TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ተመድ የኢትዮጵያን ወታደሮችን ሸለመ።

643 #የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች በደ/ሱዳን ላደረጉት የሰላም ማስከበር አገልግሎት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሜዳሊያ ተቀብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ወደ ደቡብ ሱዳን ከተሰማሩ ወዲህ ግጭቶች እንዲቀንሱ ፣ የሰብአዊ ድጋፍ ለድጋፍ ፈላጊዎች በፍጥነት እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች የተደረገው የእውቅና ስነ ስርዓት ላይ የተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው እንደነበር #UNMISS ን ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በዛሬው ዕለት በነገሌ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎች ምርጫ እየተካሄደ ነው።

ምርጫው ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ ነው እየተካሄደ ሚገኘው።

ለምርጫው ከ150 በላይ ታዛቢዎችና የምርጫ አስፈጻሚዎች መመደባቸውን ተገልጿል።

በምርጫ ክልሉ ለሁለቱም ምክር ቤቶች ሁለት በግል፣ አንድ ከኢዜማ እንዲሁም አራት ከብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎች ለውድድር ቀርበዋል። #ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አውሎ #ኢትዮፎረም

ከሳምንት በፊት ተይዘው የነበሩት የአውሎ ሚዲያ እና የኢትዮ ፎረም ባለሙያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለቢቢሲ ተናግሩ።

ጠበቃ ታደለ የሚዲያ ባለሙያዎቹ ከታሰሩ ከ1 ሳምንት በላይ ቢያልፍም እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና ያሉበትን ቦታ ቤተሰቦቻቸው ማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል።

የሚዲያ ባለሙያዎቹ የተያዙት በፌደራል ፖሊስ መሆኑን እና በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ወቅት በተለምዶ ሜክሲኮ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርምራ ማዕከል መወሰዳቸውን ተናግረዋል።

"እስከ አርብ ሰኔ 25 ድረስ ቤተሰብ ሲጠይቃቸው እና ምግብ ሲያደርስ ነበር። ከዛ በኋላ ግን 'ተለቀዋል እዚህ የሉም' ተብለዋል። ቤተሰብ ሊያገኛቸው አልቻለም። ፍርድ ቤትም እስካሁን አልቀረቡም" ሲሉ ገልፀዋል።

የሚዲያ ባለሙያዎቹ ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ከመደረጉም በላይ የተያዙበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንዳልተነገራቸው ጠበቃ ታደለ ተናግረዋል።

ጠበቃ ታደለ፥ "የባለሙያዎቹን እስር በተመለከተ ፖሊስ በአንድ መገናኛ ብዙኃን ሲጠየቅ ባለሙያዎቹ የታሰሩት ከአሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት ስላላቸው ነው የሚል ምላሽ እንደሰጠ አንብቤያለሁ። ከዛ ውጪ ግን ለእኛ በግልጽ አልተነገረንም" ብለዋል።

ጠበቃው፥ "ቤተሰብ በጣም ተጨንቆ ወደ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሄደው አቤቱታ አቅርበው ነበር። ሰኞ እና ማክሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብለን እየጠበቅን ነበር ግን ሳይቀርቡ ቀርተዋል" ሲሉ ገልፀዋል።

በአገሪቷ ሕጎች ላይ የዘፈቀደ እስር ሊኖር እንደማይገባ የገለፁት ጠበቃ ታደለ፤ ደንበኞቻቸው በተያዙ በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ነበረባቸው ነገር ግን አልቀረቡም በዚህም የአገሪቷ ሕግ ተፈጻሚ ሳይሆን ቀርቷል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። #BBC

@tikvahethiopia
ሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር አሰራጭቷል የተባለ ግለሰብ የ6 ወር እስራት ተፈረደበት።

በጋሞ ዞን ሠላምበር ከተማ አስተዳደር ሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግርን ሲያሰራጭ የነበረ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።

ተከሳሹ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃን ቀጥታ በሆነ መንገድ በግሉ በሚጠቀመው የፌስቡክ ገፁ ላይ በማሰራጨት ወንጀል ተከሷል ተብሏል።

ከተከሳሽ ፌስቡክ ገፅ የተወሰዱ የፎቶ መረጃዎችና የጻፋቸው ጽሁፎች የዐቃቤ ህግ ማስረጃዎች ሆነዉ ቀርበዋል።

የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስረጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1185/2012 በመተላለፉ ሁለት ክስ እንደተመሰረተበት ፍርድ ቤቱ ገልጿል።

ከዐቃቤ ህግ የቀረበለትን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በጥልቀት የተመለከተው የሠላምበር ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ መምህር አንተነህ ዘውዴ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ 6 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

መረጃው ከጋሞ ዞን ዐቃቤ ሕግ መምሪያ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#UNSC

ዛሬ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ይመክራል።

ስብሰባው ላይ ለመካፈል የኢትዮጵያ ዉኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ወደ ኒውዮርክ ማቅናታቸውን አል አል ዐይን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳን በገጠሙት የግድቡ ዉዝግብ ላይ ለመነጋገር በሚያደርገው ስብሰባ ላይ #ኢትዮጵያን ይወክላሉ፡፡

በስብሰባው ላይም የኢትዮጵያን አቋም ያንጸባርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያን ከሚወክሉት ዶ/ር ኢ ር ስለሺ በቀለ በተጨማሪ በስብሰባዉ ላይ የግብፅና የሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የሚገኙ ይሆናል፡፡

ከሶስቱ ሀገራት ሚንስትሮች በተጨማሪ ፦
- በአፍሪቃ ቀንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ፣
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ
- የወቅቱ የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበር የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዲፕሎማት ለተሰብሳቢዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አል ዓይን አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :

• የላብራቶሪ ምርመራ - 4,964
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 116
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 68

አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 276,799 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,341 ህይወታቸው ሲያልፍ 261,817 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 2,055,126 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
#GERD🇪🇹#ItsMyDam

ዛሬ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ግብፅ እና ሱዳን ባቀረቡት ጥያቄ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስብሰባ ይቀመጣል።

በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምክር ቤቱ የጠራውን ስብስባ በመቃወም ኒው ዮርክ በሚገኘው የተመድ (UN) መስሪያ ቤት ተገኝተው በአሁን ሰዓት ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

ሰልፉ እስከ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ድረስ ይቆያል።

"የፀጥታው ም/ቤት በሕዳሴ ግድቡ ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ማቆም አለበት" የሚለውን መልዕክት ማስተላለፍ ዋነኛው የሰልፉ ዓላማ እንደሆነ ተገልጿል።

በሰልፋ ላይ ለድርጅቱ የሚሰጥ ደብዳቤ መዘጋጀቱ ተገልጿል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#GERD 🇪🇹 #ItsMyDam

- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ያለው ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን እኤአ በ2015 በመሪዎቻቸው አማካኝነት በሱዳን ካርቱም በፈረሙት የመርህ ስምምነት መሰረት ነው።

- ኢትዮጵያ የመርህ ስምምነቱን መሰረት በማድረግ የግድቡን የግንባታ ደረጃ ተከትላ የውሃ ሙሌቱን ማከናወኗን ትቀጥላለች። በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የ18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ኪውቢክ ሜትር ውሃ ሙሌት ተጀምሯል እንጂ አልተጠናቀቀም ብለዋል።

- የ2ኛው ዓመት የውሃ ሙሌት ነሃሴ መጨረሻ ላይ የጠናቀቃል።

- ታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ባለፈው ዓመት ክረምት 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ይዟል፤ በዘንድሮው ክረምት ደግሞ 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዝ ይሆናል።

#EngineerGedionAsfaw

@tikvahethiopia
#Update

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ መምከር ጀምሯል።

ስብሰባውን በቀጥታ በ United Nations የዩትዩብ ቻናል መከታተል ትችላላችሁ።

#ItsMyDam

@tikvahethiopia
አጭር መረጃ ፦

- የUN የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

- የፀጥታው ምክር ቤት አባል የሆኑ አገራት ተወካዮች የጋራ ተጠቃሚነት መርህን ባከበረ መልኩ የህዳሴ ግድብ ድርድር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ድርድሩ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

የግድቡ ድርድር በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እንዲቀጥል ካሉት መካከል ፦

- ጎረቤታችን ኬንያ
- አሜሪካ፣
- ሩሲያ፣
- አየርላንድ፣
- እንግሊዝ፣
- ሜክሲኮ፣
- ህንድ ይገኙበታል።

- የግድቡ ድርድር በአፍሪካ ህብረት እንዲሆን ፍላጎታቸውን የገለፁ ሀገራት ችግሩ የሚፈታው ሶስቱ በአፍሪካ ህብረት በሚያደርጉት ውይይት እንጂ በሌሎች ሀገራት ጣልቃ ገብነት ሊሆን አይገባም ሲሉ አቋም አንፀባርቀዋል።

@tikvahethiopia
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በፀጥታው ም/ቤት ምን አሉ ?

- የUN ፀጥታው ም/ቤት የህዳሴ ግድቡን ጉዳይ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመልሰው ጠይቀዋል።

- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ መነሳቱ የምክር ቤቱን ጊዜ ማባከን እንደሆነ ኢትየጵያ እንደምታምን ገልፀዋል፤ በፀጥታው ምክር ቤት መድረክ ላይ የቀረቡ የመጀመሪያው የውሃ ሚኒስትር ሳይሆኑን እንዳልቀሩም ተናግረዋል።

- የጸጥታው ምክር ቤት የፖለቲካ እና የጸጥታ ጉዳይን ብቻ የሚመለከት ተቋም ነው፤ የውሃ ጉዳይ እንዲያይ መደረጉ አግባብ አይደለም ብለዋል።

- የህዳሴው ግድብ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት በልጆቿ ላብና ደም እየገነባችው ያለው መሆኑ ይታወቅ ብለዋል።

- ኢትዮጵያውያን አባይ ውሃን የመጠቀም መብት እንዳላቸው የጸጥታው ምር ቤት ሊገነዘበው ይገባል ብለዋል።

- ኢትዮጵያ የዜጎቻን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት እና በስደት የሚንገላቱ ወጣቶቿን ለመታደግ ህዳሴ ግድብን እንደምትገነባ ገልፀዋል።

- ለሱዳንና ለግብፅ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር መፍትሔ የሚያገኘው በፀጥታው ምክርቤት ሳይሆን በሶስቱ ሀገራት ቀና መንፈስ በሚደረግ ውይይት ነው ብለዋል።

- የታላቁ ህዳሴ ግድብ በትክክለኛ ጊዜ በትክክለኛ ቦታ በኢትዮጵያውያን ሃብት እየተገነባ ያለ ግድብ መሆኑንና የግድቡ መሞላት ማንም የሚረዳው ፊዚክሳዊ ቀመር መሆኑን ገልፀዋል፤ ኮንክሪት ተሞልቶ ዝግጁ ከሆነ ውሃው መሞላቱ የሚጠበቅ ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/UNSC-07-08

@tikvahethiopia
"...ግብጽና ሱዳን ጉርብትናን፣ አብሮ መልማትን ሊማሩ ይገባል" - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጸጥታው ም/ቤት (UNSC) ሀላፊነት ጸጥታን በሚያደፈርሱ ጉዳዮች ላይ መከር እንጂ የኤሌትሪክ ማመንጫ ግድብን በሚለከት መወያየት ባለመሆኑ ጉዳዩ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ጠይቀዋል።

በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ዛሬ ለሊቱን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲመክር የሃገራቸውን የኢትዮጵያን አቋም ያስረዱት ሚንስትሩ ም/ቤቱም ከተመሰረተ ግዜ አንስቶ በግድብ ጉዳይ ሲመክር ይሄ የመጀመሪያው ነው ብለዋል።

ግብጽና ሱዳን ጉርብትናን፣ አብሮ መልማትን ሊማሩ ይገባል፤ የነሱ ፍላጎትም በቅኝ ግዛት ውል ሰበብ ውሃውን ለብቻቸው የመጠቀም ፍላጎት ነው አንዱ እየጠጣ ሌላው የሚጠማበት አካሄድ አግባብ አይደለም ነው ያሉት ሚንስትሩ።

"እንደ ህዳሴ ግድብ አይነት ፕሮጀክቶችን መገንባት ተሰደው ከሄዱበት ሃገር በባዶ እግራቸው የሚባረሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት የሚቀይርም ነው" ብለዋል።

በግብጽ ፍላጎት በተጠራው በዛሬው ስብሰባ በርካታ የምክር ቤቱ አባል አገራት የግድቡ ድርድር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

በስብሰባው ላይ የግብጽ እና ሱዳን ተወካዮች ንግግር አድርገዋል።

የሃገራቸውን የኢትዮጵያን አቋም ያስረዱት የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ምክር ቤቱ በህዳሴው ግድብ ላይ የሚያደርገው የመጨረሻው ስብሰባ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ በማለት ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ ጠይቀዋል ።

ምንጭ፦ የውሃ ፣ መስኖና፣ ኢነርጂ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሀይቲ ፕሬዝዳንት ተገደሉ። የሀይቲው ፕሬዝዳንት ጆቭኔል ሞይስ ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ በግል መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ መገደላቸው ተሰማ። የፕሬዜዳንቱ ባለቤት ጉዳት ደርሶባቸዋል። - ፕሬዚዳንቱ የተገደሉት መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው። - የፕሬዜዳንቱን ግድያ ያሳወቁት የሀገሪቱ ጊዜያዊ ጠ/ሚ ናቸው። - በሀገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ ከ2018 ጀምሮ ደግሞ በሙስና መበራከት ስልጣናቸውን እንዲለቁ የሚጠይቅ…
የሄይቲውን ፕሬዜዳት ማን ገደላቸው ?

የሄይቲ ፕሬዜዳንት ጆቭኔል ሞይስ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸው መገለፁ ይታወሳል።

ፕሬዝደንቱ የገደሉት 28 አባላት ያሉት ቅጥረኛ የገዳዮች ቡድን መሆኑ የሀገሪቱ ፖሊስ ስለማስታወቁ ቢቢሲ ዘግቧል።

ከእነዚህ መካከል 26ቱ #ኮለምቢያዊያን ናቸው 2ቱ ደግሞ #የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሄይቲያዊያን ናቸው ሲል የሀገሪቱ ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን አሳውቋል።

2ቱ አሜሪካዊያንን ጨምሮ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ ስምንቱ ደግሞ እየታሰሱ እንደሆነ ተሰምቷል።

በሕይወት ካሉት ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ዋና መዲናዋ ፓርቶፕሪንስ ውስጥ ከፖሊስ ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ የሞቱ እንዳሉም ታውቋል።

ጥቃቱን ማን እንዳቀደውና ዓላማው ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ባለፈው ረቡዕ ነው የታጠቁ ሰዎች ወደ ፕሬዝደንት ጆቭኔል ሞይስ መኖሪያ ቤት ገብተው ጥቃት የፈፀሙት።

በጥቃቱ ፕሬዝደንቱ ሲገደሉ ባለቤታቸው ማርቲን ቆስለው ፍሎሪዳ ወደሚገኝ ሆስፒታል ለሕክምና ተወስደው አሁን መልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተሰምቷል።

#BBC

@tikvahethiopia