TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Metekel

በመተከል ዞን የሽፍታ እንቅስቃሴ እያገዙ 'በሁለት ቢላዋ የሚበሉ' የጸጥታ መዋቅሩ አባላት አካሄዳቸውን ማስተካከል አለባቸው ሲል በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል አሳሰበ።

ማሰበቢያው የተሰጠው በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል በመተከል ዞን ለሚሰሩ የጸጥታ ሃይል አመራሮችና አባላት ስልጠና እየሰጠ ባለበት ወቅት ነው።

ግብረ-ሃይሉ በዞኑ ከሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው ውይይት በዞኑ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ላይ አንዳንድ የጸጥታ ሃይል አባላት እጃቸው እንዳለበት መገንዘቡን አስታውቋል።

በዞኑ የሚሰሩ የጸጥታ ሃይል አመራሮችና አባላት እንዲገመገሙና ሥልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑንም አሳውቋል።

ከጋንታ መሪ እስከ ብርጌድ አዛዥ የነበሩ 109 ፀረ-ሽምቅ፣ ልዩ ጥበቃና አድማ ብተና ልዩ ኃይሎች እንዲሁም በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ 37 የፖሊስ አመራሮች ስልጠናውን መውሰድ ጀምረዋል።

የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥና የግብረ-ሃይሉ አባል ብ/ጄነራል ዓለማየሁ ወልዴ፤ የጸጥታ ኃይሉ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን በእኩልነትና በተዓማኒነት የማገልግል ሃላፊነት አለበት ብለዋል።

ከዚህ በተቃራኒ የሚደረጉ ማናቸውንም አይነት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ በፍጥነት መቆም እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።

"የህዝብ አገልጋይ መስለው የሽፍታውን እንቅስቃሴ እያገዙ 'በሁለት ቢላዋ ለመብላት' ሲነቀሳቀሱ የነበሩ የጸጥታ መዋቅሩ አባላት አካሄዳቸውን ማስተካከል አለባቸው" ብለዋል።

"ማንኛውም የጸጥታ ኃይል ከህዝብ እና አገር በታች መሆኑን አስገንዝበው ፤ የተዘበራረቀ አስተሳሰብ የሚያራምዱ የጸጥታ መዋቅር አባላት ቆም ብለው መስመራቸውን ሊያጠሩ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ባለ 5 ሊትሩን ዘይት ከ360 ብር በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ተጀመረ !

በዘይት ዋጋ ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ አከበረኝ ውጋገን በቅርቡ በዘይት ዋጋ ላይ የተከሰተው የዋጋ ጭማሪ ምክንያታዊ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ዋጋውን ለማረጋጋት የንግድ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱም የዘይት ዋጋ ከ2 ወር በፊት ወደ ነበረበት የመሸጫ ዋጋ እንዲመለስ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ይሁን እንጂ በስምምነቱ መሰረት ዘይት ዋጋ ቅናሽ አለማሳየቱን በመዲናዋ ጉዳዩ ለመከታተል የተቋቋመው ግብረ ሃይል በዳረገው ቅኝት ማረጋገጡን አንስተዋል፡፡

በዚህ መሰረት ቢሮው ባለ 5 ሊትሩን ዘይት ከ360 ብር በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው የገለጹት፡፡

በዚህ መሰረት በትናንትናው ዕለት 240 በሚደርሱ የንግድ ተቋማት ላይ በተደረገ አሰሳ 10 የሚሆኑት ከስምምነቱ ውጪ ሲሸጡ መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን የገለጹት አቶ ወጋገን፣ ከዛሬ ጀምሮ 5 ሊትሩንን ዘይት 360 ብር በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ የማሸግ እርምጃ ይወሰዳል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን ነጋዴዎች ምርታቸውን ወደ ክልሎች ለማውጣት ሙከራ ያደርጋሉ የሚሉት ምክትል ሃላፊው ይህንን ለመቆጣጠር ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል የዘይት አስመጪዎች እና አከፋፋዮች በተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ ብቻ እንዲሰሩ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ አሳውቀዋል። ~ ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
ችሎት!

የእነ አቶ ጃዋር መሀመድን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተሰይሞ የነበረው የተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመመልክት ነበር።

ይሁንና ተከሳሾቹ ቤተሰቦቻቸን ችሎት ስላልታደሙ የእምነት ክህደት ቃላቸንን መስጠት አንችልም ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል።

አቃቢ ህግም ጊዜው በተገፋ ቁጥር የተከሳሾችም ሆነ የኛንም ጊዜ እየተወሰደ ይሄዳል ስለዚህ ጊዜው ታሳቢ ቢደረግ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

አቶ ጃዋርም የፍርድ ቤቱን ጊዜ ለመውስድ አይደለም ቤተሰቦቻችን መግባት ስላለባቸው ነው ሲሉ በፍርድ ቤቱ ያላቸውን እምነት ጥሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

አቤቱታውን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመመልከት ለጥር 27 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Mekelle

ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት ጀምሯል።

በመቐለ እና አዲሽሁ ከተማ መካከል የሚገኝ ፋይበር በመቆረጡ ምክንያት በትግራይ ክልል የስልክ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጸዓሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።

የስልክ አገልግሎት የተቋረጠው ከትናንትና ማምሻ ጀምሮ ነበር።

በመቐለ እንዲሁም ሌሎች አቅራብያ አካባቢዎች ያሉ ቡድኖች ገብተው ጥገና አድርገው አገልግሎቱ ጀምሯል።

እንደ ወ/ሪት ፍሬህይወት ገለፃ ፥ ኢትዮ ቴሌኮም በአጣዳፊ ግዜ አገልግሎት እንዲሰጥ በሚያስችለው መሳሪያ ታግዞ ነው አገልግሎቱን መጀመር የቻለው።

ሙሉ ለሙሉ በአካባቢው መጨናነቅ እንዳይፈጠር የፋይበር ጥገናው እየተከወነ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለው ገልፀዋል።

ፋይበሩ የተቆረጠው በተፈጥሮ ምክንያት አልያም ሆን ተብሎ በሰው መሆኑን ገና አለመታወቁን ወ/ሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል።

መረጃው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ለBBC አማርኛው ክፍል እና ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ከሰጡት የተቀናጀ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ገለጸ፡፡

ከትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ12ኛ ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

ፈተናው በበይነ መረብ (በኦንላይን) እንደሚሰጥ የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ገልጸዋል፡፡

ለፈተናው የሚያስፈልጉ የግብዓትና የስልጠና ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ዳይሬክተሩ መግለፃቸውን አሃዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce

ከህወሓት የታጠቀ ሃይል ጋር በመሰለፍ ከመቐለ እስከ ቆላ ተንቤን ሲዋጉ እንዲሁም ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።

በቀጥጥር ስር ከዋሉት መኮንኖች መካከል ዘጠኙ የሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ፤ ሰባቱ የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ ያላቸውና ሁለቱ ደግሞ የፖሊስ ኮማንደሮች መሆናቸው ተገልጿል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከህወሓት ቡድን ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሰለፉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ በድጋሜ ጥሪ ማቅረቡን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር ሜ/ጄነራል መሀመድ ተሰማ ዛሬ ማምሻውን ለኢዜአ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለአክሱም ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ፦

ለሁላችሁም የአክሱም ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ወደ "ኲሓ ካምፓስ" እንድትገቡ የተገለፀ ቢሆንም በተደረገው ማስተካከይ ወደ ዋና ጊቢ እንድትገቡ ተወስኗል። ይህን ተገንዘባችሁ በዋናው ግቢ ተገኝታችሁ report እንድታደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

መልዕክቱን ያደረሰን የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,852
• በበሽታው የተያዙ - 476
• ህይወታቸው ያለፈ - 8
• ከበሽታው ያገገሙ - 846

አጠቃላይ 135,045 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,083 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 121,594 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

217 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት! የእነ አቶ ጃዋር መሀመድን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተሰይሞ የነበረው የተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመመልክት ነበር። ይሁንና ተከሳሾቹ ቤተሰቦቻቸን ችሎት ስላልታደሙ የእምነት ክህደት ቃላቸንን መስጠት አንችልም…
የዛሬው የነአቶ ጃዋር የፍርድ ቤት ውሎ፦

(ጋዜጠኛ ስዩም ጌቱ~ዶቼ ቨለ ፣ ቪድዮና ፎቶ : OMN )

"...ቤተሰቦቻችን እንዳይገቡ በመከልከላቸውና ወንበሮቹ በደህንነት ሰዎች በመሞላታቸው ድርጊቱ ፍትህን የሚፈትንና እውነት እንዳይሰማ የሚደረግ ጥረት አድርገን ተረድተናል" -አቶ በቀለ ገርባ

"...መታወቂያ፣ቋንቋና የለበሱት ልብስ ታይቶ ቤተሰቦቻችን ወደ ችሎቱ እንዳይገቡ ተደርገዋል/ወደእስር ቤት ተወስደዋል"-አቶ ጃዋር መሃመድ

ዛሬ ጥዋት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ችሎቱ በሚሰየምበት አዳራሽ ውስጥ ተከሳሾች እና ጠበቆቻቸው ከፀጥታ አካላት ጋር ረዘም ላለ ደቂቃ ሲሟገቱ ነበር።

ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው በዚሁ ክርክር እና ውዝግብ ውስጥ እያሉ ከተባለው 3 ሰዓት ዘግይቶ የተሰየመው ችሎት ወደ ያዘው አጀንዳ ለመግባት ቢወጥንም ሁሉም ተከሳሾች ባሉበት ቆመው በችሎቱ ሂደት ቅሬታ እንዳላቸው ለፍርድ ቤቱ ያስረዳሉ።

ችሎቱ እንዳተሰየመ ቤተሰቦቻቸው ከችሎቱ ተሳትፎ መከልከላቸው ቅሬታ እንደፈጠረባቸው በመግለፅ ችሎቱ እንዴካሄድ ፍላጎት እንደሌላቸው በቆሙበት ለፍርድ ቤት አቤት ብለዋል።

አቶ በቀለ ገርባ፥"በታዘዝነው ሰዓት በአግባቡ ብንደርስም ክፍት መሆኑ የሚታወቀው ችሎት ቤተሰቦቻችን ውጪ በመከልከላቸውና ወንበሮቹ በደህንነት ሰዎች በመሞላታቸው ድርጊቱ ፍትህን የሚፈትን እና እውነት እንዳይሰማ የሚደረግ ጥረት አድርገን ለመረዳት ተገደናል" ሲሉ በነበረው ስሜት ችሎቱን ለማካሄድ በስነልቦና አለመዘጋጀታቸውን አስረድተዋል።

አቶ ጃዋር መሃመድ፥"መታወቂያ ቋንቋና የለበሱት ልብስ ታይቶ ቤተሰቦቻችን ወደ ችሎቱ እንዳይገኑ ተደርገዋል ወይም ወደእስር ቤት ተወስደዋል በዚህ አግባብ ችሎቱ መካሄድ የለበትም" ሲሉ ሞግተዋል።

ቀጣዩን ያንብቡ : telegra.ph/JM-01-27

@tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓታት የትኞቹ የዓለማችን ሀገራት ከፍተኛ የኮቪድ-19 ሞት አስተናገዱ ?
ምን ያህል ዜጎቻቸው በቫይረሱ ተያዙ ?

1ኛ. አሜሪካ : 3,912 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 151,727 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

2ኛ. ሜክሲኮ : 1,743 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 17,165 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

3ኛ. ዩናይትድ ኪንግደም : 1,725 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 25,308 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

4ኛ. ብራዚል : 1,319 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 63,895 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

5ኛ. ጀርመን : 986 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 15,611 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

6ኛ. ደቡብ አፍሪካ : 753 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 7,070 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

7ኛ. ሩሲያ : 594 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 17,741 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

8ኛ. ስፔን : 492 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 40,285 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

9ኛ. ጣልያን : 467 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 15,204 ዜጎቿ በይረሱ ተይዘዋል።

10ኛ. ኮሎምቢያ : 395 ዜጎቿ ሞተዋል ፤ 13,953 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

በአጠቃላይ በዓለማችን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 16,852 ሰዎች ሲሞቱ 590,732 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ ጊዜ አስንቶ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 101,441,979 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል ከ2.1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞተዋል፤ ከ73.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አገግመዋል።

#ዛሬም_ጥንቃቄ_አይለያችሁ!

#Purpose #Tikvah

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ከ3 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ተማሪዎችን የሚያስመርቀው ለ21ኛ ጊዜ ሲሆን ተመራቂዎች በኮሮና ቫይረስ የተቋረጠውን የማካካሻ ትምህርት ወስደው ያጠናቀቁ ናቸው። #DillaUniversity #ENA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ወደ 70 ሀገራት መስፋፋቱን ገለጸ።

የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱ በጣም እንዲስፋፋና ክትባቱ እንዲዳከም እንዲሁም የጸረ-እንግዳ አካል የመከላከል አቅምን ደካማ የሚያደርገው አዲሱ ቫይረስ በአንድ ሳምንት ከ10 በላይ በሆኑ ሀገራት መከሰቱን አስታውቋል፡፡

እንደ ድርጅቱ ገለጻ በፈረንጆቹ ጥር በብሪቴን የተከሰተው አዲሱ ቫይረስ እስካሁን በሁሉም ቀጣናዎችና አህጉር በሚገኙ 70 ሀገራት ተሰራጭቷል፡፡

ኮቪድ202012/01 ወይም ቢ.1.1.7 በመባል የሚታወቀው አዲሱ ቫይረስ ከመጀመሪያው ቫይረስ በቀላሉ የሚተላለፍ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ብቻ ከ10 በላይ የሆኑ ሀገራትን አዳርሷል፡፡

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲሱ ቫይረስ ገዳይ ነው ያሉ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት ግን ይህን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ጥናት ያስፈልጋል ብሏል፡፡ (አል ዓይን ኒውስ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Mekelle

በትግራይ ክልል በተከሰተውን የፖለቲካዊ ቀውስ እና አለመረጋጋትን እንደክፍተት ተጠቅመው ህብረተሰቡን ለእንግልት ሲዳርጉ እና ያለአግባብ የታሪፍ ክፍያ ጨምረው ሲያስከፍሉ የነበሩ ህገወጥ አሽከርካሪዎች ላይ የቅጣት እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የመቐለ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ፅ/ቤት ለትግራይ ቲቪ አስታውቋል።

የመቐለ ከተማ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከበደ አሰፋ እንደተናገሩት ከመቐለ ከተማ መነሻ በማድረግ ወደተለያዩ የክልሉ ክፍሎች የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ከመስመራቸው ውጭ ሲጭኑና ከተፈቀደላቸው ታሪፍ ውጭ የሚያስከፍሉ እንዲሁም ህብረተሰቡ ባለበት ችግር ላይ ለሌላ ተጨማሪ ወጪ ሲዳርጉ የነበሩ 78 አሽከርካሪዎች እንዲቀጡ ተደርገዋል።

አቶ ከበደ ኣሰፋ ፥ "... ታክሲዎች ቦታቸውን እንዲይዙ ፣ በመናኸሪያ የሚገኙ ተሽከርካሪዎችም በተገቢው መንገድ አገልግሎት እንዲሰጡ በሚዲያ ቢነገራቸውም መተግበር ስላልቻሉ የሚገባንን ስራ በመስራት ተመጣጣኝ ቅጣት በማስቀመጥ ስርዓት የማስያዝ ስራ እየሰራን እያስጠነቀቅን ቆይተናል። በዚህ መሰረት ማስተካከል ያልቻሉ አሽከርካሪዎች በህጋዊ መንገድ መቅጣት ጀምረናል። እስካሁን 78 ተሽከርካሪዎች ታፔላ ያላደረጉ እና ከመስመራቸው ውጭ ሲሰሩ የተገኙ በቁጥጥር ስር አውለናል። ሌሎች ኮድ3 ተሽከርካሪዎች ከመናኸሪያ ውጭ ሲሰሩ የተገኙ እና ተጓዦችን ያለአግባብ ክፍያ የሚጠይቁ በቁጥጥር ስር አውለናል" ብለዋል።

የመቐለ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ ኃላፊ ኢንስፔክተር ይርጋለም ገ/ፃድቅ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ባጋጠመው ችግር ተጎሳቅሎ ባለበት በዚህ ሰዓት በተጨማሪ አሽከርካሪዎች የሚደረገውን ማጎሳቆልን ለማስቀረት ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT