" ዘንድሮ በመደበኛው 667 ሺህ 483 ፤ በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈተና ይወስዳሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ከ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመት የተስተዋሉ የተለያዩ እንከኖች በዚህኛው ዓመት መስተካከላቸውን የትምሕርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።
ምዝገባው በማንዋል በመሆኑ ተፈጥሮ የነበረውን የተፈታኞች መረጃ አያያዝ ጥራት ጉድለት ለማረም ዘንድሮ ምዝገባው በበይነ መረብ መካሄዱን አገልግሎቱ ገልጿል።
በተጨማሪም ከዩኒቨርሲቲ ድልድል፣ ዝግጅት እና አቀባበል ጋር በተያያዘ እክሎች የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ ችግሩ መቀረፉን አረጋግጧል።
አምና ካጋጠመው ጉድለት በመማር የፈተና ማስፈጸሚያ ማንዋል እና መመሪያውን በማዘጋጀት እና በመከለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጓል።
ባለፈው ፈተና ወቅት ተፈታኞችን ማዘጋጀት አለመቻሉ ዋና ችግር እንደነበር የጠቀሰው አገልግሎቱ በዚህ ዓመት በቂ ዝግጅት ስለመደረጉ ገልጿል።
በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 869 ሺህ 802 ትክክለኛውን የምዝገባ ሂደት ያላሟሉ 1 ሺህ 213 ተፈታኞች ምዝገባ መሠረዙንም ተገልጿል።
ዘንድሮ ፦
- በመደበኛ 667 ሺህ 483
- በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈተና ይወስዳሉ።
ፈተናው በሁለት ዙር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይሳጣል።
የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን፤ ሁለተኛው ዙር ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 25 እስከ 28 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ አገልግሎቱ አረጋግጧል።
የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኞች ከሐምሌ 16 እስከ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እ
የሚገቡ ሲሆን ሐምሌ 18 ገለጻ ይሰጣቸዋል።
የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞች ደግሞ ከሐምሌ 22 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ገብተው ሐምሌ 24 ቀን ገለጻ ይሰጣቸዋል።
ተፈታኞች ፈተናውን በራሳቸው ጥረት እንዲሠሩ አሳስበው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባለፈው ዓመት የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 17 ሺህ ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን አስታውሷል።
Credit : #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርቃት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ። ተቋማት ለዓመታት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸው ፣ የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው የሚያስመርቋቸው። ዘንድሮ ከተሰጠው የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ በምርቃት መርሃግብር ላይ ከመሳተፍ ጋር በተገናኘ በተመራቂዎች ዘንድ ጥያቄዎች የነበሩ ቢሆንም ትምህርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ የተቋማቱ #የሴኔት ውሳኔ ጉዳይ መሆኑን ገልጾ…
ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።
በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ።
ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ)
- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ)
- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ዋናው ግቢ)
- ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
- ዲላ ዩኒቨርሲቲ
- እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
- ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ)
- መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
- ቀብሪ ድሃር ዩኒቨርሲቲ
- ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
- ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
- መቱ ዩኒቨርሲቲ
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ
- ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ
- ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ
- ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
- ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
- ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ።
ተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መረጃዎች በ @tikvahuniversity በኩል ማግኘት ትችላላችሁ።
ተመራቂዎች እና መላው ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ !!
#TikvahEthiopia

ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው። በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ። ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦ - ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ) - ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) - አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ዋናው ግቢ) - ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ጂንካ ዩኒቨርሲቲ - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ…
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( #ጂጂ ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል።
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች ደህንነት ላይ ለሀገር የማይተካ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው አርቲስት ደበበ እሸቱ በኪነጥበብ ዘርፍ ላበረከቱት ውለታ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።
ዕውቅናው ሁለገቧ አርቲስት #የኢትዮጵያን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነ ጥበብ #የአዊን_ሕዝብ_ቋንቋ እና #ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬት የተበረከተላት።
የክብር ዶክትሬቱን የእጅጋየሁ ሽባባው ወላጅ እናት ተቀብለዋል።

#CBE
ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስምና አርማ በመጠቀም በሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የሌብነት ተግባር የሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች አሉ፡፡
በመሆኑም የባንኩን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ፤ ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ!
የባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች፡
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• YouTube፡- https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
• LinkedIn፡- https://www.linkedin.com/company/commercialbankofethiopia
• Twitter፡- https://twitter.com/combankethiopia
• Telegram፡- https://yangx.top/combankethofficial
• Instagram፡- https://www.instagram.com/commercialbankofethiopia/
• tiktok:- https://www.tiktok.com/@commercialbankofethiopia

#ፖሊኪዩር_መድሀኒት_ቤት
👉 https://yangx.top/PolyCure
ኦርጂናል የሆኑ የተለያዩ የወንዶች፣ የሴቶች ፣ የህጻናት የቆዳ ፣ የንጽህና እና የዉበት መጠበቂያ ምርቶች ፣ ቫይታሚኖች ፣ ወተቶች እና ኮስሞቲክሶች ከተለያዩ አገሮች አስመጥተን በ መሸጥ ላይ እንገኛለን ።
ባሉበት ቦታ ሆነው ይዘዙን በፍጥነት ያሉበት ቦታ እናደርሳለን። አድራሻ:- 22 ማዞሪያ ኖህ ህንፃ ከ ጎላጉል ህንፃ አጠገብ ። ለበለጠ መረጃ +251978454647
https://www.facebook.com/polycurepharmacy/
https://www.instagram.com/polycurepharmacy1/
@Polycure

Photo
" ለእኔ ሳይሆን ስለእኔ ብዙ ለከፈለችው ወላጅ እናቴ ይሁንልኝ " - ተመራቂው ተማሪ
54 ኮርሶችን A+ ያገኘው ተመራቂ ተማሪ ፤ " ለእኔ ሳይሆን ስለእኔ ብዙ ለከፈለችው ወላጅ እናቴ" ይሁንልኝ በማለት ሜዳልያውን እንደተቀበለ ወደ እናቱ ሮጦ በመሄድ አጥልቆላታል።
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው ተመራቂ ተማሪ ዳግም ተስፋዬ ይህን አስደናቂ ተግባር ፈጸሟል።
ተመራቂው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዕፅዋት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ከወሰዳቸው 64 ኮርሶች 54ቱን ኮርሶች A+ በማምጣት የወርቅ ተሸላሚ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
54 ኮርሶችን A+ ያገኘው ተመራቂ ተማሪ ፤ " ለእኔ ሳይሆን ስለእኔ ብዙ ለከፈለችው ወላጅ እናቴ" ይሁንልኝ በማለት ሜዳልያውን እንደተቀበለ ወደ እናቱ ሮጦ በመሄድ አጥልቆላታል።
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው ተመራቂ ተማሪ ዳግም ተስፋዬ ይህን አስደናቂ ተግባር ፈጸሟል።
ተመራቂው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዕፅዋት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ከወሰዳቸው 64 ኮርሶች 54ቱን ኮርሶች A+ በማምጣት የወርቅ ተሸላሚ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ወይዘሮ_እህተ_በቀለ #ዮርዳኖስ_ወሮታው👏
" አራት ዓመት ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ በማዕረግ አስመርቄያለሁ " - ወይዘሮ እህተ በቀለ
ወይዘሮ እህተ በቀለ ይባላሉ። ልጃቸው ዮርዳኖስ ወሮታው አካሏን በራሷ ማንቀሳቀስ የማያስችል ጉዳት አለባት።
ዮርዳኖስ በእናቷ ድጋፍ ዛሬ ትምህርቷን አጠናቃ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ከሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል #በማዕረግ ተመርቃለች፡፡
እናት አህተ ፤ " አራት ዓመት ሙሉ ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ አጠናቅቄያለሁ። አራት ዓመት ለእኔ እንደ አራት ቀን ነው። ምንም አልተሰማኝም ደስ ብሎኝ አልፏል" ብለዋል።
በአራት ዓመት የትምህርት ቆይታዋ የሚሰጣትን ትምህርት ክፍል ውስጥ አብረዋት ቁጭ ብለው እየጻፉላት እንዳስተማሯት እናት ለኢፕድ ተናግረዋል።
" ዮርዳኖስ የማንበብ ችሎታዋን እወድላታለሁ። ያነበበችውን አለመርሳቷንና አስተዋይነቷን እወድላታለሁ፤ ልጄ ትጉህ ናት " ሲሉ ገልጸዋል።
ዮርዳኖስ እስከ 12ኛ ክፍል በሞግዚት ድጋፍ የተማረች መሆኑን ጠቅሰው እንደምትችል መታየት አለበት ብዬ አራት ዓመት በዩኒቨርሲቲ አብሬያት ዘልቀናል ብለዋል፡፡
አትችልም የተባለች ልጅ ለዚህ በመብቃቷ ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቅሰው፤ የእርስዋ ብርታት እንደ ልጃቸው ቤት ለተዘጋባቸው ልጆች አርአያ የሚሆን መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
መኖሪያ ቤታቸው ከዮኒቨርሲቲው ራቅ ያለ በመሆኑ ጠዋት 12 ሰዓት ተነስተው ለአራት ዓመታት ልጃቸውን ወደ ትምህር ገበታዋ በዊልቸር በማመላለስ ለምረቃ ያበቁት እናት ዛሬ ደስታቸው እጥፍ ድርብ ሆኖ ታይተዋል።
Credit : EPA