TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ከሚዲያ ጠፍተው የከረሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ብቅ ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት የሰው ሰራሽ አካልና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን መጎብኘታቸውን ገልፀዋል።

ዶክተር አብይ አህመድ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሠራሽ አካልና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን የጎበኙት ዛሬ ረፋድ ላይ ነው።

ድርጅቱ ሰው ሰራሽ አካል እና ለመንቀሳቀስ ድጋፍ የሚሆን እንደ ክራንች ያሉትን እና ሰው ሰራሽ አካላትን በማምረት ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚዲያ ጠፍተው መክረማቸውን ተከትሎ ደህንነታቸውን በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ #ሀሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር ፤ በዚህም ቢሯቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ደህንነት በሚመለከት ትክክለኛ መረጃ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ወደ ንግድ ባንክ ሊገባ የነበረ ሃሰተኛ የብር ኖት ተያዘ።

በማእከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ባንክ ሊገባ የነበረ 29 ሺህ ሀሰተኛ ባለ ሁለት መቶ የብር ኖት መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ ሀሰተኛ የብር ኖቱ ትናንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሳንጃ ቅርንጫፍ ሊገባ ሲል መያዙን ገልጿል።

ባንኩ ባደረገው ማጣራት ገንዘቡ ሀሰተኛ መሆኑ መረጋገጡን ፖሊስ አሳውቋል።

ሀሰተኛ የብር ኖቶቹን ለማስገባት ሙከራ ያደረገው ግለሰብም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላል።

ፖሊስ ድርጊቱን በፈጸመው ግለሰብ ላይ ባደረገው ምርመራ ከወላጅ አባቱ ጋር በሬ ሸጠው ገንዘቡን እንደተቀበሉ ተናግራል። ፖሊስ የሀሰተኛ የብር ኖቶቹን ምንጭ ለመከታተል በግለሰቡ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ለኢዜአ አሳውቃል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...ሱዳን ቀድማ ወደነበረችበት ቦታ ሳትመለስ በድንበሩ ጉዳይ ድርድር አይኖርም" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብ እልባት ማግኘት የሚችለው በሰላማዊ የውይይት መድረክ ብቻ ነው የሚለው የኢትዮጵያ አቋም ዛሬም የፀና ነው ብለዋል። አምባደር ዲና ፥ በጉዳዩ ላይ እናደራድራችሁ ለሚሉ አገራትና ወገኖች ክብር…
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ያለውንና በቅርቡ የያዘችውም መሬት እንደማትለቀ ገለፀች።

የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና) ከፍተኛ የመከላከያ ኃላፊን ጠቅሶ፤ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያወዛግባት የነበረውን መሬት እንደማትለቅ ዘግቧል።

"ሱዳን ከአልፋሻጋ ይዞታ ቅንጣት ታህል እንደማትሰጥ ሜጀር ጀነራል ሀይደር አልቲራፊ አረጋግጠዋል። ለወታደራዊ ኃይል ምልመላ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል" ይላል የመንግሥታዊው ዜና አገልግሎት ዘገባ።

የሱዳኑ ጄነራል አልገዳሪፍ ውስጥ ፋላታ ከተባለው ጎሳ ድጋፍ በተቀበሉበት ወቅት ባደረጉት ንግግር "ሁሉም ዜጎች ልጆቻቸው ወታደራዊ ኃይሉን ተቀላቅለው የአገራቸውን ዳር ድንበርና ክብር እንዲያስጠብቁ እንዲያነሳሱ እጠይቃለሁ" ብለዋል።

የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ድንበር ላይ ያለውን ቀጠና ለማሳደግ የመንገድና የድልድይ ግንባታ ላይ እንደተሰማራ ተናግረዋል። "በቀጠናው የአገልግሎት ዘርፍ በመገንባት እንቅስቃሴን ምቹ ለማድረግም እየሠሩ ነው" ሲሉ አክለዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በማክሰኞ ሳምንታዊ መግለጫቸው ፥ "ኢትዮጵያ የድንበር ውዝግቡ እልባት ማግኘት የሚችለው በሰላማዊ የውይይት መድረክ ብቻ ነው የሚለው አቋም ዛሬም የፀና ነው፤ ከየትኛውም ድርድር በፊት ግን መቅደም ያለበት ቅድመ ሁኔታ አለ፤ ይኸውም ሱዳን መጀመሪያ ወደነበረችበት ቦታ መመለስና የያዘችውን መሬት መልቀቅ አለባት" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

Via Sudan News Agency, BBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#UnitedStates

የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ የአሜሪካ መንግሥት ማሳሳቡ ተሰምቷል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ለመገናኛ ብዙኃን በላኩት መግለጫ፤ ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ዘረፋ፣ መደፈር፣ እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፀሙ ታማኝ ከሆኑ ሪፖርቶች ሰምቻለሁ ብለዋል።

ቃል አቀባዩ አያይዘውም “በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን የኤርትራ ወታደሮች በሃይል ወደ ኤርትራ እየመለሷቸው ስለመሆኑ ማስረጃ አለ” ብለዋል።

አሶሼትድ ፕሬስ ከትግራይ ክልል የወጡ የዐይን እማኞችን ጠቅሶ ባጠናቀረው ዘገባ፤ የኤርትራ ወታደሮች ዘረፋ እንደሚፈፅሙ፣ ቤት ለቤት እየተዟዟሩ ሰዎችን እንደሚገድሉ እና ልክ እንደ አካባቢው አስተዳዳሪ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሃገር ከድተዋል ተብለው የሚታመኑትን የህወሓት አመራሮች ለመያዝ በሚያደርገው ውጊያ ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፈዋል ያለው ዘገባው ፤ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች መሳተፋቸውን ሙሉ ለሙሉ አስተባብሏል ብሏል። (አሶሼትድ ፕሬስ፣ የአሜሪካ ድምፅ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#UnitedStates የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ የአሜሪካ መንግሥት ማሳሳቡ ተሰምቷል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ለመገናኛ ብዙኃን በላኩት መግለጫ፤ ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ዘረፋ፣ መደፈር፣ እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፀሙ ታማኝ ከሆኑ ሪፖርቶች ሰምቻለሁ ብለዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም…
"...ስደተኞችን እያፈኑ ወደ ኤርትራ እየወሰዷቸው ነው የሚለው ክስ በወሬ ደረጃ ብንሰማም ከስደተኞች ማረጋገጫ አላገኘንም" - ሚስተር ክሪስ መልዘር (UNHCR ተወካይ)

ከቀናት በፊት የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኮሚሽን ዳይሬክተር ኣቶ ተስፋሁን ጎበዛይ እና የተመድ የስደተኞች ጉዳይ (UNHCR) የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስተር አን ኢንኮንትር ማይኣይኒ እንዲሁም ኣዲሃሩሽ የኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ ተገኝተው ጉብኝት አድርገው ነበር።

አመራሮቹ በጉብኝታቸው ከኣዲሃሩሽ የስደተኛ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

ስደተኞችን በሚመለከት መገናኛ ብዙሃን ስለሚያሰራጯቸው መረጃዎች እንዲሁም ስለስድተኞቹ ሁኔታ የUNHCR ተወካይ ሚስተር ክሪስ መልዘር ከትላንት ወዲያ ለቪኦኤ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ ሚስተር ክሪዝ መልዘር ገለፃ በጉብኝታቸው ስደተኞቹ ከዚህ በኃላ እንደማይራቡ ማረጋገጣቸውን ነገር ግን አሁንም ወደ ሰሜን ያሉ ሽመልባ እና ህፃፅ ስደተኛ ካምፖችን ሊጎበኙ አለመቻላቸውን ስጋት እንዳሳደረባቸው አሳውቀዋል።

ሚስተር ክሪስ መልዘር ፥ "አሁን ሁኔታው ጥሩ ነው ማለት ይቻላል ፤ ምክንያቱም ለ2 ወር ገዳማ ምንም አይነት ድጋፍ እያገኙ አልነበረም ፤ አጋራችን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በታህሳስ ወር ላይ የምግብ ራሽን ድጋፍ አድርጎላቸው ነበር፤ ለሁለተኛ ጊዜም የምግብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ከእንግዲህ አይራቡም ማለት ነው። ሆኖም ሌሎች ችግሮች አሉባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ኣቅርቦት ፣ ትምህርት ቤቶች፣ ክሊኒክን የመሰሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መዘጋታቸው ችግር ነው። ወደ ሰሜን በሚገኙት 2 የስደተኞች ካምፕ ግን የከፋ ችግር እንዳለ ነው የሚደርሱን መረጃዎች የሚያመላክቱት"

ቀጣዩን ያንብቡ : https://telegra.ph/UNHCR-01-28

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,003
• በበሽታው የተያዙ - 549
• ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ከበሽታው ያገገሙ - 266

አጠቃላይ 135,594 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,085 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 121,860 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

230 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢሶዴፓ ራሱን ከመድረክ አገለለ።

በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እራሱን ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) በማግለል በቀጣዩ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ በተናጠል እንደሚወዳደር አስታውቋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እንዳረጋገጡት በተለይ ለፓርቲያቸው ከመድረክ ለመውጣት መወሰን ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጋር እየተፈጠረ የመጣው ልዩነት ዋነኛው ምክኒያት ነው ብለዋል።

የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸው ኢሶዴፓ በራሱ ፈቃድ ከመድረክ እየተገለለ መምጣቱ እውን ቢሆንም ፊቺው ግን ገና በይፋ በጠቅላላ ጉባኤ ያልተደመደመ ነው ብለዋል።

ኦፌኮ በመድረክ ስር በተለመደው ሁኔታ ይቀጥላል ያሉት አቶ ሙላቱ የተለያዩ ፓርቲዎች መድረክን በጥምረት ለመቀላቀል ጥያቄ እያቀረቡም ይገኛሉ ነው ያሉት።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዓለም አቀፍ የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

- በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለፉት 24 ሰዓት 601,212 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፥ 16,388 ሰዎች በበሽታው ሞተዋል።

- አሜሪካ የ3,908 ዜጎቿን ህይወት በ24 ሰዓታት ውስጥ አፍጥታለች፥ ይህን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 443,769 ደርሷል።

- በUK ባለፉት 24 ሰዓታት የ1,239 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ፤28,680 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ብራዚል ባለፉት 24 ሰዓታት 1,439 ዜጎቿን በዚህ አስከፊ ወረርሽኝ አጥታለች፥60301 ዜጎቿም በበሽታው ስለመያዛቸው አረጋግጣለች።

- በጀርመን የሟቾች ቁጥር በእጅግ መጨመር እያሳየ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት የ862 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

- ሜክሲኮ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,623 ዜጎቿን ስታጣ፥17,944 ዜጎቿን ለቫይረሱ መጋለጣቸውን ሪፖርት አድርጋለች።

- በስፔን ዳግም የኮቪድ-19 ሞቾች ቁጥር እያሻቀበ ይገኛል፤ትላንት የ515 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ፤አጠቃላይ በበሽታው የሞቱ ሰዎች 57,806 ደርሰዋል።

- ጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 492 ዜጎቿን በኮቪድ-19 ስታጣ፥14,372 ዜጎቿ በቫይረሱ መያዛቸውን በምርመራ አረጋግጣለች።

- ደቡብ አፍሪካ በባለፉት 24 ሰዓታት የ555 ዜጎቿ ህይወት በአስከፊው ወረርሽኝ ስታጣ፤ 7,150 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በመላው አፍሪካ ትላንት 962 ሰዎች ሞተዋል፤ ከነዚህ መካከል 555 ከደ/አፍሪካ፣ 62 ከቱኒዝያ፣ 54 ከግብፅ፣ 17 ከሞሮኮ፣ 30 ከሊብያ፣ 13 ከጋና፣ 17 ከዛምቢያ ፣ 48 ከዝምባዌ፣ 38 ከሱዳን ይገኙበታል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ሪፖርት እንደሚያስረዳን 102,041,120 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፥ የ2,201,044 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 73,882,690 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
የባልደራስ የሰልፍ ጥሪ እና የፖሊስ ምላሽ ፦

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ ትላንት በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

ፓርቲው በእሁዱ ሰልፍ በ4 መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ መንግሥት ላይ ጫና ለመፍጠር አቅጃለሁ ነው ያለው፡፡

የፓርቲውን አመራሮች እስር፣ በአገሪቷ የተከሰተውን ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ፣ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ እየፈፀመ ነው የሚለውን የመሬት ወረራ እንዲሁም የሱዳን ኃይል የድንበር ጥሰትን መቃወም ዋነኞቹ አጀንዳዎቼ ናቸው ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ለጥር 23 በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያካሄድ እውቅና የተሰጠው አካል ያለመኖሩን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በዕለቱ እውቅና የተሰጠው ሰልፍ እንዳለ በማስመሰል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃም ሀሰት ነው ብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ የከንቲባ ፅ/ቤት አስተዳደር ጉዳዩች ዘርፍ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ/ም በቁጥር አ/አከፀ 18 /03/ 128 ለባልደረሳስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በፃፈው ደብዳቤ ሰልፉ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተቀባይነት እንዳለገኘ ምላሽ የሰጠ ሲሆን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በግልባጭ አሳውቋል ሲል ገልጿል።

ተቀባይነት ያላገኘ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ነው ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥር 23 በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ ሆነ መረጃውን እያሰራጩ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስቧል፡፡

ይህንን መልዕክት ተላልፈው ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት ላይ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስጠንቅቋል።

ምንጭ፦ አ/አ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ባልደራስ፣ አሐዱ ቲቪ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"ታይዋን ነጻ አገር ልሁን ካለች የሚከተለው ጦርነት ነው" - ዉ ኪን (የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ)

(በቢቢሲ የቀረበ)

ታይዋን ነጻ አገር ለመሆን አንዳች ሙከራ ካደረገች ጦርነት እንደሚገጥማት ቻይና አስጠነቀቀች።

ከቻይና እንዲህ ጠንከር ያለ የጦርነት ማስጠንቀቂያ ሲመጣ ይህ ከረዥም ጊዜ በኋላ የመጀመርያው ነው።

ማስጠንቀቂያው የመጣው ቤጂንግ የጦር አውሮፕላኖችን ወደ ደሴቲቱ አካባቢ ካስጠጋችና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የታይዋን ድንበር አካባቢ ማድረጓ ከተዘገበ ከቀናት በኋላ ነው።

ይህ ብቻ ሳይሆን ታይዋንና አሜሪካ አዲስና ጠንካራ ግንኙነት ለመጀመር ከተነጋገሩ በኋላ ቻይና ይህን ማለቷ አዲስ ስጋት ፈጥሯል።

አዲሱ የባይደን አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ከታይዋን ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክር ገልፆ ነበር።

ባለፈው ሐሙስ ዋሺንግተን ታይዋንን በመከላከያው ዘርፍ መደገፏን እንደምትቀጥል የሚገልጽ መግለጫ አውጥቷል።

ቻይና ታይዋንን እንዳመጸች አንዲት ግዛቷ አድርጋ ነው የምትመለከታት። ታይዋን ግን ራሷን እንደ አንድ ሉአላዊት አገር ነው የምትመለከተው።

የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዉ ኪን ሐሙስ ዕለት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ጠንከር ያለ ሐሳብ ሰንዝረዋል።

"ቆፍጠን ብለን መናገር የምንፈልገው ነገር ቢኖር ታይዋኖች በእሳት እንዳይጫወቱ ነው። እሳቱ ይበላቸዋል፤ ታይዋን ነጻ አገር ልሁን ካለች የሚከተለው ጦርነት ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ቻይና በታይዋን አቅራቢያ እያደረገች ያለችው ወታደራዊ እንቅስቃሴን "ትክክለኛ አካሄድ ነው፤ ብሔራዊ ሉአላዊነትንና ደኅንነትን ለማስጠበቅ የሚደረግ ነው፤ይቀጥላል" ብለዋል የቻይና መከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ።

ቀጣዩን ያንብቡ : telegra.ph/BBC-01-29

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopaia
ደም እንለግስ ህይወት እናድን !

የፊታችን እሁድ ጥር 23 በብሄራዊ የደም ባንክ (ስታዲየም) የደም ልገሳ እንደሚደረገ አቡጊዳ ሮታራክት ክለብ ለቲክቫህ አሳውቋል።

ይህ የደም ልገሳ ለ51ኛ ዙር መሆኑ ተገልጾልናል።

'ታላቅ ስጦታ የሆነውን ደም እንለግስ፥ ህይወት እናድን' የሚሉት አዘጋጆቹ በአ/አ ከተማ ነዋሪ የሆናቸው የቲክቫህ አባላት ደም በመለገስ የሰው ህይወት ታድኑ ዘንድ ጥሪ አውርበውላችኃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FaceBook

ፌስቡክ ተጠቃሚዎቹ የተለያዩ ማኅበራዊና ፓለቲካዊ ቡድኖችን እንዲቀላቀሉ የሚጠቁም መልዕክት ማስተላለፍ እንደሚያቆም አስታወቀ።

ይህ ውሳኔ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በገጻቸው ላይ የሚያዩትን ፓለቲካ ነክ ይዘት ከመቀነስ ጋር የተያያዘ ነው።

የአሜሪካ ምርጫ ሲካሄድ ፌስቡክ ለሳምንታት ያህል ፓለቲካዊ መልዕክቶችን ቀንሶ ነበር። አሁን ይህንን አሠራር በሌሎች አገራትም እንደሚተገብር ተገልጿል።

የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ "ሰዎች ፓለቲካና ግጭት መመልከት አይፈልጉም" ሲል ተናግሯል።

ማርክ ዙከርበርግ እንደሚለውም፤ ሰዎች ፌስቡክ ላይ የሚቀላቀሏቸው ቡድኖች "ጤናማና ቀና" እንዲሆኑ ይፈለጋል።

"ከፖሊሲያችን ጋር ባይጻረሩም ሰዎች እንዳይገቡ የምንፈልጋቸው ቡድኖች አሉ" ብሏል።

ማኅበራዊ እንዲሁም ፓለቲካዊ ቡድኖችን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንዲቀላቀሉ የሚላኩ ማስታወቂያዎችን ረዘም ላለ ጊዜ እንዳገዱም ገልጿል።

"ውጥረትን ለማርገብና በማኅበረሰቡ ዘንድ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ውይይት እንዲኖር የጀመርነው ሥራ አንድ አካል ነው" ሲል መስራቹ መናገሩን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia