#Oromia #Afar
ዛሬ በኦሮሚያ ክልል እና በአፋር ክልል በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በኦሮሚያ ክልል አደጋው የደረሰው በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ሲሆን በአደጋው የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ከ6 ሟቾች በተጨማሪ 15 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
አደጋው ከአዳባ ከተማ ወደ ላጆ ከተማ ሲጓዝ በነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ መኪና በመገልበጡ የተከሰተ ነው።
መኪናው የመጫን ልኩ 28 ሰው ብቻ የነበረ ቢሆንም ከመጠን በላይ በመጫን 40 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ አደጋው መድረሱ ተገልጿል፡፡
በአፋር ክልል ደግሞ የትራፊክ አደጋ የደረሰው በሎጊያ ከተማ ሲሆን መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ተሽከርካሪው ጥዋት ከሎጊያ 15 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ አፍዴራ ሲጓዝ ኮሪ ወረዳ ልዩ ቦታው " ጉያህ " ላይ ተገልብጦ ነው አደጋው የደረሰው። 5 ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ 10 ሰዎች ቀለል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው።
አሸክርካሪዎች ይዛችሁ የምትጓዙት ክቡር እና የማይተካውን የሰው ህይወት ነው እና ሁሌም ጥንቃቄ ማድረግ፣ ህግ እና ስርዓትን ማክበር አትዘንጉ።
@tikvahethiopia

የንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል።
በስርዓተ ቀብሩ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ የዓለም ሀገራት መሪዎች ተገኝተው ነበር።
@tikvahethiopia
በስርዓተ ቀብሩ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ የዓለም ሀገራት መሪዎች ተገኝተው ነበር።
@tikvahethiopia
መሪዎቹ በለንደን...🚌
በንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ወቅት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና የሀገራት ተወካዮች #በአውቶብስ እንዲጓጓዙ ሲደረግ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በራሳቸው ጥይት መከላከያ ባላት " ዘ ቢስት " የተሰኘችው ሊሞዚን እንዲጓዙ መደረጉ መነጋገሪያ ሆኗል።
ዛሬ የንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊ ስርዓተ ቀብር ተፈፅሟል።
ለዚሁ የቀብር ስነስርዓት ለንደን የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ተወካዮች ለስነስርዓቱ በአውቶብስ እንዲጓዙ የዩኬ (UK) መንግስት አመራር ሰጥቶ እንደነበር ተሰምቷል።
መንግስት ይህን ያደረገው ከደህንነት አንፃር ሲሆን በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሀገራት መሪዎች በአንድ ጊዜ መገኘታቸው ሁሉም የራሳቸውን መኪና እንዲጠቀሙ ማድረግ ከደህንነት አንፃር የማይታሰብ እንደሆነበት ነው የተነገረው።
ከሌሎች መሪዎች በተለየ ግን የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ባይደን በራሳቸው የግል መኪና " ዘ ቢስት " እንዲጓዙ መደረጉ መነጋገሪያ ሆኗል።
በተለይ የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ፣ የታንዛኒያዋ ሳሚያ ሱሉሁን ጨምሮ አፍሪካ መሪዎች በአንድ ባስ ውስጥ ሆነው የሚታዩበትን ፎቶ ከባይደን ጋር በማነፃፀር " ለአፍሪካ መሪዎች የተሰጠው ዝቅተኛ ክብር " በሚል በርካታ አፍሪካውያን ሲቀባበሉት ውለዋል።
ምንም እንኳን በስፋት የአፍሪካውያን መሪዎቹ አንድ አውቶብስ ውስጥ ያሉበት ፎቶ ቢታይም የቤልጂየሙ ንጉስ እና ንግሥት፣ የስፔኑ ንጉሥ እና ንግሥት ፣ የስዊድን ንጉሥ እና ንግሥት እና የኔዘርላንድ ንጉሥ እና ንግሥት የግል መኪናቸውን አልተጠቀሙም ተብሏል።
የቻይና ልዑካንም በአውቶብስ እንዲጓዙ መደረጉ ተነግሯል።
የመረጃ ምንጭ ዘ ኢንዲፔንደንት እና ሌሎች ፤ ምስል ከሶሻል ሚዲያ ፤ አንደኛው ምስል ቅንብር የKenyans.Co.ke ነው።

በዓለም አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድር ለሩብ ፍጻሜ የደረሰው ኢትዮጵያዊው ወጣት !
አቤል ዳኜ የሠራው በሁካታ መሃል ሆኖ ድምፅን ማጥፋት የሚቻልበት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ፅንሰ ሃሳብ የሚያስረዳው ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።
ነዋሪነቱን በአሜሪካ ያደረገው አቤል ዳኜ የ18 ዓመት ወጣት ሲሆን " ብሬክስሩ፣ ጁኒየር ቻሌንጅ " በተሰኘ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ሂሳብ ውድድር ላይ ከ2400 ሰዎች መካከል ለዕሩብ ፍጻሜ ከደረሱ 30 ሰዎች አንዱ መሆን ችሏል።
ለ #ቪኦኤ በሰጠው ቃል " ኮምፒውተር ሳይንስ ፍቅሬን ያዳበርኩት ከአባቴ ነው " የሚለው አቤል የወደፊት ፍላጎቱም ትምህርቱን ጨርሶ #ኢትዮጵያን መርዳት እንደሆነ ተናግሯል።
ባለፈው ክረምትም በደብረ ማርቆስ ሀዲስ ዓለማየሁ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚማሩ ከመቶ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ዌብ ግንባታ ሲያስተምር ቆይቷል።
አቤል ይህን " ብሬክስሩ " የተሰኘ ሽልማት ካሸነፈ የ250 ሺ ዶላር የነጻ የትምህርት ዕድል፣ 100 ሺ ዶላር ለተማረበት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ቤተ-ሙከራ ግንባታ እና እሱን ላበረታታ እና ላነቃቃ መምህር የ50 ሺ ዶላር ሽልማት የሚያገኝ ይሆናል።
ነገር ግን ይሄ ይሆን ዘንድ " ብሬክስሩ ቻሌንጅ " የፌስቡክ እና የዩቱብ ገጽ ላይ ሰዎች ላይክ፣ ኮሜንት በማድረግ እንዲያግዙት ጠይቋል።
የህዝብ ድምፅ አሰጣጡ #የመጨረሻ_ቀን ዛሬ መስከረም 10 (September 20) ነው። #አሁኑኑ በፍጥነት የሚከተሉትን 2 ቪድዮዎች ‘Like’ አድርጋችሁ ድምፃችሁን ስጡት።
1. Facebook https://www.facebook.com/watch/?v=595860615362156
2. YouTube https://www.youtube.com/watch?v=PzTAhCHoIMQ&feature=youtu.be

የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ !
የ5 አመቷን ህጻን የደፈረው ወልደሚካኤል አሚጋ የተባለ ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱን ከፍትህ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሹ ሚያዚያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 12፡30–3፡00 ሰዓት ባለው ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ክልል ልዩ ቦታው ደብረ-አባይ ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ዕድሜዋ 5 ዓመት የሆናትን የግል ተበዳይ እጇን ይዟት ወደ ታጠረ ባዶ ቦታ በመውሰድ መሬት ላይ በጀርባዋ አስተኝቶ ድርጊቱን ፈፅሟል።
ይህን ተከትሎም በፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የኮልፌ ቀራኒዮ ምድብ ዐቃቤ ህግ በፈፀመው በህፃናት ሴቶች ላይ የሚፈፀም የግብረ-ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል።
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ምድብ ሴቶችና ህፃናት የወንጀል ችሎት የቀረበው ተከሳሽ ወልደሚካኤል አሚጋ የተከሰሰበት ክስ በችሎት ተነቦለት የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ ተከራክሯል።
አቃቤ ህግም 4 የሰው ምስክሮችን አቅርቦ በማሰማት ተከሳሹ ድርጊቱን ስለመፈጸሙ በበቂ ሁኔታ አስረድቷል። በዐቃቤ ህግ በቀረበበት ክስ እና ማስረጃ መሰረት የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።
ፍ/ቤቱም ተከሳሽ ወልደሚካኤል አሚጋን በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደወሰነበት ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#Irreecha2015
የ2015 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል መስከረም 21 " ሆራ ፊንፊኔ " ፤ መስከረም 22 በቢሾፍቱ " ሆራ ሃርሰዴ " እንደሚከበር የኦሮሞ አባ ገዳዎች በዛሬው ዕለት አስታውቀዋል፡፡

TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia #Afar ዛሬ በኦሮሚያ ክልል እና በአፋር ክልል በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል። በኦሮሚያ ክልል አደጋው የደረሰው በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ሲሆን በአደጋው የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል። ከ6 ሟቾች በተጨማሪ 15 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። አደጋው ከአዳባ ከተማ ወደ ላጆ ከተማ ሲጓዝ በነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ መኪና…
በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በለጋምቦ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 5 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 15 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል
መነሻውን ከመካነ ሰላም በማድረግ ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ያደረገ የሰሌዳ ቁጥር ኢት 3-93269 የሆነ ሲኖትራክ የጭነት መኪና ለጋምቦ ወረዳ 029 ቀበሌ ልዩ ቦታው " እህል ማፍሰሻው " ከተባለው ስፍራ ሲደርስ መንገድ ስቶ ተገልብጧል (ማለዳ 12:00 ሰዓት ላይ) ።
በዚህም 5 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 15 ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የለጋምቦ ወረዳ ፖሊስ አደጋውን በተመለከተ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ከለጋምቦ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ትላንት በኦሮሚያ ክልል " አዳባ ወረዳ " እና በአፋር ክልል " ሎጊያ ከተማ " በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል።
ትላንት እና ዛሬ ብቻ በአማራ ፣ አፋር ፣ ኦሮሚያ በድምሩ 16 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ICHREE.pdf
233.1 KB
#ሪፖርት
በኢትዮጵያ ጦርነት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ በተመድ የተቋቋመው የሰብዓዊ መብቶች የባለሙያዎች ቡድን (ICHREE) 19ኝ ገፆች ያሉት የመጀመሪያ ግኝት ሪፖርት።