animation.gif
324.9 KB
ብርሃን ባንክ የትምርት ቤቶችን ክፍያ በዲጂታል ሥርዓት ማስተናገድ ጀመረ!
የክፍያ መንገዶች በማዘመን ሒደት ትምህርት ቤቶችን በዲጂታል የክፍያ አገልግሎት ተካታች የሚያደርግ ሥርዓት መዘርጋቱን ብርሃን ባንክ አስታውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴርም በሥርዓቱ አብሮ መሥራት ጀምሯል፡፡
ብርሃን ባንክ ሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ ያስጀመረው የትምህርት ቤቶች የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ‹‹ብርሃን ስኩል ፔይ›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
ወላጆች በሚያመቻቸው የክፍያ አማራጭ የልጆቻቸውን የትምህርት ቤት ክፍያዎችን ካሉበት ሆነው እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
ከስማርት ስልኮች በተጓዳኝ በማንኛውም ዓይነት የሞባይል ስልክ አገልግሎት የሚሰጥበት ይህ አሠራር ፣ የትምህርት ቤት ክፍያዎች ከሞባይል በተጨማሪ በኢንተርኔት መፈጸም ያስችላል፡፡
ባንኩ ከትምህርት ቤቶች ጋር ውል በመግባት እያንዳንዱ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ተማሪ የራሱ ሚስጥራዊ መለያ ቁጥር ተሰጥቶት በዚሁ መለያ ቁጥር ወይም ኮድ አማካይነት ክፍያ የሚፈጽምበት ዘመናዊ የክፍያ ዘዴ ለወላጆች እና ተማሪዎች ማቅረቡን ባንኩ ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ችሎት!
አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ ክስ መሰረተ።
ክሱ በ2 የተከፈለ ሲሆን፥ ከአቶ እስክንድር ነጋ እስከ 3ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ በሽብር ወንጀል ነው ክስ የተመሰረተው።
ቀሪዎቹ ከ4ኛ እስከ 7ኛ ተከሳሾች ላይ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭት በመፍጠር ወንጀል ነው ክስ የተመሰረተው።
ክሱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው የተመሰረተው። በአሁኑ ወቅት ችሎቱ ጉዳያቸውን እየተመለከተ ነው።
Via Tarik Adugna (FBC)

#UPDATE
በትግራይ ምርጫ ለሊቱ ድምፅ ሲቆጠር አድሮ ጠዋት በየምርጫ ጣብያው ውጤት ተለጥፏል።
ትላንት ጳጉሜ 4 በትግራይ የተካሄደው 6ኛው ክልላዊ ምርጫ ውጤት ፣ ድምፅ በተሰጠባቸው 2,672 የምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ንጋት ጀምሮ የየምርጫ ጣብያው ውጤት ይፋ እየተደረገ ነው።
በመቐለ ከተማ የሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ጣብያዎች የተለጠፈ ውጤት ህወሓት ከፍተኛ ድምፅ ማግኘቱ የሚያመለክት ሲሆን ባይቶና ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይና የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ተወካዮችም የህዝብ ድምፅ ማግኘታቸውን ዶቼ ቨለ (DW) ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የግል ትምህርት ቤቶች በ2013 አመት የትምህርት ዘመን ምዝገባ ምንም አይነት ክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ለSRTV አስታውቀዋል፡፡
የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ፋታህ፦
"እንደሚታወቀው ከነሃሴ 20/2012 ጀምሮ የግል ትምህርት ቤቶች ምዝገባ እየተካሄደ እንዳለ ይታወቃል። ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜ በፌደራል እና በሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ መሰረት ነው።
አሁን መግለፅ የምፈልገው ግን በግል ትምህርት ቤቶች የምዝገባ ወቅት ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት ቤቶች በተዘጉበት ወቅት የመምህራን ደሞዝ ለመሸፈን ወላጆችን ክፍያ እንዲፈፅሙ መጠየቁ የሚታወስ ነው።
ዛሬ ላይ ድግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የወቅቱን ሁኔታ በማየት ክፍያ የመጨመር አዝማሚያ የሚታይ በመሆኑ ጉዳዩ ከህግና ስርዓት ውጭ መሆኑን ሊረዱ ይገባል።
በዚህም ከአንዳንድ ወላጆች የደረሱን መረጃዎች በመኖራቸው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ይህን ጉዳይ የሚከታተል ይሆናል።"

በአፋር ክልል ሁለት ከተሞች አነስተኛ መጠን ያለው ርዕደ - መሬት መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
ጳጉሜ 3 እና 4 /2012 ዓ/ም በሎግያ-ሰመራ ከተማ በተለያዩ ሰአቶች ሶስት ጊዜ በሬክተር እስኬል መለኪያ ከአንድ እስከ ሁለት የሚለካ ቀላል ርዕደ-መሬት መከሰቱን ዩኒቨርሲቲው ለኢዜአ ገልጿል።
ምንም እንኳን በክስተቱ በአካባቢው የደረሰ ጉዳት ባይኖርም በቀጣይ በአካባቢዉ ተጨማሪ ክትትል እና ጥናቶችን ማድረግ አስፈላጊ ስለመሆኑ አመላካች ነገሮች መኖራቸዉ ተገልጿል።
ርዕደ-መሬቱ የተከሰተዉ በተለይም ጳጉሜ 3 በተለያዩ ሰዓታት መሆኑ የተነገረ ሲሆን ትናንትናም ማምሻውን ጨምሮ በተለያዩ ሰአታት አራት ጊዜ ርእደ-መሬቱ በተመሳሳይ አካባቢዎች ተመዝግቧል።

በላሬ ወረዳ ከ5,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል!
በጋምቤላ ክልል በላሬ ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ከአምስት ሺ (5,000) ሰዎች በላይ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው እደሚገኙ ከጋምቤላ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ጎርፉ ከአቅም በላይ በመሆኑ ህብረተሰቡ ላይ ችግር እየደረሰ ስለሆነ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋርዊቺ ቢየል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የላሬ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ኛዳክ ፓች በተደጋጋሚ በሚጥለው ዝናብ ምክናያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው በትምህርት ቤት አጥር ጊቢ ውስጥ ተጠልለው እደሚኖሩ ተናግረዋል።
ወይዘሮዋ አክለውም ጎርፉ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የአልባሳትና የምግብ ፍጆታ አቅርቦት መንግስት ድጋፍ እንድያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጋርዊች ቢየል በበኩላቸው በተመሳሳይ ጎርፉ በወረዳው ባሉ 28 ቀበሌዎች ለጊዜው ቁጥራቸው ባይታወቅም ከተጠቀሰው ቁጥር ባላይ ተፈናቃዮች እንዳሉ ነው የተናገሩት፡፡
ተጎጅዎቹ ባለባቸው የመጠለያ እና የምግብ ችግር ለተለያዩ በሽታዎች አደሚዳረጉ ገልጸው ችግሮችን ለመቅረፍ የባለድርሻ አካላት ርብርብ እደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

#Hawassa
የሀዋሳ ከተማ ትራንስፓርት እና መንገድ ልማት መምሪያ በትራንስፓርት ዘርፍ ተጥሎ የነበረው ታሪፍ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፊት ወደነበረበት መመለሱን ገልጿል።
አሽከርካሪዎች በወንበር ልክ መጫን አለባቸው ተብሏል ፤ ባጃጅ ሾፌሩን ጨምሮ ሶስት ሰዎችን ማሳፈር እንዳለበት ተገልጿል ፤ ከወንበር በላይ በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ሞተር ሳይክልን በተመለከተ አሽከርካሪው ብቻ መጠቀም እንዳለበት ከሀዋሳ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲኤምሲ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ በበርካታ የንግድ ሱቆች ፣መጋዘኖች እና ሬስቶራንቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ዛሬ በእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች በዛሬው ዕለት የ6 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ አድርገዋል።
በተጨማሪም የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 600ሺህ ብር እና ለአዲስ አመት በዓል ሁለት በሬዎችን በስጦታ አበርክቷል፡፡
ምንጭ፦ Mayor Office of AA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ዛሬ በእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች በዛሬው ዕለት የ6 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ አድርገዋል።
በተጨማሪም የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 600ሺህ ብር እና ለአዲስ አመት በዓል ሁለት በሬዎችን በስጦታ አበርክቷል፡፡
ምንጭ፦ Mayor Office of AA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ ከሳዐዲ አረቢያ 147 የሚሆኑ ሴቶችና ህጻናት ገብተዋል። በቀጣይ 5 ሳምንታት 2,000 የሚሆኑ የዛሬን ጨምሮ ሴቶችና ህጻናትን ይመጣሉ።
#Tsion
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Tsion
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia