ፎቶ ፦ በመቐለ የፀጥታ ኃይሎች በሓድነት ክፍለ ከተማ ባካሄዱት ኦፕሬሽን ትውልዱን እያጠፉና አደጋ ላይ እየጣሉ ነው ያሏቸውን አደገኛ ዕፆችንና መጠቀሚያቸውን በማቃጠል እንዲወገዱ አድርገዋል።
Photo Credit : Tigrai Television
@tikvahethiopia
Photo Credit : Tigrai Television
@tikvahethiopia
" የሰላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉና ዘላቂነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ሲደረግም አሜሪካ የኢትዮጵያን የአጎዋ ተጠቃሚነት ዳግም ለመመለስ ቁርጠኛ ናት " - አንቶኒ ብሊንከን
ብሊንከን ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ለመመለስ ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ገለፁ።
አሜሪካ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ሙሉ ተግባራዊነት ተከትሎ ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ እድል ተጠቃሚነት ለመመለስ ቁርጠኛ መሆኗን በአዲስ አበባ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መናገራቸውን ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ዘግቧል።
ብሊንከን ለፋና በሰጡት ቃለመጠይቅ አሜሪካ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራች ነው ብለዋል።
ይህም አሜሪካ፥ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ያላትን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያበረታታ ተናግረዋል።
የሰላም ስምምነቱ በሚመለከታቸው አካላት ሙሉ በሙሉና ዘላቂነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ሲደረግም አሜሪካ ኢትዮጵያን ምርቶቿን ከኮታና ቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ እንድታስገባ ወደ ሚፈቅደው የአጎዋ ተጠቃሚነት ዳግም ለመመለስ ቁርጠኛ ናት ብለዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቃለ መጠይቁ ወቅት " ኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕን ለመተግበር የጀመረችውን ጥረት አድንቀዋል ያለው " ፋና ብሮድካስት " የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ሒደት በጥሩ ሁኔታ እየተፈጸመ መሆኑን ገልፀዋል ብሏል።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NEBE : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ ለማካሄድ እያጋጠሟቸው ያሉትን የሕግ ጥሠቶች አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከላይ የተያያዘውን ደብዳቤ ልኳል።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እንደ ሀገር ምንም አይነት የምርት እጥረት የለም "
የጤፍና ሌሎች የምርቶች ዋጋ ንረትን በተመለከተ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ፣ ከኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ እና ከፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥቷል።
በዚህም መግለጫ ወቅት የምርት እጥረት የለም ተብሏል።
ሚኒስቴሩ " የምርቶች የዋጋ ንረት በምርት እጥረት ሳይሆን በህገ-ወጦች አማካኝነት ምርት ወደ ገበያ እንዳይገባ በመደረጉ ነው " ብሏል።
" እንደ ሀገር ምንም አይነት የምርት እጥረት የለም " ያለው ሚኒስቴሩ " የዋጋ ንረቱ የተከሰተው የንግድ ፈቃድ የሌላቸው አካላት ምርቱን በከፍተኛ ዋጋ ገዝተው በመደበቃቸውና ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ ወደ ገበያ ውስጥ እንዳይገባ በማድረጋቸው ነው " ሲል ገልጿል።
ችግሩን ለመቅረፍ ክልሎች ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመስራት ህገ-ወጦችንና ህገ-ወጥ ተግባራቸውን በመግታት በህጋዊ ነጋዴዎች እና በህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ምርት ወደ ገበያ የሚገባበት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል ብሏል።
በአሁኑ ወቅት ዩኒዮኖች እና የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ጤፍና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ምርቶችን በተመጣጠነ ዋጋ ወደ አዲስ አበባ እያስገቡ በመሆኑ ሸማቹ ህብረተሰብ ተረጋግቶ እንዲሸምት በመግለጫው ጥሪ ቀርቧል፡፡
በኦሮሚያ ክልል እና በአማራ ክልል ከደህንነት ኬላዎች ውጪ ምንም አይነት የምርቶችን ህጋዊ እንቅስቃሴ የሚገድቡ ኬላዎች ባለመኖራቸው ማንኛውም ህጋዊ ነጋዴ የንግድ ፈቃዱን ይዞ ምርቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ ማቅረብ የሚችል በመሆኑ በህገ-ወጥ መንገድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ተከታትሎ እርምጃ የመውሰድ ስራ እንደሚሰራም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳውቋል።

" መርሀባ "
አማራ ባንክ አ.ማ " መርሀባ " ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን እንዲሁም ለአገልግሎቱ የተዘጋጀውን ኮር ባንኪንግ (Multiple Company Multiple Book) ሲስተም ትግበራ ለባንክ ኢንደስትሪው በማስተዋወቅ ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ ሥራ እንደሚያስጀምር ዛሬ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።
ባንኩ ወደ ሥራ ከገባ ጀምሮ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጾ እስከ አሁን ከ35 ሺህ በላይ የመርሃባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች ማፍራት እንደቻለ አመልክቷል።
በዚህ ዓመት መጨረሻም ሙሉ በሙሉ መርሃባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ 30 ቅርንጫፎችን እንደሚከፍትም ባንኩን በላከልን መግለጫው ገልጿል።

" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " - ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ
የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
ሙሴቬኒ ይህን ያሉት አገራቸው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ አዲስ ሕግ እያረቀቀች ባለችበት ወቅት ነው።
የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀል በሆነባት ኡጋንዳ እየተረቀቀ ያለው ሕግ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ላይ የበለጠ ጠንካራ ቅጣት የሚጥል ነው።
ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ትናንት ሐሙስ መጋቢት 07/2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ይህን ብለዋል ፦
" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ።
ምዕራባውያን የራሳቸውን አሰራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው።
አውሮፓውያኑ የአጎት እና የአክስት ልጅ ጋር ትዳር ይመሰርታሉ እዚህ [ኡጋንዳ] የአንድ ጎሳ አባልን ማግባት ነውር ነው።
እነሱ የቅርብ ዘመድ እንዳያገቡ ማዕቀብ እንጣል ? ይህ የእኛ ሥራ አይደለም። "
ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን አፈንጋጭ ብለው የገለጿቸው ሲሆን በጉዳዩ ላይ ብዙ ምክክር መደረግ አለበት ብለዋል።
ኡጋንዳ አሁን ላይ እያረቀቀች ባለችው ሕግ መሠረት በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ውስጥ ያለ ወይም እራሱን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪ ብሎ የሚገልጽ ሰው እስከ 10 ዓመታት የእስር ጊዜን እንዲያሳልፍ ያዛል።
የኡጋንዳ መንግሥት በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የውጭ አገራት መንግሥታት ተቋማት እና ምዕራባውያን ኤጀንሲዎች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን እያስተዋወቁ ነው በማለት ይከሳል።
#ቢቢሲ

#አፋልጉን
በአዲስ አበባ ሳሪስ አዲስ ሰፈር በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች " ቤዛዊት በቀለ " የምትባል ሞግዚት / ግለሰብ ከምትሰራበት ቤት የ2 ዓመት ህጻን የሆነችውን ሶልያና ዳንኤልን (ከላይ በፎቶ ተያይዟል) ከቤት ይዛት መሰወሯን ቤተሰቦቿ ገልጸውልናል።
እናት እና አባትን ጨምሮ መላው ቤተሰብ ጭነቅት ላይ የሚገኙ ሲሆን የንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ ጉዳዩን እንዲያውቀው ተደርጓል።
ህፃን ሶልያና ዳንኤልን ይዛ የተሰወረችው የቤት ሰራተኛ መታወቂያም ሆነ ፎቶ ባይኖራትም መንገድ ላይ እሷ ትሆን ብሎ የሚጠራጠር መልኳ ቀይ፣ መካከለኛ ቁመትና ቀጠን ያለች በተደጋጋሚ ታይትና ሻሽ የምትለብስ ሴት ናት ተብሏል።
ህፃን ሶሊያና በወቅቱ ሶቢጫ ኮፍያ ያለው ሹራብ ከክፍት ጫማ ጋር አድርጋ ነበር።
አጠራጣሪ ነገር በመንገድ ላይ / በየትኛውም ቦታ ስትመለከቱ በ0951090999 (ዳንኤል) እንዲሁም በ0947365252 (ዮብዳር) ብላችሁ ደውሉ።
https://yangx.top/tikvahethmagazine/19071
Via : @tikvahethmagazine

#GetachewReda #AntonyBlinken
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከህወሓት አመራሮች አንዱ ከሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።
አቶ ጌታቸው ረዳ አዲስ አበባ ላይ ከብሊንከን ጋር መገናኘታቸውንና ስለ ሰላም ስምምነቱ አተገባበር እድገት እና ስላሉት እንቅፋቶች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው ፤ በውይይቱ ወቅት #ለሰላም ያላቸውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንዲሁም ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የሚፈጥሩትን ተግዳሮቶች ለመወጣት በእነሱ በኩል ያላቸው የማያወላዳ ቁርጠኝነት እንዳረጋገጡ ገልጸዋል።
" ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረትን ጨምሮ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት ሁሉ እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን " ሲሉም ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ከብሊንከን ጋር በነበረው ውይይት በትግራይ ውስጥ እና በትግራይ ላይ በተደረገው ጦርነት ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አስፈላጊት ላይ ሃሳባቸውን እንዳካፈሉ አመልክተዋል።
አቶ ጌታቸው፤ ጠንካራ የሽግግር የፍትህ ማእቀፍ ተቀባይነት ያለውና የሚያስመሰግን ቢሆንም በትግራይ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ከሀገራዊ ማዕቀፍ የዘለለ በመሆኑ ዓለም አቀፍ ጥረቶች አስፈላጊ ናቸው የሚል አቋማቸውን እንደገለፁ አስረድተዋል።
አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው ፤ ሀገራቸው አሜሪካ የሰብአዊ ድጋፍን ለማጠናከር፣ ለመልሶ ማቋቋም ሃብት ለማሰባሰብ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በመላው ቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከስምምነቱ ተዋናይ ወገኖች ጋር በጋራ እንደምትሰራ በድጋሚ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

" 13 ሰዎች ሞተዋል ፤ በርካታ እንስሳት በጎርፍ ተወስደዋል " - የኮንሶ ዞን
በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ገርጨ እና አይሎታ ደካቱ ቀበሌዎች ነፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት 13 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ እንስሳት በጎርፍ መወሰዳቸውን ዞኑ አሳውቋል።
የጎርፍ አደጋው የተከሰተው በሰገን ዙሪያ ወረዳ ዶዴ እና መገርሳ ወንዞች መሆኑን ተገለፀው ዞኑ በአካባቢው አሁን እየዘነበ ያለው ዝናብ ከ4 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ገልጿል።
ዝናቡን ተከትሎ ህብረተሰቡ ለተጨማሪ የጎርፍ አደጋ እንዳይጋለጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የዞኑ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል፡፡
በተጨማ ህፃናትና ታዳጊዎች በወንዞች አቅራቢያ እንዳይንቀሳቀሱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ምንጭ፦ የኮንሶ ዞን ኮሚኒኬሽን/ኤፍ ቢሲ

#Update
የተቋረጠው #የባጃጅ_ትራንስፖርት አገልግሎትን አስመልከቶ ዛሬ መጋቢት 8/2015 ዓ.ም መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ ከሰዓት 9 ሰዓት የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም የተቋረጠውን የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጥ " አሻም ቴሌቪዥን " ዘግቧል።
የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ አሽከርካሪዎች የዕለቱ ጉርሳቸውን ማጣታቸውን፣ ተጠቃሚዎችም ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን እየገለፁ እንደሚገኙ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን /ኢሰመኮ ትላንት ባወጣው መግለጫ የባጃጅ ትራንስፖርት እገዳው እንዲነሳ መጠየቁ ይታወሳል፡፡
Credit : #AshamTV