ የኒቨርስቲ ቦርድ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በበኩላቸው ፤ መቐለ ዩንቨርስቲ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰበትን ጉዳት ተቋቆቁሞና ወደ ስራ ተመልሶ በአጭር ጊዜ ይህን የመሰለ ድንቅ የምረቃ ስነ-ሰርአት ማዘጋጀቱ ነገ ለመድረስ ያቀደውን እንደሚያሳካ እንደ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።
ይህንን የሆነው ለሰላም በተከፈለው እጅግ ወድ ዋጋ በመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች ሆኑ ሌላው የማህበረሰብ ክፍል የተጀመረው ሰላም ስር እንዲሰድ በተሰማሩበት ሁሉ ሰላምና ልማት መስበክ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዩኒቨርስቲው በ29 አመታት ጉዞው የዛሬ ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁ ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያስረዳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#ATTENTION🔊
በዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ በመሙላቱ / ከመደበኛ ፍሰቱ ወጥቶ ሞልቶ በመፍሰሱ ዜጎቻችን እየተጎዱ ነው።
እንደ ዳሰነች ወረዳ አስተዳደር መረጃ ፦
- በ34 ቀበሌያትና በ7 ደሴቶች የሚኖሩ 79,828 ቤተሰብ አባላት በወንዙ ሙላት የተጎዱ ተጎድተዋል።
- በወረዳው ካሉ 40 ቀበሌያቶች 34ቱ ቀበሌያት በውሃ የመዋጥና የመከበብ አደጋ ያጋጠማቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 27ቱ ቀበሌያት ሙሉ በሙሉ በውሃ ሙላት ተውጠዋል ፤ 7ቱ ቀበሌያት ደግሞ በቀጣይ ስጋት ውስጥ ናቸው።
- በኦሞ ወንዝ ሙላት ሳቢያ 1,435.75 ሄ/ር በመስኖ የተዘራ ሰብልና 123,000 ሄ/ር የእንስሳት የግጦሽ መሬት ሙሉ በሙሉ በውሃ ተሸፍኗል።
- በደሴቶች ውስጥ የነበሩና በውሃ ሙላት የተከበቡ እንስሳት ብዛት 2,993,135 ሲሆን ከዚህ ውስጥ አስካሁን ከውኃ ሙላት የወጡ 889,454 እንስሶች ናቸው።
- በውሃ መጥለቅለቁ 8 የሰው ጤና ኬላዎች፣ 1 ጤና ጣቢያ፣ 6 ትምህርት ቤቶች፣ 6 የእንስሳት ጤና ኬላ፣ 5 የአርብቶ አደር ማሰልጠኛ ጣቢያ ፣ 4 የመኖ ቤል እስቶር እና በ14 ቀበሌያት በስራ እድል ፈጠራ በማህበራት ተደራጅተው ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት ተበድረው ወደ ስራ የገቡ እና በፕሮጀክት የታቀፉ 32 ማህበራትና 15 ሼዶች ሙሉ ለሙሉ በውሃ ሙላት ተውጠዋል፤ ስራም አቁመዋል።
በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመተባበርና በመቀናጀት አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጡ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

#እንድታውቁት
ከለሊት 11 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ መንገዶች ይዘጋሉ።
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ነገ በአዲስ አበባ መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ የሚካሄድ የሩጫ ውድድር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ፡-
- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ ሃያ ሁለት ዘሪሁን ህንፃ ላይ፣
- ከቦሌ መድሀኒአለም ወደ ኡራኤል አትላስ መብራት ላይ፣
- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣
- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ላይ
- ከጎፋ ማዞሪያ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሀር ጨርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ፣
- ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ከባድ መኪና ቡልጋሪያ መዞሪያ ሌሎች ገነት ሆቴል ላንድማርክ ላይ፣
- ከአፍሪካ ህብረት ወደ ንግድ ምክር ቤት ጠማማ ፎቅ ላይ፣
- ከሳርቤት ወደ ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት ጥይት ቤት፣
- ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ ክፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ፣
- ከኑር ህንፃ ባልቻ መስቀለኛ ኑር ህንፃ አካባቢ ከተስፋ ኮከብ ት/ቤት ወደ ልደታ ኮንዶምኒየም ተስፋ ኮከብ ት/ቤት ላይ፣
- ከፈረሰኛ ወደ ጌጃ ሰፈር ፈረሰኛ መብራት ላይ፣
- ከሞላ ማሩ ወደ ጌጃ ሰፈር ሞላ ማሩ ላይ፣
- ከበርበሬ በረንዳ ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በርበሬ በረንዳ፣ ከጎማ ቁጠባ ወደ አረቄ ፋብሪካ ፣ወደ ሰንጋ ተራ እንዲሁም ወደ ብሄራዊ ቴአትር ጎማ ቁጠባ ላይ፣
- ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት ሜትሮሎጅ ላይ፣
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል ላይ
- ከጎላ ሚካኤል ወደ ኢሚግሬሽን ጎማ ቁጠባ መስቀለኛ ላይ፣
- ከቸርቸር ወደ ለገሀር ቴዎድሮስ አደባባይና ኢሚግሬሽን መብራት ላይ፣
- ከንግድ ማተሚያ ፣ኦርማ ጋራዥና ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ (ኦርማ ጋራዥ)፣ ከአራት ኪሎ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፓርላማ መብራትና የድሮው አሮጌ ቄራ መስቀለኛ (ኮንሰን ላይ)፣
- ከአዋሬ ሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ ቶታል ሴቶች አደባባይ ላይ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል፡፡
ውድድሩ በሚያሄድባቸው መንገዶች ላይ #ከዋዜማ ጀምሮ ለረዥም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ መሄድ ፍፅሞ የተከለከለ አዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

እርምጃዎን ወደስኬት ያድርጉ!!
በባንካችን የወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ በመጠቀም ካሰቡበት ይድረሱ፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!!
የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
https://yangx.top/Globalbankethiopia123

በ14.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው የቧንቧና መገጣጠሚያ ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ!
በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ፤ በ3000 ሜትር ካሬ ስፋት ላይ፤ በ14.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተገነባው የቧንቧ እና መገጣጠሚያ ማምረቻ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ተከፍቷል። ፋብሪካው፥ በኢ.ዜድ.ኤም ትሬድና ኢንቨስትመንት እንዲሁን በሪኢፎ ኩባያ የተቋቋመ ነው።
በሁለቱ ድርጅቶች አጋርነት የተመሰረተው ፋብሪካው፥ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፣ እጅግ የዘመኑና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ፒፒአር፣ ኤችዲፒኢ፣ ፒቪሲ ቧንቧዎች እና ቱቦዎችን ከአስፈላጊ የመገጣጠሚያ ዕቃዎች እና መለዋወጫዎች ጋር ለማምረት ይችላል ተብሏል።
ኢትዮጵያዊ ኩባንያ የሆነው ኢዜድኤም ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ እስመለዓለም ዘውዴ እንደተናገሩት የአዲሱ ፋብሪካ ምርቶች ወደ ገበያ ሲቀላቀሉ ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚደርስ የገበያ ዋጋ ቅናሽ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
በዘርፉ ልምድ እንዳለው የተነገረለት ዓለም አቀፉ ተቋም "ሪኢፎ ኩባያ" ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው፣ “ በደቡብ አፍሪካ ከተከልነው ግዙፍ ኩባንያ ቀጥሎ ሁለተኛው ነው፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።
ፋብሪካው፥ በተለያዩ ዘርፎች ያለውን የቧንቧ እና የትቦ ዝርጋታ ሥርዓት አቅርቦትና ጥራት እጥረትን ለመፍታት ያስችላል የተባለ ሲሆን ከውጭ ይመጣ የነበረውን በማስቀረትም የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ እንደሚያስችል ተጠቁሟል።

#ጎንደር
° " የሽንኩርት ሽያጭ ዋጋ በኪሎ 60 ብር ነበር አሁን በእጥፍ አድጎ እስከ 120 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው " - የጎንደር ነዋሪ
° " በሚታየው የዋጋ ጭማሪ ምክንያት የዕለት ከዕለት ኑሮን መግፋት አስቸጋሪ ሆኖብኛል " - የጎንደር ነዋሪ
በጎንደር ከተማ ተከስቶ የነበረውን ግጭት መነሻ በማድረግ በኢንዱስትሪና በግብርና ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በመከሰቱ የዕለት ከዕለት ኑሯቸውን ለመምራት መቸገራቸውን ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
ካነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወጣት አስተሪዮ አስማረ በሰጠው አስተያየት ቀደም የሽንኩርት ሽያጭ ዋጋ በኪሎ 60 ብር ነበር አሁን ዋጋው በእጥፍ አድጎ እስከ 120 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው፡፡
የዘይትና የሌሎች የሸቀጥ ምርቶችም ላይም የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል፡፡
ታዲያ የዋጋ ንረት በመከሰቱ " የዕለት ከዕለት ኑሮዬን ለመምራት ተቸግሪያለሁ " ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
ሌላው በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት የከተማዋ ነዋሪ አቶ ጎበዬ መኩሪያው ደግሞ በአካባቢው ተከሰቶ የነበረውን ግጭት ምክኒያት በማድረግ በግብርና ምርቶችና በሸቀጥ ምርቶች ላይ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል ይላሉ፡፡
የጤፍ ዋጋ በኪሎ 65 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ወደ 110 ብር አሻቅቧል፡፡
" በእያንዳንዱ የሸቀጥ ምርቶችም ላይም በተመሳሳይ የሽያጭ ዋጋቸው እየጨመረ ነው፡፡ ነጋዴዎች ያላግባብ ምርት ያከማቻሉ፡፡ ያላግባብ ዋጋ ይጨምራሉ፡፡ ነዋሪዎች ግጭት ይነሳል በሚል ስጋት እህል እየገዙ ያከማቻሉ፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ የዕለት ከዕለት ኑሮን መግፋት አስቸጋሪ ሆኖብኛል " ሲሉ አስተያየት ሰጭው ይናገራሉ፡፡
እየተደረገ ያለው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ተገቢ ባለመሆኑ የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ ከሰሞኑን በነበረ አንድ መድረክ ላይ ፤ " በከተማዋ በኢንዱስትሪና በግብርና ምርቶች ላይ ያላግባብ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል፡፡ ይህ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎችና የመንግሰት ሰራተኞችን አስመርሯል፡፡ በቀጣይ ችግሩን ለመፍታት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት ይሰራል " ብለዋል፡፡
" የከተማ አስተዳደሩ ለዳሽን የሸማቾች ህብረት ስራ ዩኔን 20 ሚሊየን ብር ያለ ወለድ ብድር ሰጥቶ በመሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት የግብርና ምርቶችን የማሰራጨት ስራ እየተሰራ ነው " ያሉት ከንቲባው በቀጣይ ለመሰረታዊ የሸማቾች ህብረት ሰራ ማህበራት የሚደረገው ያለ ወለድ የገንዘብ ብድር ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፤ የማህበራትን አቅም የማሳደግ ስራም በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።
ያለ አግባብ ምርት በሚያከማቹ ግለሰቦች ላይም ክትትልና ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል፡፡
መረጃውን የጎንደር የቲክቫህ-ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል ነው የላከው።

" 53 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ለማድረግ በአብላጫነት ይደግፋሉ " - የአፍሮባሮሜትር ጥናት (በኢዮብ ትኩዬ) 66 በመቶ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ እንደሚሹ መመላከቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ #አፍሮባሮሜትር ይፋ ካደረገው ጥናት ተረድቷል። የዳሰሳ ጥናቱ ከላይ ከተጠቀሰው የገደብ ፍላጎት በተጨማሪ 67 በመቶ ኢትዮጵያውያን የሕገ…
#ኢትዮጵያ #ጥናት
54 በመቶ ኢትዮጵውያን የኢትዮጵያን የባህልና የቋንቋ ብዝሃነት ለማስተናገድ ከአሃዳዊ ይልቅ ፌደራላዊ የመንግሥት ሥርዓትን እደሚመርጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አፍሮባሮሜትር ከግንቦት 17 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም አጠናሁት ካለው የጥናት ግኝቶች ተገዝቧል።
42 በመቶ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ፌደራሊዝምን ወደ ግጭት የሚመራ ሥርዓት አድርገው ይመለከታሉ።
በጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች መሠረት፦
- ከአሥሩ ውስጥ አራቱ (42 በመቶ) ኢትዮጵያውያን ፌደራሊዝምን ወደ ግጭት የሚመራ ሥርዓት አድርገው ይመለከታሉ፣ ስለዚህ ወደ አሃዳዊ የመንግሥት ሥርዓት መሸጋገሩን የሚደግፉ ናቸው።
ጥናቱ 54 በመቶ በገጠር፣ 56 በመቶ በከተማ እንዲሁም 54 በመቶ በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያውያን ፌደራሊዝም ኢትዮጵያ ካላት የባህል እና የቋንቋ ብዝሃነት የተነሳ፣ ነጻ የሆኑ የክልል መንግሥታት ያለው ፌደራሊስም ሥርዓት የተሻለነው ማለታቸውን ያስረዳል።
ነገር ግን 43 በመቶ በገጠሩ፣ 40 በመቶ በከተማ እንዲሁም 42 በአገራዊ ያሉ ኢትዮጵያውያን " በባህልና በቋንቋ ማንነት ላይ የተመሰረተው የፌደራሊዝም ሥርዓት አንዳንዴ ወደ ግጭት ስለሚመራ ኢትዮጵያ ወደ አሃዳዊ መንግሥት መቀየር አለባት፣ ማእከላዊ መንግሥት በሥልጣን አሰጣጥ የበለጠ ሥልጣን ይኖረዋል " ብለው እንደሚስማሙ የጥናት ውጤቱ ይገልጻል።
3 በመቶ በገጠር፣ 4 በመቶ በከተማ፣ 3 በመቶ በአገራዊ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሁሉም አልስማማም፣ አላውቅም፣ ፈቃደኛ አይደለሁም ማለታቸውን ጥናቱ ያስገነዝባል።
- በ2012 ከተደረገው የተቋሙ የዳሰሳ ጥናት ጋር ሲነጻጸር፣ የፌደራል ሥርዓት መንግሥትን የሚደፉ ሰዎች በሰባት በመቶ (ከ61 በመቶ ወደ 54 በመቶ ወርዷል)። አሃዳዊ የመንግሥት ሥርዓትን በመደገፍ ረገድ ደግሞ የአምስት በመቶ ብልጫ አለው።
በ2020 61 በመቶ ኢትዮጵያውያን ፌደራሊዝም የተሻለ ሥርዓት ነው ብለው ይስማሙ እንደነበር፣ በ2023ቱ ጥናት ደግሞ ፌደራሊዝም የተሻለ ሥርዓት ነው የሚሉት ወደ 54 በመቶ ዝቅ እንዳለ እንዲሁም በ2020 ጥናት 37 በመቶ የሚሆኑት ሥርዓቱ ወደ አሃዳዊ የመንግሥት መዋቅር መቀየር አለበት ብለው እንደነበር፣ በ2023 ደግሞ አሃዳዊ ይሁን ያሉት ወደ 42 በመቶ ከፍ እንዳለ ግራፉ ያመለክታል።
- ግማሽ ያህሉ (49 በመቶ) ኢትዮጵያውያን ፌደራሊዝም በብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማንነት መሠረት የተቀመጡ ክልሎችን መሠረት አድርጎ ፌደራላዊ የመንግሥት ሥርዓት መቀጠል እንዳለበት፣ ግማሾቹ (48 በመቶ) ክልሎቹ ደግሞ በመልካዓ ምድራዊ ገፅታዎች እንጅ የተለያዩ ብሄር፣ ብሄረሰቦች በሚኖሩበት መልኩ መሆን እንደሌለበት መናገራቸው በጥናቱ ተቀምጧል።
በዚህም 54 በመቶ የሚሆኑት የከተማ ነዋሪዎች መልካዓ ምድራዊ ገፅታዎች መሠረት ያደረገ የፌደራል ሥርዓትን የመምረጥ ዝንባሌ እንዳሳዩ፣ በገጠር ያሉ 51 በመቶ የሚሆኑ ነዋሪዎች ደግሞ በማንነት ላይ መሠረት ያደረገውን የፌዴራል ሥርዓት የመምረጥ ዝንባሌ እንዳሳዩ፣ ይህም በአገር ደረጃ ከ2012 ዓ.ም ጥናት ጋር ሲነጻጸር እነዚህ አስተሳሰቦች እምብዛም እንዳልተለወጡ ጥናቱ አክሏል። ይህኑም በግራፍ መግለጫው በዝርዝር አብራርቷል።
ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ለዘጠነኛ ጊዜ የተጠና ሲሆን፣ 53 በመቶ ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ለማድረግ፣ 66 በመቶ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ እንደሚሹ ከዚሁ ጥናት የተመለከትነውን ከቀናት በፊት መዘገባችን ይታወሳል።
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

Photo
አፍሮባሮሜትር ማነው ?
" አፍሮባሮሜትር " የተባለው ተቋም ከሰሞኑን እንዲሁም ከዚህ ቀደም #ኢትዮጵያን የሚመለከቱ የተለያዩ የጥናት ውጤቶችን ይፋ ሲያደርግ ነበር።
ለመሆኑ ይህ ተቋም ማነው ?
አፍሮባሮሜትር የተባለው ተቋም ፤ አፍሪካ ላይ ትኩረት አድርጎ ገለልተኛ የሆኑ የጥናት እና ምርምር ስራዎችን የሚሰራ መንግሥታዊም / ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም እንደሆነ ይገልጻል።
ይህ ተቋም ታማኝ የሆኑ መረጃዎችን በዋናነት በዴሞክራሲ፣ አስተዳደርና የኑሮ ጥራት ላይ በማሰባሰብ የካበተ ልምድ ማፍራቱን ይናገራል።
ተቋሙ ዘጠኝ ዙር ጥናቶችን እኤአ ከ1999 ጀምሮ በ42 ሀገራት ላይ መስራቱን ይገልጻል።
ጥናት የሚካሄደው በዋናነት በገፅ ለገፅ ቃለመጠይቅ መሆኑን የሚያስረዳው ተቋሙ፤ የጥናቱ መረጃ አሰባሰብ ሂደት የጥናቱ ተሳታፊዎች በመረጡት ቋንቋ እንደሆነ ያመለክታል።
ጥናቱ የሚካሄደው ወካይ የሆነ #ናሙና መጠን በመመደብ እንደሆነም ይገልጻል።
ይህ ተቋም ሰሞኑን ኢትዮጵያን በተመለከተ ይፋ ያደረገው ጥናት ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) በተገኘ ድጋፍ ሲሆን 2400 ቃለመጠይቆችን (ዕድሜያቸው 18ና ከዚያ በላይ የሆናቸውን) በማሳተፍ ያዘጋጀውና መረጃው ከግንቦት 17 እስከ ሰኔ 15 /2015 ዓ/ም የተሰባሰበ ነው።
ይኸው ጥናት የናሙናው መጠን በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰራቱንና ወካይነት ያለው መሆኑን ገልጾ የአስተማማኝነት ደረጃውም 95 በመቶ መሆኑን አስረድቷል።
አፍሮባሮሜትር ከዚህ ቀደም ጥናት ያካሄደው በ2012 ዓ/ም ነበር።
(ሰሞኑን ይፋ የተደረጉት የጥናት ውጤቶች ከላይ የተያያዙት ናቸው)