TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( #ጂጂ ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል። አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች…
#AAU #DrBinyamBelete😢

ዛሬ ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው የሜቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ በመድረኩ ላይ ንግግር አድርገው ነበር።

ያደረጉት ንግግር እጅግ ስሜትን የሚነካ ስለነበር ተመራቂዎች እና ታዳሚያንን #እያለቀሱ ሲያዳምጡ ነበር።

አቶ ቢንያም በለጠ ምን አሉ ?

" ...ለእኔ ብዙ ትልቅ ቦታ አትስጡኝ ፤ እኔ የማልረባ ሰው ነኝ ፤ ቅድም ስለእኔ ስትገልፁ ከብዶኛል።

እውነቴን ነው እግዚአብሔር ይሰራል እሱን አልክድም ሜቄዶንያ ላይ ፤ ምክንያቱም ካለምንም እርዳታ ይሄን ሁሉ ሺህ ሰው በሀገር ውስጥ በየቀኑ አንድ ሚሊዮን የእግዚአብሔርን ስራ መሆኑ ግልፅ ነው በጣም።

እኔኮ በሽተኛ ነኝ ሲጀምር ብዙ ጊዜ ተኝቼ ነው የምውለው ፤ ስራ ያቆምኩ ሰው ነኝ እኔ እንደውም የህብረተሰብ ሸክም መሆን ያለብኝ ሰው ነኝ እውነት ለመናገር።

እንደ እኔ አይነት ሰው ዝም ብላችሁ ብታስቡት እንኳን እንደዚህ ለማድረግ ይቅርና እራሴንም ለመቻል ወይ አግብቶ ወልዶ ለመኖር ሰው ለመርዳት ቀርቶ ለመለመን እንኳን አንድ ሰው ጤነኛ መሆን አለበት ፤ ለመለመን ወጣ ብሎ አንድ ቦታ መቀመጥ አለበት እኔ መቀመጥም አልችልም።

ለመኖር እራሱ የማይገባኝ ሰው ነኝ ፤ በእግዚአብሔር ኃይል ነው ያለሁት ፤ እውነቴን ነው የምነግራችሁ ቀልዴን አይደለም። አንድ ሰው ለመለመን መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ሰው መጠየቅ አለበት አይደል እንደዛ እንኳን የምችል ሰው አይደለሁም። ስለዚህ እግዚአብሔር ነው የሚሰራው።

አንድ የህብረተሰብ ሸክም የሆነ ሰው ፤ እግዚአብሔር ምን ያህል ሃጥያተኛ ሰዎችን በመንፈስም በስጋም ደካማ የሆኑ ሰዎችን እንዴት መርዳት እንደሚችል አንዳንድ ሰዎች በቤተሰብ፣  በትዳር፣ ወይ ሰው አስቀይሟችሁ እንደው እግዚአብሔርን የለም ብላችሁ/ እግዚአብሔር ረሳኝ ብላችሁ ከሆነ እግዚአብሔር እንደዚህ ይሰራል። በማይረቡ ሰዎች፣ በተራ በጣም በወንጀለኛ ሰዎች መስራቱን ስታዩ ሁሉንም ሰው እግዚአብሔር እንደሚረዳ የሚያሳይ ነገር ነው።

ክብር ዶክትሬት ተብሏል ፤ እኔ ትንሽ ከብዶኛል በጣም ምክንያቱም እናተ ሸልማችሁኛል ፤ የእግዚአብሔር ፍርድ ደግሞ ከባድ ነው እውነት የእግዚአብሔር ፍርድ በጣም አስፈሪ ነውና ከሲኦል እንድድን እግዚአብሔር ከዚያ እንዲያወጣኝ ፀሎት አድርጉልኝ የእውነት። ይሄ በጣም ከባድ ነገር ስለሆነ ነው። ቀልድ አይደለም እግዚአብሔር ዝም ብለን ሃጥያት ስንሰራ ዝም የሚለን አምላክ አይደለም። የእግዚአብሔር ፍርድ ከባድ ነውና እኔ የምፈራው እሱን ነው እንኳን ልሸለም ለፍርድ እንዲቀልልኝ የማስብ ሰው ነኝ።

ሜቄዶንያ ላይ ብዙ ሰው አስተዋጽኦ ያደርጋል። እኔ የተለየ አስተዋጽኦ የለኝም ከዛ ያነሰ ነው የእኔ አስተዋፅኦ። በሽተኛ ስለሆንኩኝ ስራም ስለሌለኝ አንደኛው ተደጓሚ ነኝ እራሴ በመቄዶንያ ነገር ግን መቄዶንያ ባልፉት ዓመታት እዚህ ለመድረስ ብዙ አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ ሰዎች አላችሁ ምስጋናም ክብርም የሚገባው ለእናተ ነው።

ተማሪዎች፣ ወጣቶች ፣በጎፍቃደኞች፣ የመንግሥት ኃላፊዎች፤ የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ፣ ሚኒስትሮች ፣ ኮሚሽነሮች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሁሉም ሜቄዶንያን አግዘዋል በየቢሮው ያስተናግዱናል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የክልል መስተዳደሮች በሙሉ፣ ለሜቄዶንያ እዚህ መድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። "

(የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( #ጂጂ ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል። አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች…
" ይሄ ለእኔ የሚገባኝ አይደለም። ግን ስላከበራችሁኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ " - እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)

እጅግ ተወዳጇ አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተበረከተላትን የክብር ዶክትሬት በተመለከተ መልዕክት አስተላልፋለች።

ምን አለች ?

እጅጋየሁ ሽባባው ፦

" እምዬ ሀገሬ ፤ ውድ ሀገሬ ኢትዮጵያ እንዲሁም በጣም የምወዳችሁ የማከብራችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ሰላም ሰላም ብያለሁ።

በአክብሮት የሰጣችሁኝን የአክብሮት ዶክትሬት በጣም በትልቅ ደስታ ነው የተቀበልኩት ፤ በጣም አመሰግናለሁ፤ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እኔ በጣም በጣም ነው የገረመኝ ታጭቼ ብገኝ እንኳን የሚያስደንቀኝ ነበር ተመርጬ ስለተነገረኝ በጣም ነው የማመሰግነው፤ እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

ፍቅራችሁ እንዲሁ አክብሮታችሁ ስለሆነ በእኔና በወገኖቼ ስም እንዲሁም በዚህ ሁሉ ደስ በሚላቸው ኢትዮጵያውያን ስም ከልቤ በጣም በጣም አመሰግናለሁ።

እግዚአብሔር ህይወታችሁን ይባርከው ፣ የኢትዮጵያ ዛሬ ያሉትን #ተማሪዎች እንዲሁም የወደፊቱን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክ፣ ሀገራችንን መንፈስቅዱስ ይጠብቅልን።

ያስቸግራል ለመግለፅ ደስታዬን ፤ በጣም አመሰግናለሁ፣ ፍቅራችሁና ክብራችሁ ከልክ ያለፈ ነው ፤ ለእኔ የሚገባኝ አይደለም። ግን ይሄን ሁሉ ስላከበራችሁኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

የኢትዮጵያን ህዝብ እግዚአብሔር ይጠብቅልን ፤ ምስጋናዬ በጣም ከፍ ያለ ነው፤ በአካል ተገኝቼ አንድ ቀን እዛ መጥቼ አያችኃለሁ ፤ በሰላም ቆዩኝ ይሄንን አጭር መልዕክቴን ይቅር በሉኝ ፤ በደንብ አድርጌ ሌላ ቀን አመሰግናችኃለሁ ፤ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እጅጋየሁ ነኝ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው። በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ። ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦ - ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ) - ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) - አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ዋናው ግቢ) - ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ጂንካ ዩኒቨርሲቲ - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ…
ምን ያህል ተማሪዎች ተመረቁ ?

ዛሬ ብቻ ከ53,582 በላይ ተማሪዎች ተመርቀዋል።

ዛሬ ከ28 የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) ብቻ ከ53,582 በላይ ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች፣ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተመርቀዋል።

- አዲስ አበባ ፦ 8,642 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 5,121 ፣ በ2ኛ ዲግሪ 3,221 ፣ በ3ኛ ዲግሪ 300)

- ሀዋሳ ፦ 7,571 ተማሪዎች (ቅድመ እና ድህረ ምረቃ)

- አምቦ ፦ 4,036 ተማሪዎች (ቅድመ ምረቃ 2,829 ፣ 1207 ድህረ ምረቃ ፣ 3 Phd ፣ 21 የህክምና ዶክተር)

- መደ ወላቡ ፦ 4,017 ተማሪዎች (በቅድመ እና ድህረ ምረቃ)

- ዋቸሞ ፦ 2,276 ተማሪዎች (በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በከፍተኛ ዲፕሎማ)

- ደብረ ብርሃን ፦ 2,147 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 1692 ፣ 2ኛ ዲግሪ 448 ፣ Phd 3 ፤ PGDT 4)

- ጅማ ፦ 2,124 ተማሪዎች (1,835 የቅድመ ምረቃ ፣ 282 ድህረ ምረቃ 7 ፒ.ኤች.ዲ)

- ደብረ ማርቆስ ፦ ከ2 ሺህ በላይ (በመጀመሪያ ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ)

- ዲላ ፦ 1,829 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 1,590 ፣ ሁለተኛ ዲግሪ 100 ፣ ሶስተኛ ዲግሪ 2 ፣ HDP 137)

- አርባ ምንጭ ፦ 1,457 (በቅድመ ምረቃ 859 ፣ በ2ኛ ዲግሪ 586 ፣ በ3ኛ ዲግሪ 12)

- ወልድያ ፦ 1,376 ተማሪዎች (በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ)

- ወለጋ ፦ 1,347 ተማሪዎች (976 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 350 በሁለተኛ ዲግሪ፣ 21 በሶስተኛ ዲግሪ)

- ሰመራ ፦ 1,309 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 1,104 ፣ በሁለተኛ ዲግሪ 190)

- ቡሌ ሆራ ፦ 1,299 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 907 ፣ 2ኛ ዲግሪ 392)

- አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፦ 1,236 ተማሪዎች (በመጀመሪያና በ2ኛ ዲግሪ ፣ በPhd)

- ደብረ ታቦር ፦ 1,202 ተማሪዎች (በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ)

- ሚዛን ቴፒ ፦ 1,285 ተማሪዎች

- ወልቂጤ ፦ 1,195 ተማሪዎች (በቅድመ ምረቃ 1,112 ፣ በድህረ ምረቃ 83)

- ወላይታ ሶደ ፦ 1129 ተማሪዎች (ባችለር ዲግሪ 374፣ ማስተርስ 743 ፣ ስፔሻሊቲ 11 ፣ ዶክትሬት 1)

- ጅግጅጋ ፦ 1,090 ተማሪዎች (808 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 282 ሁለተኛ ዲግሪ፣ 34 የእስሳት ህክምና ዶክተሮች)

- ቀብሪ ድሃር ፦ 885 ተማሪዎች (በመደበኛ 818 ፣ በ2ኛ ዲግሪ 67)

- ሰላሌ ፦ 855 ተማሪዎች (የመጀመሪያ ዲግሪ 617 ፣ 238 ሁለተኛ ዲግሪ)

- እጅባራ ፦ 750 ተማሪዎች (በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በከፍተኛ ዲፕሎማ)

- ወራቤ ፦ 720 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 632 ፣ በ2ኛ ዲግሪ 88)

- መቱ ፦ 647 ተማሪዎች (በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ)

- ጂንካ ፦ 501 ተማሪዎች

- ደባርቅ ፦ 374 ተማሪዎች

- ኦዳ ቡልቱም ፦ 283 ተማሪዎች (በአንደኛ እና ሁለተኛ ዲግሪ)

በድምሩ የዘረዘርናቸው የመንግሥት ተቋማት ዛሬ ያስመረቁት ከ53,582 በላይ ተማሪዎችን ነው።

ተቋማቱ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እና በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቁት።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#ቴሌብር

ወርሃዊ ደሞዝዎ በቴሌብር ይከፈልዎታል?

ለርስዎ የሚሆን እስከ 50,000 ብር ድረስ ልዩ ብድር በቴሌብር አድራሽ በቴሌብር ሱፐርአፕ እና *127# ተመቻችቶልዎታል!

ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአጋርነት
#የፋይናንስአገልግሎትለሁሉም
ቴሌብር ፋይናንስ ለተሻለ ህይወት!
#ዲጂታልኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ

ለበለጠ መረጃ https://www.ethiotelecom.et/አድራሽ/?lang=am
#ጥቆማ

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በተለያዩ የማኅበረ-ፖለቲካዊ ዘርፎች የሠለጠኑ ባለሙያዎች ተሳትፎ የክልሎች አስተዳደር ከዴሞክራሲያዊ መርሖዎች አንፃር የሚመዘንበትን ሒደት አመቻችቷል።

የምዘናው ዋነኛ አካል ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ወርክሾፕ ሲሆን፣ በወርክሾፑ የሚሳተፉት ባለሙያዎች በሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ላይ እየተወያዩ ምዘናቸውን ይሰጣሉ።

በእነዚህ ወርክሾፖች የሚሳተፉ ባለሙያዎች የዕለት ወጪ አበል ይታሰብላቸዋል። 

የምዘና ሒደቱ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች የሚከተሉት ሙያዊ ብቃቶች ሊኖሯቸው ይገባል ፦

▪️በአንድ ክልል ወይም ክልሎች ውስጥ ያለውን አስተዳደራዊ ሁኔታ በቅርብ የሚያውቁ እና የሚከታተሉ፣ 

▪️በሲቪል ነጻነት፣ በምርጫ እና ፖለቲካዊ ብዝኃነት፣ በማኅበረ-ፖለቲካዊ መብቶች፣ በመንግሥት አገልግሎት ቀልጣፋነት፣ በአናሳ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች ጥበቃ፣ ወይም በሥልጣን ቁጥጥር እና ሚዛን ርዕሰ ጉዳዮች የተለየ ትኩረት እና ዕውቀት ያላቸው፣

▪️ለጉዳዩ ረብነት ባለው የማኅበራዊ ሳይንስ ጥናት ሁለተኛ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ ያለቸው፣ 

የተመረጡ አመልካቾች 30 ጥያቄዎች ላይ በመወያየት መጠይቅ የሚሞሉበት ወርክሾፕ ላይ ለአንድ ቀን ይሳተፋሉ።

ተሳታፊዎች በቀን 3,000 ብር (ሶስት ሺህ ብር) አበል ይታሰብላቸዋል።

አንዳንድ ባለሙያዎች በትምህርት እና ልምዳቸው መሠረት በበርካታ ወርክሾፖች ላይ እንዲሳተፉ ሊመረጡ ይችላሉ። 

በእነዚህ ወርክሾፕ ላይ ለመሳተፍ ይህንን ሊንክ ክሊክ በማድረግ ፎርሙን ይሙሉ።

የማመልከቻው ጊዜ መጠናቀቂያ ሐምሌ 29፣ 2015 ነው።

#CARD
7 ዓመታትን ያለ ኤሌክትሪክ . . .

ለ7 ዓመታት ኤሌክትሪክ በተቋረጠበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፤ ካማሽ ዞን ነዋሪዎች " የከፋ ችግር ላይ " ስለመሆናቸው ቪኦኤ ሬድዮ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

አቶ ለማ ሮሮ የተባሉ የካማሽ ዞን፤ ካማሽ ከተማ ነዋሪ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳላገኙ  ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ እንዲጀምር ጥረት ቢደረግም ማታ ማታ ታጣቂዎች መስመሮች እየቆረጡ እንደሚያስቸግሩ በዚህም በመብራት የሚሰሩ ስራዎችን ለማከናወን መቸገራቸውን አስረድተዋል።

አሁን ያለውን ከፍተኛ ችግር ለመወጣት ስንል ነዳጅን በመጠቀም በጃነሬተር ለመስራት ጥረት እያደረግን ቢሆንም ነዳጅ ማግኘት በራሱ ፈተና መሆኑን ገልጸዋል።

በመብራት ምክንያት ኔትዎርክም እያስቸገረ መሆኑን አክለዋል።

አቶ ዳንኤል አየለ የተባሉ ነዋሪ ፤ ለዚህ ሁሉ ዓመታት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ መንግሥት ለችግሩ ትኩረት አለመስጠቱ ማሳያ ነው ብለዋል።

መንግሥት ሁሌም " የፀጥታ ችግር " ን እንደምክንያት ቢያነሳም እኔ የማስበው ግን ትኩረት ያለመስጠት ነው ሲሉ ገልጸዋል። ባለው ሁኔታ ችግር ውስጥ ነን ሲሉ አስረድተዋል።

ሌላ ነዋሪ ደግሞ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ #ከ6_ዓመት በላይ መሆኑና በህክምና ተቋማት ላይ ከባድ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ገልጸዋል። በ5 ወረዳ ውስጥ ኔትዎርክ እንደማይሰራ ፣ ካማሽ ላይም በተቆራረጠ ሁኔታ እንደሚሰራ ፣ ባንክም አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ነው ሲሉ አክለዋል።

ሰዎች የባንክ አገልግሎት ፍለጋ 2 እና 3 ቀናት በእግር ተጉዘው ነው ካማሽ የሚመጡት ፤ ተማሪዎችም ለማጥናትም እንደተቸገሩ ነው ሲሉ አብራርተዋል።

በአካባቢው ፀጥታ ከደፈረሰበት 2010 በፊት ችግር መኖሩን ያነሱት እኚሁ ነዋሪ የሚዘረጉትን የኤሌክትሪክ መስመሮች የሚቆራርጡ አካላትን " ላይተው እንደማያውቁ " ገልጸዋል።

የካማሽ ዞን ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጀርሞሳ ተገኝ ፥ በዞኑ አምስት ወረዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር እንዳለ ገልፀው ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከ2008 አጋማሽ አካባቢ አንስቶ መብራት መቆራረጥ እንዳጋጠማቸው ከግንቦት ወር በኃላ ግን ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን አስረድተዋል።

አቶ ጀርሞሳ ተገኝ ለውጡን ተከትሎ በሀገሪቱ በተለያየ አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የመብራት ኃይል ስራውን ማከናወን ስላልቻለ በአሁን ወቅት #መላው የዞኑ ማህበረሰብ የመብራት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ቡድን መሪው ፤ " አሁን ካማሽ ከተማ ላይ ባንክ አለ ፣ ቴሌ አለ ጄነሬተር በ500 ሺህ ፣ በሚሊዮንም ገዝተው ያመጣሉ ጄነሬተሩ እራሱ እየተበላሸ ከፍተኛ እንግልት ነው እየደረሰባቸው ያለው። " ብለዋል።

" ነዳጅ በብላክ ማርኬት/ጥቁር ገበያ ነው የሚገዛው ዋጋው ደግሞ ከጣም ውድ ነው " የሚሉት ቡድን መሪው " ኮምፒዩተር ቤቶች አሉ፣ በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች አሉ ፣ ሆስፒታል ላይ አልትራሳውንድ ፣ ላብራቶሪ ክፍል ያለመብራት አገልግሎት ስለማይሰጡ እነዚህ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ችግር እየደረሰ ነው በመንግስት ስራ ላይ ማለት ነው " ሲሉ የችግሩን መጠን ገልጸዋል።

" እንደመፍትሄ አባይ አሁን ላይ አገልግሎት መስጠት እየጀመረ ስለሆነ ፤ የተወሰነ #ከአባይ በትልቅ ታወር ተቀንሶልን እዚህ ማዕከል ላይ ማከፋፈያ ተሰርቶ ከዚህ ጥገኝነት እንላቀቅ የሚል ጥያቄ ነው ህዝቡ እያነሳ ያለው " ብለዋል።

" የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል " ችግሩን #በዘላቂነት ለመፍታት አዲስ የማከፋፈያ ጣቢያ ለመስራት ቃል ተገብቶ የነበር ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ተግባራዊ እንዳልተደረገ የቡድን መሪው አሳውቀዋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለካማሽ ዞን አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የ " ጊምቢ ኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ " አገልግሎት የተቋረጠው ከ2010 ጀምሮ መሆኑ አሳውቋል።

" ካማሽ " ላይ ብቻ ሳይሆን ፤ " ኪንጊ " በተባለ ስፍራ አዲስ ፕሮጀት ሰርተን በፀጥታ ችግር የዘረጋነው የኤሌክትሪክ መስመር በማይታወቅ አካል በመፈታቱ በአካባቢው አገልግሎት እንዳይኖር ተደርጓል ብሏል።

ያለውም ችግር ለመፍታት ከ2 ወር በፊት የጠፋውን የኤሌክትሪክ ሽቦ በመተካት ፕሮጀክቱ ሊጠናቀቅ ሲል 42 ኪ/ሜ በሚሆን ሽቦ ላይ ዛፍ ጥለው ፈተው ወስደውታል። የት እንዳደረሱት አይታወቅም ፤ ክትትል አድርጎ ያስመለሰም አካል የለም ሲል የማከፋፈያ ጣቢያው ገልጿል።

አካባቢው ነዋሪዎችን ስንጠይቃቸው ለሊት የሚፈፀም ድርጊት ስለሆነ ማን እንዳደረገው አናውቅም ይሉናል ፤ ህብረተሰቡ ንብረቱን እስካልጠበቀ እና የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ እስካልተሻሻለ ድረስ " መፍትሄ አይኖርም " ብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን የካማሽ ኤሌክትሪክ መቋረጥ መስሪያ ቤታቸውን እንደማይመለከት መግለፃቸውን ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

@tikvahethiopia