ስለምትተማመኑብን...
**
ከ20 ዓመታት በፊት ብዙዎች በእምነታቸው ምክንያት ከባንክ አገልግሎት ርቀው የሚገኙበት ወቅት ነበር፡፡
ይህን በውል የተረዳው ባንካችን እ.ኤ.አ ከ2003 ጀምሮ ልዩ ወለድ የማይታሰብባቸው የሂሳብ አገልግሎቶችን በማቅረብ የራቁትን ማቅረብ ጀመረ፡፡
በባንካችን እና በሌሎችም ጥረት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ህግ እና መመሪያ ሲወጣም ባንካችን የመጀመሪያው በመሆን ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
እናንተ ውድ ደንበኞቻችንም ስለምትተማመኑብን ከእኛ ጋር ለመስራት አላቅማማችሁም፡፡
አሁን ከ6.4 ሚሊዮን በላይ የሲቢኢ ኑር ደንበኞች ከእኛ ጋር ይሠራሉ፡፡
ከወለድ ነፃ አገልግሎት የጀመርንበትን 10ኛ ዓመት ስናከብር ከደንበኞቻችን ጋር ከስካሁኑ የላቀ ስኬት እንደምናስመዘግብ እርግጠኛ በመሆን ነው፡፡
እና ስለምትተማመኑብን እናመሰግናለን!
ስኬታማ ምዕራፍ፤ ብሩህ ተስፋ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የ2016 የሶፊማልት ታለቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ በሰላም ተጠናቋል
የ2016 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ደስታን፣ጨዋታን ጤናን ተላብሶ ውሏል
በዛሬው ዕለት" ታላቁ ሩጫ የኛ መገለጫ" የሚል መርህን የያዘው፣ መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ በአዲስ አበባ የተካሄደው የ10 ኪ.ሜ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎችን ፣በመቶ የሚቆጠሩ አትሌቶችን አሳትፎ በሠላም
ተጠናቋል
#ምንያስሮጥሀል #ገብስያስሮጠኛል #ሶፊማልት

#እንድታውቁት
የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ከነገ ህዳር 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባ ያደርጋል።
ቢሮው በዚህ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት ያልቻሉ 33,766 አዲስ ተማሪዎችን ከደረጃ I እስከ V ተቀብሎ ያሰለጥናል።
ቢሮው በአዲስ አበባ በሚገኙ 15 የመንግሥት እና 114 የግል ትምህርት ቤቶች በ22 የስልጠና ዘርፎች አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያሰለጥን የቢሮው ኃላፊ ሀቢባ ሲራጅ ገልፀዋል።
በ85 የሙያ ዓይነቶች ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሠልጣኞች አጫጭር ስልጠናዎች ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡
በ2013 ዓ.ም ያጠናቀቁ ተማሪዎች በየኮሌጁ እየሔዱ በአካል እንዲመዘገቡ ዕድል መመቻቸቱ ተመላክቷል።
ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ያሉ ተማሪዎች በኦንላይን http://aatvetb.edu.et ላይ በመግባት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
Via @tikvahuniversity

" 65 ቢሊዮን ብር የት እንደገባ አይታወቅም " - አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ
በቀድሞ አጠራሩ የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በአዲሱ አወቃቀር ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ላይ የሒሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ባደረገው የሒሳብ ኦዲት ምርመራ፣ 65 ቢሊዮን ብር የት እንደደረሰ እንደማይታወቅ ተገለጸ፡፡
በአገሪቱ ከሚገኙ ትልልቅ ድርጅቶች መካከል አንዱ የነበረው ሜቴክ ከተመሠረተ ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2012 ዓ.ም. ድረስ የነበረው የሒሳብ ኦዲት ከተሠራ በኋላ ከፍተኛ ኪሳራ መገኘቱን የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት ሱሌማን ደደፎ (አምባሳደር) ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።
" የሒሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን በሠራው ሪፖርት መሠረት 65 ቢሊዮን ብር የት እንደደረሰ ስለማይታወቅ፣ የኦዲት ሪፖርቱን መሠረት በማድረግ መንግሥት እንዲሽረው (Write off) ተጠይቆ ውሳኔ አግኝቷል " ብለዋል፡፡
በዚህም መሠረት የተገኘው የኪሳራ ገንዘብ በዕዳ እንዳይመዘገብ መንግሥት ሽሮታል (Writeoff) ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
በኦዲት የተገኘው ገንዘብ ምንም ሥራ ላይ ያልዋለና በወቅቱ የነበሩ አመራሮች ተከፋፍለው የወሰዱት በመሆኑ በዚህ ተቋም አማካይነት የአንድ ህዳሴ ግድብ መሥሪያ ብር መዘረፉን ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ ከተደረገ በኋላ ወታደራዊ ምርቶች ለብቻ እንዲሆኑ በመክፈል እንደ አዲስ የተዋቀረው ግሩፑ፣ የደረሰበትን ሀብትና ዕዳውን የመለየትና ጥፋቶችን በመመርመር በሕግ የሚገዛ አገራዊ ተቋም ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የቀድሞው ሜቴክ ከተመሠረተበት ጀምሮ እስካሁን ያለውን አጠቃላይ ሒሳብ ኦዲት መደረግ የተጀመረ መሆኑን፣ እስከ 2012 ዓ.ም. ድረስ ያለውን በማጠናቀቅ ከ2012 ዓ.ም. በኋላ ያለው በሒደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኦዲት ሪፖርቱ ግኝት መሠረት ከኪሳራው በተጨማሪ፣ በሀብት ደረጃ የተመዘገቡት እንዲሸጡ በማድረግ ለግሩፑ ገቢ እንዲሆን እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት ያለ አገልግሎት የተቀመጡ 5 ቤቶችን ወደ ገንዘብ ለመቀየር በቅርቡ ለሽያጭ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል፡፡
" የቀድሞ የድርጅቱ አመራሮች የዝርፊያ ሥልት አሁንም ድረስ በተለያዩ መንገዶች እየቀጠለ በመሆኑ፣ ከኪሳራ እንዳይላቀቅ ማነቆ እየሆነ ነው " ብለዋል፡፡
በቅርቡ ይፋ የተደረገው የፓወር ኢኪዩፕመንት ፋብሪካ ውስጥ የሚገኙ ስምንት አመራሮች #ከብረት_ስርቆት ጋር በተገናኘ መያዛቸው አንዱ ማሳያ መሆኑን፣ ሌሎች አመራሮችም ቀስ በቀስ ተጠያቂ እንደሚደረጉ አሳውቀዋል።
መረጃው የሪፖረተር ጋዜጣ ነው።
@tikvahethiopia

ለ#መክሰስTime - ከ #ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️
When the snack is too good to share 😋 Let us indulge in #SnackTime with #SUNChips and share #SunnyMoments.☀️
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia

#AddisAbaba
" ባለንብረቶች የሚቀጥሯቸውን ጥበቃዎች ማንነት በሚገባ ሊያረጋግጡ ይገባል " - ፖሊስ
በጥበቃ ስራ ተቀጥሮ ከሚሰራበት ኮንዶሚኒየም ሁለት ተሽከርካሪዎችን ከግብረ አበሮቹ ጋር በመመሳጠር የሠረቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳወቀ።
እንደ ፖሊስ መረጃ ፤ ተከሳሽ ወንጀሉን የፈፀመው ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ/ም ከለሌቱ 7:00 ሰዓት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤቶ (ኮንደሚኒየም) ቅጥር ግቢ ነው።
ግለሰቡ በጥበቃ ስራ ተቀጥሮ ጥቂት ቀናትን ከሠራ በኋላ ተመሳሳይ የመኪና ቁልፍ በማዘጋጀት ከሌሎች 3 ግብረ አበሮቹ ጋር በመመሳጠር ሁለት ተሽከርካሪዎችን ሰርቀው ከአካባቢው ተሰውረዋል።
የአራብሳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መርመራ ክፍል የግል ተበዳዮች ተሽከርካሪያቸውን ካቆሙበት መሰረቁን ወደ ፖሊስ ጣቢያው ቀርበው ካመለከቱ በኋላ ምርመራ የማጣራት ሂደቱን ይጀምራል።
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦሮ 17692 ነጭ ሚኒባስ ታክሲ እና የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 88009 ሀይሉክስ ተሽከርካሪዎችን ተከሳሹ ሌሎች 3 አባሪዎችን በመያዝና ለዚሁ ወንጀል ተግባር ባዘጋጀው ቁልፍ በመጠቀም ተሽከርካሪዎቹን ይዘው መሠወራቸውን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
ፖሊስ የደረሠውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባደረገው ክትትል ፤ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦሮ 17692 ሚኒባስ ታክሲውን በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከሚሴ ከተማ የያዘ ሲሆን ሌላኛውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 88009 የሆነው ሀይሉክስ ተሽከርካሪ ደግሞ አጣዬ አካባቢ ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሊያውል ችሏል።
ባለንብረቶች የሚቀጥሯቸውን ጥበቃዎች ማንነት በሚገባ ሊያረጋግጡ እንደሚገባም ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
መረጃው የአዲስ አበባ ፖሊስ ነው።

#ትግራይ
የአስፋልት ዳር የትራፊክ አደጋ መከላከያ ብረት ስርቆት በትግራይ ምን መልክ አለው ?
" በአከባቢው ያልተለመደ አዲስ የሌብነት አይነት "
በትግራይ የነበረው ጦርነት ተከትሎ ከባድ የሆነ የፀጥታ መደፍረስና ሰፊ የስርቆት ተግባራት ተፈፅሟል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ሪፓርተር ጦርነቱ ተከትሎ በአገርና ህዝብ ሃብት የሆነው በአስፋልት ዳር የሚተከለው የትራፊክ አደጋ መከላከያ ብረት ሰርቆት ምልከታ አድርጓል።
በአስፋልት ዳር የሚተከለው የትራፊክ አደጋ መከላከያ ብረት ሰርቆት ምልከታ ለማካሄድ ከመቐለ በተምቤን አድርጎ እንዲሁም ከመቐለ በዓዲግራት አድርጎ ወደ ዓድዋ ፣ አክሱም ፣ ሽረ ፣ ሸራሮ ሑሙራ የሚወሰደው መንገድ ተከትሎ እስከ አክሱም ከ200 ኪሎሜትር በላይ ተጉዟል።
ከመቐለ በዓዲግራት በኩል እስከ ዓድዋ ሲጓዝ በርካታ የአፋልት ዳር የትራፊክ አደጋ መከላከያ ብረት ብሎኑ ተፈትቶ የተወሰደ ፣ የወደቀ እና በመኪና የተገጨ ተመልክቷል።
በተመሳሳይ ከመቐለ በተምቤን ዓብዪ ዓዲ ወደ ዓድዋ አክሱም ሲጓዝ በተለይ ከዓብዪ ዓዲ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ወርቃምባ ወረዳ ልዩ ቦታ እንዳባኖ እስከ ወርዒ የተባለ ድልድይ ድረስ ብቻ ከ28 በላይ የትራፊክ አደጋ መከላከያ ብረት ተዘርፎ መወሰዱ ፣ ከተወሰደው የማይተናነስ ቁጥር ያለው ደግሞ ተፈትቶ ለስርቆት በሚመች መልኩ ወድቆ ተመልክተዋል የአከባቢው እማኞችና ሹፌሮች በማነጋገርም አረጋግጧል።
የቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ ሪፓተር ከ10 በላይ ሹፌሮች ፣ ተጓዦችና የአከባቢው ነዋሪዎች አነጋግሮ እንዳረጋገጠው ፤ የሰርቆት ተግባሩ ጦርነት ወለድና በአከባቢው ያልተለመደ አዲስ የሌብነት አይነት ፣ ሌብነቱ በተለይ በጦርነቱ ጊዜ በቀን በጠራራ ፀሃይ መጥረቢያና ቢላዋ የመሳሰሉ በታጠቁ ህገወጦች መፈፀሙ ፤ ጦርነቱ ከረገበ በኋላ ድግሞ በሌሊት ሲፈፀም እንደነበር መረጃ አግኝቷል።
ይህንን በጉዞ ላይ ያሉት ተሽከርካሪዎች በፊት ሆኖ በማንፀባረቅ ጠመዝማዛና ፣ ገደላማ መንገድ ከሚያስከትለው አደጋ በመታደግ እንዲያሽከረክሩ የሚያሳየው የአስፋልት ዳር የትራፊክ አደጋ መከላከያ ብረት በውድ ዋጋ የተገዛ የአገርና የህዝብ ሃብት እንደሆነ ፣ እንዳይዘረፍና ሃላፊነት በጎደላቸው አሽከርካሪዎች ጉዳት እንዳይደርስት መከላከል የሁሉም ዜጎች በተለይ የአከባቢው ነዋሪዎች ሃላፊነት መሆኑ አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።
ህዝብ በአከባቢው የሚገኘውን የህዝብና የመንግስት ሃብት በተደራጀና በተናጠል የመጠበቅ ሃላፊነት ፤ ከታች እስከ ላይ ያለው የመንግስት መዋቅር ከፓሊስ በመተባበር ዘሪፊዎቹ በቁጥጥር ስር በመዋል አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ ፤ የተሰረቁት ኢንዲተኩ የተነቀሉትና የተገጩት መልሰው እንዲተከሉና እንዲጠገኑ የማድረግ ስራ የክልልና የፌደራል መንግስት ሃላፊነት መሆኑ አስተያየት ሰጪዎቹ አክለዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ሪፖርተር ፤ ስለጉዳዩ አክሱም ከተማ ድረስ በመሄድ ለትግራይ ማእከላዊ ዞን ዋና ፓሊስ አዛዥ በለጠ ገ/ስላሴ አነጋገሯቸዋል።
ዋና የፓሊስ አዛዡ የትራፊክ አደጋ መከላከያ ብረት ስርቆት መኖሩ በማመን ፤ ተግባሩ ሰርአት አልበኝነት በስፋት በታየበት በጦርነቱ ወቅት ገንኖ ይታይ እንደነበረ ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ ግን እጅግ እንደቀነሰ ፤ በዚሁ የዝርፍያ ወንጀል እስከ አሁን የተያዘ ተጠርጣሪ እንደሌለ ቢሆንም የስርቆት ተግባሩ የፈፀሙ ዘራፊዎች ተይዘው ለህግ እንዲቀርቡ እስከ ታች ያለው የፓሊስ መዋቅር ከአከባቢው ማህበረሰብ በመቀናጀት በመከታተል ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

#ኦሮሚያ
" ከ1 ሺህ በላይ ሃኪሞችን ለመቅጠር ብፈልግም ተቀጣሪ አጣሁ " - የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ
የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ 1 ሺህ 100 ሀኪሞችን ለመቅጠር ባለፈዉ ዓመት ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ማስታወቂያ ቢያወጣም ተቀጣሪዎችን ባለማግኘቱ በጀቱን ወደ ሌላ ዘረፍ ማዛወሩን ማስታወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
የቢሮዉ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ጉሻ በለኮ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ በሰኔ 2015 ላይ 1 ሺህ 100 ሀኪሞችን ለመቅጠር ማስታወቂያ የወጣ ቢሆንም ተቀጣሪዎችን ባለማግኘቱ ቢሮዉ በጀቱን ለሌላ ጉዳይ ማዋሉን ተናግረዋል፡፡
" ለ 2 ወራት ያክል ማስታወቂያዉን ክፍት ብናደርግም ገበያ ላይ ተቀጣሪዎችን አላገኘንም " ሲሉ ኣክለዋል።
ምክትል ኃላፊው ፤ በየአንዳንዱ ጤና ተቋም ሀኪሞች መኖር ስላለባቸዉ ያንን ለማሟላት ማስታወቂያ መውጣቱን አስረድተው " ሀኪሞችን ባለማግኘታችን በምትኩ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን፣ አዋላጆችን እና ነርሶችን ለመቅጠር ተገደናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት ለመላዉ ኦሮሚያ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 72 ሺህ ነበር ያሉት ሃላፊዉ አሁን ላይ ቁጥሩ ወደ 85 ሺህ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።
" በተቻለን አቅም ማስታወቂያ አዉጥተን ገበያ ላይ የነበሩትን ለመዉሰድ ሞክረናል ነገርግን አሁንም የሀኪሞች ዕጥረት አለ " ብለዋል፡፡
" ማስታወቂያ አይተዉ የመጡትን እንቀጥራለን ፤ ካልመጡ ግን ገበያዉ ላይ የሰዉ ሃይል እንደሌለ ነዉ የሚቆጠረዉ " ሲሉም አስረድተዋል።
ምክትል ሃላፊዉ በተጨማሪም ባለፈዉ ዓመት ሃኪሞችን ለመቅጠር ባወጣነዉ ማስታወቂያ ሀኪሞችን ማግኘት ስላልቻልን ወደ 7 መቶ አከባቢ የሚሆኑ የተለያዩ ባለሙያዎችን ቀጥረናል ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
የዚህ መረጃ ባለቤት ኢትዮ ኤፍ ኤፍም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።